• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአዲስ አበባ 325 የትህነግ አሸባሪዎች ከነመሣሪያቸው ተይዘዋል

July 19, 2021 09:24 pm by Editor Leave a Comment

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በጥናት ላይ በመመስረት እና ከህዝብ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በከተማችን በስጋትነት በተለዩ የተለያዩ ንግድ ቤቶች እና ድርጅቶች ላይ ባደረገው ብርበራ እና ፍተሻ ልዩ ልዩ የጦር መሳሪዎችን፣ ሰነዶችን እና የፀጥታ አካላት የደንብ አልባሳትን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።

መንግስት የህግ የበላይነትን ለማስከበር በህወሃት ጁንታ ቡድን ላይ እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ ህግ የማስከበር ዘመቻው በድል ተጠናቆ የሀገር መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ጨምሮ መላው ትግራይን መቆጣጠሩ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ሐምሌ 11 ቀን 2013 ዓ/ም በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት በዚህ ሀገርን የማዳን እና ትግራይን የመታደግ ዘመቻ አብዛኞቹ የጁንታው አመራሮች ሲማረኩ፣ የተወሰኑት ደግሞ ተደምስሰዋል።

ወቅቱ የእርሻ በመሆኑ የትግራይ አርሶ አደሮች በእርሻ ስራቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ እና ለህዝብ ሰላም ሲባል መንግስት የተናጠል ተኩስ ማቆም እርምጃ መውሰዱን ኮሚሽነሩ አስታውሰው ነገር ግን ጁንታውና የጁንታው ደጋፊዎች የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም እርምጃ እንደ ፍርሃት በመቁጠር ልዩ ልዩ ሚዲያዎችንና ማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመጠቀም የበሬ ወለደ አሉባልታ በማናፈስ ሀገርን የማተራመስ ሴራቸውን እንደ አዲስ ለማስቀጠል ላይ ታች ሲሉ መሰንበታቸውን ገልፀዋል።

በጁንታው የአገዛዝ ዘመን ልዩ ተጠቃሚ የነበሩ እና ለውጡ ስጋት ላይ የጣላቸው የጁንታው ናፋቂዎችና ደጋፊዎች ቀደም ባለው ጊዜ ህግ የማስከበር ዘመቻውን ለማደናቀፍ ብሎም ለውጡን ለመቀልበስ ከጁንታው ተልዕኮ ተቀብለው ቢንቀሳቀሱም በፀጥታ ኃይላችን ጥረት በህዝባችን ቅን ተባባሪነት ሴራቸውን ማክሸፍ ተችሏል ብለዋል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው።

በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ወቅት በአዲስ አበባ ብቻ ከጁንታው ተላላኪዎች እጅ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የሚታወቅ ነው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በጥናት ላይ በመመስረት እና ከህዝብ የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ ከሰኔ 19 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ/ም በሁሉም ክፍለ ከተሞች ባከናወነው ህግን የማስከበር ተግባር አሸባሪው ህወሃት በሀይል መቀሌን እንደተቆጣጠረ አስመስሎ ያናፈሰውን ሀሰተኛ መረጃ በማስተጋባት እንዲሁም በከተማችን ብጥብጥና ረብሻ ለማስነሳት ከጁንታው ተልእኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 325 ግለሰቦች በህግ አግባብ ተይዘው ምርመራ እየተጠራባቸው እንደሚገኝ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ገልፀዋል።

በተጨማሪም በስጋትነት በተለዩ ግሮሰሪዎች፣ ጭፈራ ቤቶች፣ ሆቴሎች እና ሌሎች ንግድ ቤቶች በድምሩ 793 ተቋማት ላይ ፖሊስ ባደረገው ብርበራ እና ፍተሻ 126 ልዩ ልዩ ሽጉጦች፣ 918 የሽጉጥ ጥይት እና 124 የሽጉጥ ካርታዎች፣ 3 ክላሽኢንኮቭ ጠመንጃ፣ 390 የክላሽ ጥይት ከ4 ካርታ ጋር፣ 1 ኤስ.ኬ.ኤስ እና 1 ኡዚ መሳሪያ በኤግዚቢትነት ተይዘዋል።

ከተጠርጣሪዎቹ እጅ በርካታ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የቀድሞ የደንብ ልብስ፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን፣ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ፣ የፖሊስና የሀገር መከላከያ ማዕረጎች እንዲሁም ልዩ ልዩ መለዮዎች እንደተያዙም ኮሚሽነር ጌቱ አብራርተዋል። ከእነዚህ በተጨማሪ ለፖሊስ ምርመራ የሚረዱ መረጃዎች የተገኘባቸው ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፍላሾች፣ ታብሌት ስልኮች፣ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች፣ ሲም ካርድ፣ የፋክስ ማሽን እንዲሁም ጂ.ፒ.ኤስ እንደተያዙ ኮሚሽነር ጌቱ ጠቅሰዋል።

የጁንታው ቡድን አባላት ውይይት ሲያደርጉበት የነበረ ቃለ ጉባኤ እና የህወሃት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም የጁንታው መልዕክት የተጫነባቸው ሞባይል ስልኮች መገኘታቸው የጁንታው ተላላኪዎች አደረጃጀት ፈጥረው እና ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሰቀሱ እንደነበር በምርመራ መረጋገጡን ኮሚሽነሩ አብራርተዋል። ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ምርመራ ከ175 ሺ በላይ ብር እና 11 ሺ የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ከጁንታው ተላላኪዎችና ደጋፊዎች እጅ ተይዟል።

በከተማችን አዲስ አበባ መንግስት የወሰደውን የሰላም ዕርምጃ ከሽንፈት የቆጠሩ ተሸሽገውና አንገታቸውን ደፍተው የነበሩ የጁንታው ተላላኪዎች በአንዳንድ መዝናኛ እና ጭፈራ ቤቶች ሰንደቅ አላማችንን በሚያዋርድ መልኩ ያልተገባ ድርጊት እየፈፀሙ ሲጨፍሩ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።

ምንም እንኳን የጁንታው አፈ-ቀላጤዎች በተለመደው የሐሰት ፕሮፖጋንዳ አሸንፈናል እያሉ መቃዠታቸው ለሁሉም ግልፅ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ ከእኛው ጋር የሚኖሩ፣ ሰላማቸው ተጠብቆላቸው የጥይት ድምፅ ሳይሰሙ በሠላም ውለው በሠላም እያደሩ እኛው መሐል ሆነው የሽብርተኛ ቡድኑ አጋር መሆናቸውን በግልፅ አሳይተዋል።

የከተማችን ሰላም ወዳድ ነዋሪ ለዘመናት በገነባው ጨዋነት እና አርቆ አስተዋይነት ግለሰቦቹ የጁንታው ተላላኪዎች መሆናቸውን በተግባራቸው ቢያረጋግጥም ለሚመለከታቸው የፍትህ አካላት ጥቆማ በመስጠት ህጋዊ የዜግነት ኃላፊነቱን ከመወጣት ውጪ እንደ እነሱ ስሜታዊነት አላሸነፈውም ፤አንዳችም ህገወጥ ተግባር አልፈፀመም። በዚህ አጋጣሚ ሠላም ወዳድ ለሆነው ለከተማችን ነዋሪ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በራሳቸው እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም መላው የከተማችን ነዋሪዎች በተደራጀ እና በነቃ ትብብር አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ ፣ ከፖሊስ እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ያላቸውን የመረጃ ልውውጥ እንዲያጠናክሩ ፣ ወቅታዊ መረጃን በየዕለቱ ከትክክለኛው የመረጃ ምንጭ እንዲከታተሉ እና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም ወዲያውኑ ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ጥሪያቸውን አስተላፈዋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf children soldiers

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule