ባለፉት 24 ሰዓታት “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ - #Handsoffethiopia” በሚል መሪ ቃል በተካሄደ የትዊተር ዓለም አቀፍ ዘመቻ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች የነቃ ተሳትፎ ማድረጋቸው ተገለፀ። 100 ሺህ ገደማ የትዊተር መልዕክት በተሰራጨበት ዘመቻ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዲከበር የሚጠይቁ እና አሸባሪው ህወሓት አገር ለማፍረስ እየሰራ ያለውን ሴራና ግፍ የሚያወግዙ መልዕክቶች ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እና መገናኛ ብዙሃን ጭምር ተላልፈዋል። በትዊተር ዘመቻው በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሚጠይቀው መልዕክት ዐቢይ አጀንዳ ነበር። የትዊተር ዘማቾቹ በተለይም ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡትን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማን እየጠቀሱ፣ … [Read more...] about ዘመቻ: “እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ – #Handsoffethiopia”