ዳያስፖራው በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት ወራት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ (ሬሚታንስ) በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት ዳያስፖራው 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገር ቤት በሕጋዊ መንገድ እንዲልክ ታቅዶ 2 ነጥብ 35 ቢሊዮን ዶላር መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
በበጀት ዓመቱም አራት ቢሊዮን ዶላር ከሬሚታንስ ለመሰብሰብ መታቀዱን አመልክቷል።
በተያያዘም በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት 4 ሺህ 83 የዳያስፖራ አባላት በአገር ውስጥ በሚገኙ ባንኮች 4 ሚሊዮን 953 ሺህ 333 ዶላር ተቀማጭ እንዲያደርጉ ታቅዶ፤4 ሺህ 7 ዳያስፖራዎች ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸውን ገልጿል።
ዳያስፖራው በ’አይዞን ኢትዮጵያ’ የበይነ መረብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ አማራጭ እና በውጭ አገራት በሚገኙ ሚሲዮኖች አማካኝነት ለተፈናቀሉ ዜጎችና ለተጎዱ መሰረተ ልማቶች መልሶ ግንባታ የሚውል ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ በገንዘብና በአይነት ድጋፍ ማድረጉን ኤጀንሲው አመልክቷል።
በ’አይዞን ኢትዮጵያ’ በ’አይዞን ኢትዮጵያ’ የበይነ መረብ የገንዘብ ማሰባሰቢያ አማራጭ ከ6 ነጥብ 1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ከ25 ሺህ 400 በላይ ዳያስፖራዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች መሰብሰቡ ተጠቁሟል።
ዳያስፖራው በሰባት ወሩ ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሕልውና ዘመቻ ከ109 ሚሊዮን 8 ሚሊዮን ብር በላይ በገንዘብና አይነት ድጋፍ ማድረጉን ነው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ያስታወቀው።
በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት በኢንቨስትመንትና ንግድ ላይ ለመሰማራት 895 ዳያስፖራዎች ፍላጎት ማሳየታቸውን አመልክቷል።
ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ ዳያስፖራው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ትግል በማድረግ እንዲሁም ባለው ሙያ የእውቀት፣ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ገልጿል። የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ለኢትዮጵያ ልማትና እድገት እያበረከቱት ያለውን አስተዋጽኦ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል። (ኢ ፕ ድ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply