የቤተ-ክርስቲያን መስኮት ሰብረው ከሙዳየ ምፅዋት ገንዘብ ሰርቀው ሊሰወሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ። በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ጊሚሴ ቀበሌ ቤተክርስቲያን ሰብረው ገንዘብ የዘረፉ ግለሰቦች በሁለት ወንድማማች እና በአከባቢው ህብረተሰብ ትብብር ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጋቸውን ወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ትዛዙ ፍቅሬና አብርሀም ሞላ የተባሉት ተጠርጣሪዎቹ መድሀኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን መስኮት ሰብረው ከሙዳየ ምፅዋት ውስጥ ገንዘብ ሰርቀው ሊሰወሩ ሲሉ በመቅቡል መሀመድ፣ በሀይሩ መሀመድ እና በአካባቢው ማህበረሰብ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ ተይዘው ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አለማየሁ ደነቀ ተናግረዋል። ወንጀለኛ አብርሀም ሞላ ከዚህ በፊትም ነጌሳ ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የተቀመጠ ጤፍ በመዝረፍ ክስ ቢመሰረትበትም እድሜው አልደረሰም … [Read more...] about ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ
News
ዜና
ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ
አርሶ አደር ዳንኤል ሾጦጦ ይባላሉ፤ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የሺጋዶ ቀበሌ ነዋሪ ናቸዉ። ባላቸው አነስተኛ መሬት ላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሰብሎችን በማምረት ይተዳደራሉ።አርሶ አደሩ ማሳቸውን አቋርጣ የሚታልፍ አነስተኛ ወንዝ በመጥለፍ ባዘጋጁዋቸዉ ገንዳዎች ዓሣ የማልማት ሀሳብ ይዘዉ ወደ ተግባር ገቡ፤ በእነዚህ የዉኃ ገንዳዎች 6 ሺህ የዓሳ ጫጩቶችን ወደማርባት ተሸጋገሩ።በአሁኑ ወቅት የሚያረቡትን የዓሣ ጫጬት ብዛት እስከ 80 ሺህ ማድረስ ችለዋል። የገንዳዎቹንም ቁጥር ወደ 3 አሳድገዋል። (ቲክቫህ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ
ተስፋቢሱ ቴድሮስ
በዕውቀት ማነስ የሚሰቃየውና ሐኪም ሳይሆን የዓለምን የጤና መሥሪያቤት እየመራ ያለው ቴድሮስ አድሃኖም ተስፋው የተበተነ ይመስላል። በነ ቢል ጌትስና ወዳጆቻቸው ድጋፍ ያለብቃት አናት ላይ ላይ የተቀመጠው ቴድሮሰ አድሃኖም አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፈው የተቀጠረበትን መሥሪያቤት በማገልገል ሳይሆን እንደ ፍንዳታ ስልኩ ላይ ተጥዶ ማኅበራዊ ሚዲያውን በማሰስ ነው። ነጋጠባ ትግራይ ትሰርዕ እያለ የሚፖስተው ቴድሮስ ከዱሮ የተጠናወተው ሰካራምነት አሁን ብሶበታል። በድጋሚ እንዳይመረጥ ዘመቻ ተከፍቶበት የነበረ ቢሆንም ጌቶቹ በቀጣይ ዓመታት የሚጠርግላቸው ቆሻሻ ስላለ አርፈህ ቀጥል ብለውታል። እርሱም ተስፋ ቆርጦ በመጠጥ መደንዘዙን ቀጥሎበታል። በትግራይ ከተደረገው ውጊያ በፊት ጀምሮ ትግራይን ልክ እንደ አገር በማስመሰል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲታትር የነበረው ቴድሮስ አንዳንዴ ቀጥተኛ ሌሎች … [Read more...] about ተስፋቢሱ ቴድሮስ
ከሽፏል!
የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት HR6600/S3199 ሕግ ሆኖ እንዲፀድቅ የቀረበው የውሳኔ ኃሳብ እንዲቋረጥ ወሰነ። HR6600 እና S3199 ረቂቅ ሕጎች ሕግ ሆነው ከመውጣት እንዲዘገዩ የአሜሪካ ኮንግረስ እና ሴኔት ውሳኔ ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በትዊተር ገጹ አስታውቋል። ረቂቅ ህጉ እንዲቋረጥ ለጊዜው ከስምምነት የተደረሰበት ውሳኔ በቀጣይም ህግ ሆነው እንዳይፀድቁ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው የዲፕሎማሲ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ካውንስሉ አሳስቧል። የኢትዮጵያ አሜሪካ ሲቪክ ካውንስል በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫና በመቃወምና ዳያስፖራ ማህበረሰቡን ጭምር በማስተባበር ከፍተኛ የህዝብ ዲፕሎማሲ ስራ በመስራት ላይ ያለ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገ ተቋም ነው። (AMN) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከሽፏል!
የምግብ ዘይት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ተከማችቶ ተገኘ
በአዲስ አበባ ከተማ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ በወረዳ 03 ያለአግባብ የተከማቸ የምግብ ዘይት በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል። ክ/ከተማው በ11 ሱቆች ላይ ተደረገ ባለው ፍተሻ 442 ሊትር ዘይት በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን አሳውቋል። ፍተሻ የተደረገው በወቅታዊ የዋጋ ንረት ምክንያት ካሉ 6 ቀጠናዎች በ3ቱ ቀጠናዎች ላይ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል። ክ/ከተማው በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት ባልተገባ ቦታ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ተደብቆ መገኘቱን የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ እንደዚህ አይነት ድርጊት የሚፈፅሙትን "ሌባን ሌባ " ሲል እንዲያጋልጥ ጥሪ አቀርቧል። በአግባቡ ስራቸው ላይ የሚገኙ ነጋዴዎች አሁን በያዙት ልክ ዘይትን ወደ ፊት በማምጣት መሸጥ ይኖረባቸዋል የተባለ ሲሆን ህገወጥ ስራዎችን በሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ ንግድ ፍቃድ መሰረዝ ጨምሮ ጠበቅ ያሉ እርምጃዎች … [Read more...] about የምግብ ዘይት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ተከማችቶ ተገኘ
166, 800 የአሜሪካን ዶላር፤ 19,850 ዩሮና ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያ ተያዘ
መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ ያደረገ አንድ ህገወጥ የገንዘብ አዘዋዋሪ ግለሰብ ዶላር እና ዩሮ በመኪና ጭኖ ወደ ጅቡቲ በጉዞ ላይ እያለ በቁጥጥር ስር ውሏል። ግለሰቡ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-68991 በሆነ ኮንቴነር ተሽከርካሪ ላይ 166 ሺህ 800 የአሜሪካን ዶላር እና 19 ሺህ 850 ዩሮ በመጫንና መዳረሻውን ጅቡቲ በማድረግ በመጓዝ ላይ እያለ በተደረገ ጥብቅ ክትትል መያዙን የኢፕድ ምንጮች ገልጸዋል። በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ላይ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በደረሰው ጥቆማ አዘዋዋሪውን ከነ ገንዘቡ በቁጥጥር ስር እንዲውል ማድረጉንም ነው ምንጮቻችን ጨምረው የገለጹት፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መነሻቸውን ሀረሪ ክልል ሀረር ከተማ ያደረጉ ሶስት ህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ግለሰቦችም ከእነጦር መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እነዚሁ … [Read more...] about 166, 800 የአሜሪካን ዶላር፤ 19,850 ዩሮና ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያ ተያዘ
በሰባት ወር ውስጥ ከ2.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ በዳያስፖራው ወደ አገር ቤት ተልኳል
ዳያስፖራው በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት ወራት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ (ሬሚታንስ) በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ። በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት ዳያስፖራው 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገር ቤት በሕጋዊ መንገድ እንዲልክ ታቅዶ 2 ነጥብ 35 ቢሊዮን ዶላር መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል። በበጀት ዓመቱም አራት ቢሊዮን ዶላር ከሬሚታንስ ለመሰብሰብ መታቀዱን አመልክቷል። በተያያዘም በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት 4 ሺህ 83 የዳያስፖራ አባላት በአገር ውስጥ በሚገኙ ባንኮች 4 ሚሊዮን 953 ሺህ 333 ዶላር ተቀማጭ እንዲያደርጉ ታቅዶ፤4 ሺህ 7 ዳያስፖራዎች ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸውን ገልጿል። ዳያስፖራው … [Read more...] about በሰባት ወር ውስጥ ከ2.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ በዳያስፖራው ወደ አገር ቤት ተልኳል
፻፳፮ኛው የዓድዋ በዓል በፎቶ
“… የተተከለው ድንኳን ሲታይ ከብዛቱ የተነሳ አፍሪካ ኤሮጳን ለመጠራረግ የተነሳች ይመስላል፡፡ የጦርነቱ ዕለት ኢትዮጵያውያኑ ደማቅ ቀለም ያለው ካባ ለብሰው፤ ጠመንጃና ጦር ይዘው፤ ጎራዴ ታጥቀው፤ የነብር ያንበሳ ቆዳ ለብሰው፤ አዝማሪዎቹ እየዘፈኑ፤ ቄሶች፤ ልጆች፤ ሴቶች ሳይቀሩ ፀሐይዋ ፈንጠቅ ስትል በተራራው ላይ በታዩ ጊዜ የኢጣሊያን ክፍል አሸበሩት” የበርክለይ ምስክርነት፤ አጤ ምኒልክ በጳውሎስ ኞኞ፤ ገጽ 195 ዛሬ የተከበረው ፻፳፮ኛው የዓድዋ በዓል በእምዬ ምኒልክ አደባባይና በተለያዩ አካባቢዎች ተከብሯል። በፎቶ ይህንን ይመስላል። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ፻፳፮ኛው የዓድዋ በዓል በፎቶ
ሩሲያ የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል ልታዘምን ነው
የሩሲያ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ለረጅም አመታት የዘለቀ መልካም ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያለው ሲሆን የዚህም ጉብኝት ዓላማ የዚሁ ትብብር አንድ አካል መሆኑ ተመልክቷል ፡፡ የሩሲያ ፌዴሬሽን ባህር ኃይል ልዑክ መሪ በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌዴሬሽን ተልዕኮ ሀላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በጉብኝታቸው ወቅት እንደተናገሩት ፣ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያውያን በጋራ የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባህር ኃይልና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ አቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ ፣ የኢትዮጵያ … [Read more...] about ሩሲያ የኢትዮጵያን ባሕር ኃይል ልታዘምን ነው
“አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እንቅስቃሴ ለመጀመር ታስቧል”
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም የተለያዩ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱ ለሰላም ምክክሩ ገንቢ ሚና እንዳለው በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡ ህወሃት ጸብ በመጫር የእርዳታ ስራውን እያስተጓጎለ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከተመድ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው የገለጹ ሲሆን በተግባር እያሳየ መሆኑን የተመድ ምክትል ጸሀፊ አሚና መሀመድ መናገራቸውንም አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ከታላቁ ህዳሴ ግድብና ከድንበር ጋር በተያያዘ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ውይይት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡ የመተማ ገላባት መንገድ እንደቀደሙ ሁሉ ለዜጎች እንቅስቃሴ ክፍት እንዲሆን ከሱዳን መንግሥት ጋር ንግግር መደረጉንም ማንሳታቸውን የኢዜአ ዘገባ … [Read more...] about “አማርኛ ቋንቋ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲሆን እንቅስቃሴ ለመጀመር ታስቧል”










