
አምንስቲ ኢንተርናሽናል ለምርጫ ያነሳሁትን ፎቶ ወስዶ የተጠቀመበትን መንገድ እንዲያስተካክል የተቻለውን ጥረት አድርጎ የማይፈታ ከሆነ ጉዳዩን በተመለከተ ተቋሙን ለመክሰስ እገደዳለሁ ሲል የፎቶግራፍ ጋዜጠኛ አማኑኤል ስለሺ አስታወቀ።
ጋዜጠኛ አማኑኤል በጉዳዩ ዙሪያ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገረው፤ አምንስቲ ኢንትርናሽናልን ለማነጋገር ጥረት እያደረገ ነው።
“በስልክና በኢ-ሜይል ለማግኝት ጥረት እያረግን ቢሆንም እስካሁን ምንም ምላሽ አልሰጡንም። አሁን 22 ሰዓታት አልፎታል። በርካታ አለም አቀፍ ሚዲያዎችና ተቋማት ይህንን የተቀናበረ ምስል ተቀባብለውታል። ለራሳቸው ዓላማ የሚያውሉት እንኳን ቢሆን መቀየር የተከለከለ ነው” ሲል ተናግሯል።
አምነስቲ ለመረጃው የተጠቀመውን ፎቶ ግራፍ በተመለከተ በውይይት ለመፍታት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አመልክቷል።
“በኢትዮጵያ የሚገኘውን የአምኒስቲ ጽህፈት ቤት ለማናገር ጥረት አደርጋለሁ፤ ችግሩን በመግባባት ለመቋጨት እሞክራለሁ። እንደ ባለሙያ በፍርድ ቤት ክስ መስርቶ መጠየቅም ይቻላል” ብሏል።

አምንስቲ ፎቶውን የማየነሳና ተገቢውን ማስተካከያ የማያደርግ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ህግ ለመውሰድ እንድሚቻል በመጥቀስ ካላስፈላጊ እሰጥ አገባ ይልቅ በመግባባት ለመፍታት በሚል ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።
“አምኒስቲ ኢንትርናሽናልን ለማነጋገር እስከ ለሊቱ 9:00 ሰዓት ስንሞክር ነበር። ነገር ግን ምንም ምላሽ አልሰጡንም። አሁንም ምላሻቸውን እየተጠባበቅን እንገኛለን” ሲል ፎቶግራፍ ጋዜጠኛ አማኑአል ጠቅሷል።
ፎቶው በኢትዮጵያ በተካሄደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ወደ ምርጫ ጣቢያ ያመሩ መራጮች በፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ ሲደረግላቸው የሚያሳይ መሆኑን ያስታወሰው ጋዜጠኛው፤ አምንስቲ በተቀነባበር መንገድ ከአውድ ውጭና ያለአግባብ ስሜን ተጠቅሞበታል ብሏል።
ደንበኞቻችን ምንም አይነት ፎቶ ሲጠቀሙ ቀይረው እንዲጠቀሙ አይፈቀድም፣ ከአውድ ውጪ በሆነ መንገድ በማቀናበር መቀየር የሚከለክል የተቋማችን ህግም አለ፤ ከእዚህ በተጨማሪም ተዛማጅነት የሌለው መልዕክት ማስተላለፍ እንደማይቻል በህጉ ተጠቅሷል፤ ነገር ግን አምንሰቲ ህግ በመጣስ ላልተገባ ዓላማ አውሎታል ሲል ገልጿል።
“በቲውተር ገፄ ምስሉ ያላግባብ ተቀይሮ ላልተገባው ዓላማ መዋሉን አሳውቄያለሁ። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትም ድርጊቱን ለማጋለጥ የሄደበትን መንገድ እንደ አንድ አማራጭ እወስደዋለሁ” ብሏል።
እኛ እንደ አንድ ትልቅ ተቋም በፍርድ ቤት የመክሰስ መብት አለን። ነገር ግን ነገሮች እንዳይካረሩ በሚል በንግግር ለመፍታት ጥረት እያደረግን እንገኛለን ሲልም ተናግሯል። (ዘላለም ግዛው)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply