
አሸባሪው የትህነግ ቡድን በኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ላይ በተሰወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ታላላቅ ጀብዱዎች መፈጸማቸውን የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ገለፁ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት በወልድያና አካባቢው፣ ጋይትና አካባቢው፣ ዛሬማና አካባቢው፣ ሰቆጣና አካባቢው፣ ጋሸናና አካባቢው በትህነግ የሽብር ቡድን ላይ በተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ታላላቅ ጀብዱዎች መፈጸማቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም የሽብር ቡድኑ የደረሰበት ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ከባድ መሆኑንም ነው አቶ ሙሉነህ የገለፁት፡፡
ይህ ሆኖ ሳለ የማህበረሰብ አንቂዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በማህበራዊ ተስስር ገፆች የትህነግ የሽብር ቡድንን ለመደምሰስ የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲታቀቡ አቶ ግዛቸው አሳስበዋል፡፡
በጦርነቱ ምክንያት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተፈናቅለዋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ለዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሁን ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ሳይኖር የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዋና ዳይሬክተሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሌላ በኩል አሸባሪው ትህነግ ወረራ በፈፀመባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች እያደረሰ ካለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት ባሻገር የአርሶ አደሩን የግብርና ምርት እንቅስቃሴ እያደናቀፈ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በሰሜን ወሎ፣ ዋግ ኽምራ፣ ሰሜን እና ምእራብ ጎንደር ዞኖች በአሸባሪው ትህነግ ወረራ ምክንያት በዚህ ክረምት ለማከናወን በታሰበው ልክ የእርሻ ስራን መፈፀም እንዳልተቻለ ቢሮው ገልጿል፡፡
በአማራ ክልል በዚህ የመኽር ወቅት 4.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ የነበረ ቢሆንም እስከአሁን በዘር የተሸፈነው 3.8 ሚሊዮን ሄክታር ብቻ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ ዶክተር መለስ መኮንን ገልፀዋል፡፡
ይህም በአሸባሪው የትህነግ ቡድን የወረራ እንቅስቃሴ ምክንያት መሆኑን ነው ኃላፊው የገለጹት፡፡
በሌላ በኩል በ12 ዞኖችና 112 ወረዳዎች ከ10 ሺህ ሄክታር በላይ የዘማች አርሶ አደሮች ማሳ በህብረተሰቡ ትብብር በዘር እንዲሸፈን ተደርጓል ብለዋል፡፡
ከ5ሺ ሄክታር መሬት በላይ የዘማች እርስ አደሮች ሰብል የማረም ስራ መከናወኑንም አክለዋል፡፡ የግብርና ስራው ለተራዘመ ጊዜ ተስተጓጉሎ እንዳይቆይ አርሶ አደሩ በተባበረ ክንዱ አሸባሪው ትህነግን ለመደምሰስ እያደረገው ያለውን ተጋድሎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ ቀርቧል፡፡ ©አማራ ኮሚዩኒኬሽን እና ኢብኮ
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply