“አደንዛዥ ዕጽ የሚሰጧቸው በበርሜል ሻይ አፍልተው በመቀላቀል ነው”
አሸባሪው ትህነግ (የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር) ዜጎችን ወደ ውትድርና ተመልምለው ለውጊያ የሚያደርሰው በሁለት መንገድ ነው፤ አንዱ ምንም የጦር ዕውቀትና ልምምድ ሳይኖራቸው በግድ ከሽፍታው ቡድን ጋር እንዲቀላቀሉ የተደረጉ ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አደንዛዠ ዕፅ አፍልተው ነው።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሰሞኑን የወጣው መረጃ እንደሚያመለክተው ትህነግ ህጻናት ልጆችን ለጦርነት እየመለመለ እንደሚሰማራ በማስረጃ ተረጋግጦበታል። ልጆቹ በተለይ ለዚህ ግዳጅ እንዲሰማሩ የሚደረግበትን አካሄድ በየኔታ ትዩብ ላይ የተናገረው በቅርቡ በምርጫ የተወዳደረው ማኅበራዊ አንቂ ብሩክ አበጋዝ ነው።
ብሩክ እንደሚለው ትህነግ ልጆቹን ከሰበሰበ በኋላ የጠጡት ምን እንደሆነ በማያውቁበት ሁኔታ እንደ መደበኛ የሚጠጣ ነገር ሻይ ይሰጣቸዋል። ልጆቹ የሚያውቁት ወይም የሚነገራቸው ሻዩ የሚሰጣቸው ለብርታት ተብሎ እንደሆነ ብቻ ነው።
በሌላ በኩል የኢትዮፕያ ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበው አሸባሪው ትህነግ ህጻናትን ለጦርነት እየማገደ ነው፤ ሚዛን አልባው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወንጀሉን ከማጋለጥ ይልቅ የጁንታው “የህዝብ ድጋፍ” ማሳያ አድርጎታል።
በዓለም አቀፍ ህግ ህጻናትን ለጦርነት መጠቀም ወንጀል መሆኑ እየታወቀ ራስ ወዳዱ ጁንታ እድሜያቸው ለትምህርት እንጂ ለጦርነት ያልደረሱ ህጻናትን በሀሽሽ አደንዝዞ ጦርነት ውስጥ እያሰለፈ ነው።
ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀንም ጉዳዩን በራሳቸው ዘገባ ጭምር ይዘው ቢወጡም ጉዳዩን ከማውገዝና አጥፊዎችን ከመኮንን ይልቅ በተቀራኒ ተሰልፈው የጁንታው ወንጀል አስተባባዮች ሆነዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በቅርቡ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ሕጻናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል። የመከላከያ ሠራዊቱ እነዚህን ሕጻናት ወታደሮች የመታደግ ሞራላዊ ግዴታ ወድቆበታል” ሲሉ የጉዳዩን አደገኛነት አስታውቀዋል።
የጁንታው አፈ ቀላጤ ጌታቸው ረዳ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓም በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከፈጸሙ በኋላ የህግ ማስከበር ዘመቻው ሲፋፋምባቸው የትግራይ ህጻናት ድንጋይም ቆንጨራም በመያዝ እንዲታገሉ ጥሪ ማድረጉ አይረሳም። አሁንም በተጨባጭ እየሆነ ያለው ይሄው ነው።
ዓለም፤ “… ስለ ርዳታና ስለ ረሐብ ሲናገር መቆየቱን ዘንግቶ ጁንታው ሕጻናትን ሲያሰልፍ እንኳን ዝምታን መርጧል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክታቸውን የገለጹት፤ አሁን ለጁንታው የተሰጠው እድል የመጨረሻ የሰላም አማራጭ መሆኑን በመጥቀስ ነው። (ኢፕድ)
ጎልጉል ከተለያዩ ማህበራዊ ገጾች እና ከራሱ ከጁንታው ደጋፊዎች ገጾች የሰበሰባቸውን የህጻናት “ወታደሮች” ምስሎችን እንዲህ አቅርቧቸዋል።
በተቃራኒው ጄኔቭ ሆኖ “ግፋ በለው” እያለ ህጻናቱን የሚማግደው የአሸባሪው ትህነግ አባል ቴድሮስ አድሃኖም ለራሱና ለልጆቹ በአውሮጳ የተደንደላቀቀና የቅምጥል ኑሮ የኖረ ነው። በጦር ወንጀለኝነት ሊጠየቅ ይገባዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
yigletu says
SHAME ON YOU ADHANOM ;;;
Tesfa says
ያለፉት ጠ/ሚ መለስ ከወርቃማው ከእናንተ በመወለዴ ደስ ይለኛል ሲሉ ራሳቸውንና በትግራይ ህዝብ ስም የሚዘርፉትን ፍርፋሪ ለቃሚዎች እንጂ በልቶ ለማደር የሚፍጨረጨረውን 98% የትግራይ ህዝብ ወክለው አልነበረም። ፓለቲካ ከመሸታ ቤት አይለይም። ድሮም ከሻቢያ ጋር ተቃቅፈው ሲተኙና በጋራ ሃገር ሲያፈርሱ አደንዛዥ እጽ ይጠቀሙ እንደነበረ ዛሬ በህይወት ያሉ ይናገራሉ። በበርሚል በሻሂ መልክ ተፈልቶ የሚሰጣቸው እነዚህ ህጻናትን ነው ወደ ጦር ግንባር ወስዶ በማራገፍ ባልገባቸው ጉዳይ እንደ ቅጠል እንዲረግፉ ወያኔ የሚልካቸው። የሚያሳዝነው ሞታቸው ሁሉ ለወያኔ ፓለቲካ መሆኑ ነው። በውጊያው ላይ የተገደሉትን ሁሉ ሰብስቦ በመውሰድ የአብይ መንግስት ይህን ሰራ ብሎ ለማሳጣት በአስከሬናቸው ላይ ሁሉ ፓለቲካ የሚሰራ ጨርቁን የጣለ ድርጅት ነው። ግራ የሚገባኝ ተምረናል፤ አውቀናል፤ መጥቀናል የሚሉን የትግራይ ልጆች ይህ ግፍና በደል እንዴት እንደማይታያቸው ነው። ሰው ነገርን ከባህር ማዶ ሆኖ በስማ በለው በውሸት ተለውሶ የሚሰራጨውን የወስላቶች ዜና ከመስማትና አምኖ ከመቀበል ይልቅ ለምን በቦታው ሰው ልከው ሁኔታውን አያጣሩም። በእኔ እምነት በየትኛውም መመዘኛ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጊዜ ያለፈበት የፓለቲካ ስልት የሚከተል፤ የትግራይን ህዝብ ለ 50 ዓመታት መነገጃ ያደረገ፤ ከአንድ መንደር ከአድዋ የሆኑ ቀለብተኞች በሃገሪቱ ጀርባ ላይ ሲናጥጡ የኖሩባት፤ አንድ ለአምስት በሚል አልባኒያዊ የፓለቲካ ህሳቤ ሰውን ቀፍድዶ የያዘ፤ ከሰላም ይልቅ ጦርነትን የሚያራምድ ራሱ ገድሎ ሰው ገደለው ብሎ ቀብር የሚቆም ፍጽም ፋሽሽታዊ ቡድን ነው። ይህ እውነት አይደለም የሚሉ ቱልቱላዎች መለስ ብለው በረሃ የቀሩትን የትግራይ አርሶ አደር ልጆችን መቁጠር ተገቢ ይሆናል። ከደርግ ጋር በተደረጉ ውጊያዎች ከሞቱት የትግራይ ልጆች ቁጥር ይልቅ ወያኔ በየምክንያቱ አፈር የመለሰባቸው የትግራይ ልጆች ይበዛሉ።
የሃገር አለቃ ከሆነ በህዋላ የሰራው ግፍ ጣራ ለመድረሱ የኢትዮጵያ ህዝብ ድንገት አፍ ውስጥ እንደገባች ትንኝ አክ እንትፍ ብሎ እንደተፋው የቅርብ ጊዜ ታሪካቸው ያሳያል። ሙት ይዞ ይሞታል ይላሉ አበው አሁን ማን ይሙት ጌታቸው ረዳ ለትግራይ ህዝብ ይገደዋል? ዶ/ር ደብረ ጽዪን ልጆቹንና ሚስቶቹን ባህር አሻግሮ የአርሶ አደር ልጆችን እሳት መማገድ ጀግና ያሰኘዋል? ጻድቃንና ሌሎችም የወያኔ ቁንጮዎች እንዴት እብደታችን አናታችን ላይ ወጥቶ ነው ተሳስተናል ሃገራችንና ህዝባችን አንጎዳም በማለት ነገሮችን ለማርገብ አይሞክሩም። ግን ከላይ እንዳልኩት ፓለቲካ ነቃን እናውቅልሃለን የሚሉ በዘርና በጎሳ በሃይማኖት ዙሪያ የተሰለፉ ወስላቶች የመኖሪያ ብልሃት ነው። ሌላ ትርጉም የለውም።
መስሎን ነው እንጂ አሜሪካ እንዲህ አለች፤ የአውሮፓ ህብረት ወያኔን ደገፈ፤ አረቡ አለም ከትግራይ ጋር ቆመ የሚባለው ሁሉ ዝንብን ለመግደል መዶሻ እንደማቀበል ነው። የእኛን መገዳደል፤ መፈራረስ ሁልጊዜ ይሻሉ። አፍርሰን ሰራን ያሏቸውን ሃገሮች ዛሬ የቆሙበትን ፊት ከነበራቸው አቋም ጋር መዝኖ መፍረድ ነው። በተለይ ነጩ ዓለም ጥቁሩን ህዝብ አይወድም። ይህ በመረጃ እንጂ ዝም ብሎ ከሚያልፍ ወንዝ የተቀዳ ወሬ አይደለም። በዚህ ሳቢያ የተገደሉ የአፍሪቃ መሪዎችን፤ የተመዘበረው አንጡራ ሃብቷ፤ ዛሬም ያንኑ ሃብት በመሻት እርስ በእርሳችን እንድንባላ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ እሳት እያቀበሉና እየጫሩ የሚያጫርሱን እነርሱ ናቸው። ይህ የማይታየው ተምሬአለሁ የሚል የቁም ደንቆሮ ነው። ግን እኛ ወንድምና እህታችን ገድለን መፎከር የምናቆመው መቼ ነው? ያለ ልባችን ጦር ሜዳ ተማግደን እኛ የእሳት ራት ሲሆን ጥቂቶች በእልፍ ደም የሚፈነጥዙበት ጊዜ ማብቂያው መቼ ነው? ሁሌ ዘራፍ እንዳሉ መኖር መታመም አይደለምን? ግን ሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ሁልጊዜ የጦር አውድማ መሆኑ እጅግ ያሳዝነኛል። የውጭ ወራሪዎች የሞከሩን በዚሁ በር ነው። እኛም ደግመን ደጋግመን የምንገዳደለው ሰሜናዊውን ነፋስ ተከትለን ነው። የትግራይ ልጆች በወያኔ ግፊት ሌላውን ከመግደል፤ ከመሞት እንዲድኑ ምን መደረግ አለበት? እብደታችን የሚያበቃበት ጊዜ ይናፍቀኛል። ሌላው የፓለቲካ ታንቡርና ጡርንባ ሁሉ የለቅሶ እንጂ የጀግንነት አይደለም። ሰው ወንድምና እህቱን ገድሎ ጎራው የሚልባት ሃገር ጤና የጎደላት ምድር ናት። የደም መፋሰሱ የማብቂያ ጊዜ ይናፍቀኛል። ይመጣ ይሆን? በቃኝ!