ሽብርተኛው የህወሀት ሽብርተኛ ቡድን አገራችንን ለመበታተንና ህዝባችንን አንገት ለማስደፋት የከፈተብንን ጦርነት ለመመከት በማይፀብሪ ግንባር የተሰማሩት የምዕራብ ዕዝ ፣ የአማራ ልዩ ሀይል ፣ ህዝባዊ ሚሊሻ ፣ ፋኖ እና የክተት ጥሪውን ተቀብለው የተሰለፉ ሀይሎች አንፀባራቂ ጀግንነት በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።
ጁንታው ባለፉት ቀናት የሰነዘረውን ማጥቃት በመመከትና ወደ መልሶ ማጥቃት በመሸጋገር በተወሰደው እርምጃ 222 የጠላት ሀይል ተደምስሷል።
01 ዲሽቃ፣ 04 መትረየስ፣ 01 ስናይፐር፣ 04 ተተካይ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 31 ኋላቀር መሳሪያ፣ 25 ክላሽንኮቭ ጠመንጃ፣ 4 ሺ የብሬን ጥይት፣ 3ሺ800 የብሬን ጥይት፣ 100 የዲሽቃ ጥይት በመማረክ በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ችሏል።
የምዕራብ ትንታጎቹ በግንባሩ ከተሰማራው ሀይል ጋር በመሆን የተበተነውን የሽብርተኛ ቡድን በማደን እና ጥሏቸው የሸሻቸውን ቁሳቁሶች በመሰብሰብ ላይ ናቸው።
መላክ በቃሉ (ከግዳጅ ቀጣና) ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply