በዕውቀት ማነስ የሚሰቃየውና ሐኪም ሳይሆን የዓለምን የጤና መሥሪያቤት እየመራ ያለው ቴድሮስ አድሃኖም ተስፋው የተበተነ ይመስላል። በነ ቢል ጌትስና ወዳጆቻቸው ድጋፍ ያለብቃት አናት ላይ ላይ የተቀመጠው ቴድሮሰ አድሃኖም አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፈው የተቀጠረበትን መሥሪያቤት በማገልገል ሳይሆን እንደ ፍንዳታ ስልኩ ላይ ተጥዶ ማኅበራዊ ሚዲያውን በማሰስ ነው።
ነጋጠባ ትግራይ ትሰርዕ እያለ የሚፖስተው ቴድሮስ ከዱሮ የተጠናወተው ሰካራምነት አሁን ብሶበታል። በድጋሚ እንዳይመረጥ ዘመቻ ተከፍቶበት የነበረ ቢሆንም ጌቶቹ በቀጣይ ዓመታት የሚጠርግላቸው ቆሻሻ ስላለ አርፈህ ቀጥል ብለውታል። እርሱም ተስፋ ቆርጦ በመጠጥ መደንዘዙን ቀጥሎበታል።
በትግራይ ከተደረገው ውጊያ በፊት ጀምሮ ትግራይን ልክ እንደ አገር በማስመሰል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲታትር የነበረው ቴድሮስ አንዳንዴ ቀጥተኛ ሌሎች ቀናት ደግሞ የኮድ መልዕክቶችን ለጁንታው አባላትና ለመላው ወያኔዎች ሲልክ ነበር። በአሜሪካ የሕግ መወሰኛ ምክርቤት ኢትዮጵያን የሚያሸመቅቅ ሕግ ለማስወጣት ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረገው ሰካራሙ ቴድሮስ የሠራው ሁሉ የዕንቧይ ሲሆንበት አገልጋይነቱ እስከመቼ የሚል ጥያቄ ቢፈጥርበትም ፈርሞ የገባበት ስለሆነ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ለነጮች ፈረስም አህያም መሆኑ የማይቀር ሆኗል።
በትግራይ ጉዳይ ሁሉ ነገር የተዘጋጋበት ቴድሮስ ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ ስለ ትግራይ ቢጮህ ሰሚ አላገኘም። ትግራይን ከዩክሬይን ጋር እንደ አገር በማነጻጸር ዓለም ለዩክሬይን ያደረገውን ለትግራይ አላደረገም እያለ ሲያላዝን ነበር። አርፈህ ተቀመጥ ስለ ትግራይ በኢትዮጵያ ላይ ያደረግነውን ስብሰባ ስንት እንደሆነ ቁጠር የተባለ የሚመስለው ቴድሮስ ከትላንት ወዲያ የለቀቃት ትዊት ይህንኑ አመላካች ሆናለች።
ብቃት ዓልባው ቴድሮስ ዳግም መመረጥ የለበትም-ለተባበሩት መንግሥታት ጥሪ ቀረበ
Biden Must Move Fast to Replace WHO’s Tedros (foreignpolicy.com)
መቀሌ ተቀምጦ እንደ ቀድሞው የመንግሥት እርሻ ወደ ጎን እየተለጠጠ የመጣው ጌታቸውና ወንበዴ ጓደኞቹም የቴድሮስን ዐቅመቢስነት ከበፊቱም የሚያውቁት ነው። ከጥቂት የፌስቡክ ተዋጊዎች በስተቀር ቴድሮስን ብቃት እንዳለው አስፈጻሚ የሚደግፈው ቁጥር አዘቅዝቋል።
ከአምስት ዓመት በኋላ አገር ዐልባ ሆኖ እንደማንኛውም ስደተኛ ወይ ስዊትዘርላንድ ወይም አንዱ አውሮጳ አገር ወይም አሜሪካ አሳይለም (የፖለቲካ ጥገኝነት) ለመጠየቅ እየተዘጋጀ ያለው ቴድሮስ “በቃ ምንስ ተስፋ ባይደረግ?” በማለት ነበር ትዊት ያደረገው። ተስፋ የተሟጠጠው ከቴድሮስ ብቻ ሳይሆን ከትህነግም ይመስላል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply