“ሀገርን ለማዳን እዘምታለሁ የትም መቼም በምንም” በሚል መሪ ቃል ፀረ ሰላም ሀይሎችን ለመፋለም ቆርጠው የተነሱ የቁርጥ ቀን ልጆች በሀገሪቷ በሚገኙ የውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤቶች በመግባት ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡
የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ከዚህ ቀደም በርካታ የሰራዊት አባላትን በሁለት ዙሮች አሰልጥኖ ያስመረቀ ሲሆን÷ በአሁኑ ጊዜም የ3ኛ ዙር ሰልጣኞችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡
አሰልጣኝ የ22ኛ ሻለቃ ዘመቻ ሀላፊ መቶ አለቃ ዲኔ መሀመድ የዚህ ዙር ሰልጣኞች ከሁለቱ ዙር ሰልጣኞች ለየት የሚያደርገው ሀገርን ለማፈራረስ የተነሱት የሀገር ሀዲዎች የህወሓት እና የሸኔ የሽብር ቡድኖችን ለመፋለምና ሀገርን ከመፈራረስ ታድጎ አንድነቷን ለማስቀጠል ለሀገሬ እዘምታለሁ በማለት ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ወደ ስልጠናው የተካተቱ መሆናቸው ነው ብለዋል፡፡
ሰልጣኞች በበኩላቸው እየተሰጣቸው ያለው ስልጠና ከፍተኛ የውትድርና አቅም እንደፈጠረላቸው እና ከሀዲዎቹን የሽብር ቡድኖች የሆኑትን የህወሓት ጁንታ እና የሸኔ ቡድንን ከኢትዮጵያ ለአንድና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስና ለመቅበር ዝግጁ መሆናቸውን ነው የገለፁት፡፡
“ከራስ በፊት ለህዝብ እና ለሀገር” የሚለውንና አንደኛውን የተቋሙን እሴት ሰራዊቱ እስከ ህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ህዝቦች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ ሀገርም እንዳትፈራርስ በተግባር እየተገበረው መሆኑንም አንስተዋል።
ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሱ ሀይሎች እራሳቸው ሲፈርሱ÷ ኢትዮጵያ ግን በጀግኖች ልጆቿ ደም እና አጥንት ታፍራና ተከብራ ትቀጥላለች ማለታቸውን ከሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ (ፋና)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply