የትግራይ ህዝብ በአሸባሪው ህወሀት ቡድን የተጋረጠበትን የመጥፋት አደጋ መታደግ አላማውን ያደረገ ንቅናቄ ተመሰረተ።
ንቅናቄው “ራዕይ የተጋሩ ኢትዮጵያዊያን ሀገር አቀፍ ህዝባዊ ንቅናቄ” የሚል ስያሜ እንዳለው ተገልጿል።
ንቅናቄው በትግራይ ክልል ተወላጆች የተመሰረተ ሲሆን ለጥቂት የህወሓት አሸባሪ ቡድን ተብሎ የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያውያን ጋር እንዲለያይ ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ እንደሚቃወም በንቅናቄው ይፋዊ ምስረታ መግለጫ ላይ ተጠቅሷል።
የህወሓት የሽብር ቡድን ከጥንት ጀምሮ ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል እቅድ እንዳለው በማኒፌስቶው ጭምር ያስቀመጠ መሆኑን ያስታወሱት መግለጫውን የሰጡት የክልሉ ተወላጆች ይህ እንዲሆን መፍቀድ በትግራይ ህዝብ ላይ ክህደት መፈጸም ነው ብለዋል።
በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን አይደለንም የሚሉ ዜጎች የትግራይን ህዝብ እንደማይወክሉ ተገልጿል።
ንቅናቄው ከየትኛውም ሀይማኖትና የፖለቲካ ፖርቲ ነጻ ነው የተባለ ሲሆን ሀሉም የትግራይ ተወላጆች እንዲቀላቀሉና ሶስተኛ ትውልድ እያስጨረሰ ያለውን የሽብር ቡድን በጋራ እንድንታገል ሲል ጥሪውን አቅርቧል። (ኢብኮ)
በአቶ ሊላይ የሚመራው ይህ ድርጅት አስቀድመው ከተመሠረቱትና በተመሳሳይ አቋም ሲታገሉ ከነበሩት የነ ዶ/ር አረጋዊ በርሔ ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጋር አብረው ለምን እንደማይሠሩ ባይገልጹም የእንደርታው ተወላጅ አቶ ሊላይ የአድዋውን ዶ/ር አረጋዊ ከነ ስብሃት ነጋ እኩል ሲወነጅሉ በተደጋጋሚ መሰማታቸው የሚታወቅ ነው።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply