ዳያስፖራው በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት ወራት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ (ሬሚታንስ) በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ቤት መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታወቀ። በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት ዳያስፖራው 2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ወደ አገር ቤት በሕጋዊ መንገድ እንዲልክ ታቅዶ 2 ነጥብ 35 ቢሊዮን ዶላር መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል። በበጀት ዓመቱም አራት ቢሊዮን ዶላር ከሬሚታንስ ለመሰብሰብ መታቀዱን አመልክቷል። በተያያዘም በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት 4 ሺህ 83 የዳያስፖራ አባላት በአገር ውስጥ በሚገኙ ባንኮች 4 ሚሊዮን 953 ሺህ 333 ዶላር ተቀማጭ እንዲያደርጉ ታቅዶ፤4 ሺህ 7 ዳያስፖራዎች ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተቀማጭ ማድረጋቸውን ገልጿል። ዳያስፖራው … [Read more...] about በሰባት ወር ውስጥ ከ2.3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በሕጋዊ መንገድ በዳያስፖራው ወደ አገር ቤት ተልኳል