
የዕርዳታ አቅራቢዎች ከኢትዮጵያ ኢትዮጵያ በአፍራሽ ስራ ላይ ተሰማርተዋል ያለቻቸውን አንዳንድ የእርዳታ አቅራቢዎችን ከሀገር ልታባርር እንደምትችል አስጠነቀቀች።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥረው ነበር።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፥ “አንዳንድ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪዎች በሌሎች ሀገራት እንደተለመደው በኢትዮጵያም ከዚህ በፊት እንደታየው ከእርዳታ እህልና ከእርዳታ አቅርቦት ጋር በማያያዝ ሌላኛውን ወገን የማስታጠቅ ፣ ትግሉ፣ እንቅስቃሴው እንዳይቆም፣ ቀውሱ እንዳይበርድ ለማድረግ የሚያስችል አፍራሽ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል” ብለዋል።
አክለውም፥ በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ባለፉት 8 ወራት ይህ ሌላኛውን ወገን ለማስታጠቅ የሚደረገው ሙከራ እንዳጋጠመ ፤ ይህ ጉዳይ መልክ መያዝ እንዳለበት መንግስት ሲያሳስብ እንደነበር ገልፀዋል።
አምባሳደሩ፥ “አንዳንድ አካላት በተለይም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብዓዊ እርዳታ እናስተባብራለን የሚሉ አንዳንድ ወገኖች በተናጠል ኢትዮጵያ ውስጥ ተቀምጠው እንዲሚያስተባብሩ ከተመደቡ ሰዎቻቸው ውጭ ከርቀት ሆነው ከእርዳታ ይልቅ የፕሮፖጋንዳ ስራ የማስተባበር፣ ኢትዮጵያን የማዋከብ እና የማጠልሸት ዘመቻ ከፍተው ይገኛሉ” ሲሉ ወቅሰዋል።
መንግስት ከዚህ አይነት አፍራሽ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማስጠንቀቅ ሞክሯል ያሉት አምባሳደር ሬድዋን ይህን ድርጊት የማይቆም ከሆነ መንግስት ሀገርን ለማዳን ስለሚገደድ ከአንዳንዶቹ ጋር አብሮ የመስራቱን ሁኔታ እንደሚያጤን አንዳንዶቹንም ከሀገር ለማስወጣት እንደሚገደድ አስጠንቅቀዋል።
ተመድ ሆነ ማንኛውም ኢትዮጵያን እረዳለሁ የሚል /እርዳታ አቀርባለሁ የሚል አካል ስራው በእርዳታና ሰብዓዊነት ላይ ብቻ ታጥሮ መንቀሳቀስ እንዳለበት መንግስት ያሳስባል ሲሉም አክለዋል። (ቲክቫህ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply