• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ብቃት ዓልባው ቴድሮስ ዳግም መመረጥ የለበትም-ለተባበሩት መንግሥታት ጥሪ ቀረበ

July 1, 2021 09:13 am by Editor 1 Comment

በአለም ጤና ድርጅት ውስጥ እየጨመረ በመጣው የሥነ ምግባር ጉድለት፤ ማጭበርበርና ጾታዊ ጥቃት የድርጅቱ ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተጠይቋል።

አለም አቀፉ ኢንዲፔንደንት ፋይናንሽያል ኦዲት ባቀረበው የኦዲት ሪፖርት በአለም ጤና ድርጅት ውስጥ የሥነ ምግባር ጉድለት፣ ማጭበርበር፣ ጾታዊ ጥቃትና የሙያ ደረጃዎችን ያልጠበቁ አሰራሮች በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል።

የአለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ የ2020 አመታዊ አፈጻጸምን በተመለከተ የኦዲት ሪፖርት ቀርቧል። በዚህም በተቋሙ እየጨመረ የመጣውን የሥነ ምግባር ጉድለት ማጭበርበርና ጾታዊ ጥቃት ተከትሎ የድርጅቱ ዳይሬክተር ለሁለተኛ ጊዜ እንዳይመረጡ የአለም ኤች አይቪ ኤድስ ሄልዚኬር ፋውንዴሽን ጠይቋል።

ሪፖርቱ በ2020 የበጀት አመት የአለም ጤና ድርጅት ከ332 ሚሊዮን ዶላር በላይ ከአሰራር ውጪ ከአማካሪ ድርጅቶች ጋር ስምምነት ማድረጉን አመላክቷል። በተጨማሪም 2.5 ሚሊዮን ደላር ደግሞ ከደረጃ በታች ለሆኑ ውሎችን በመዋዋል ገንዘቡ ኪሳራ ላይ መዋሉን ነው የተገለጸው።

ፋውንዴሽኑ በድርጅቱ ለታዩት ችግሮች ተጠያቂው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም መሆናቸውን አመልክቶ ለሁለተኛ ዙር የድርጅቱ አመራርነት እንዳይመረጡ በማሳሰብ  ነው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥያቄውን ያቀረበው።

የኦዲት ግኝቶቹ በአለም የጤና ድርጅት ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና በስራዎቹ ላይ ግልፅነት የጎደለው አሰራር መኖሩን እንደሚያመለክቱም አስታውቋል።

“በዚህ ችግር ምክንያት ሰዎች የኮቪድ መከላከያ ክትባቶችን እንዳያገኙ፣ ሚሊዮኖች ለሞት እንዲዳረጉና ከግለሰቦች እጅ በልግስና የሚሰበሰበው ገንዘብ ከጥቅም ውጪ ሆኗል” ሲሉ የኤች አይቪ ኤድስ ሄልዚኬር ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት ማይክል ዌንስተን ተናግረዋል።

የአለም ጤና ድርጅትን አመኔታ ለመመለስና የታዩ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ችግሮች ለመቅረፍ ተመድ አዲስ ፕሬዚዳንት ሊሾም እንደሚገባም ፕሬዚዳንቱ ማስታወቃቸውን ቢዝነስ ዋየር አስነብቧል። (ኢቢሲ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ አንድ ዓመት በፊት የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? በሚል ርዕስ ትህነጉ ቴድሮስ አድሃኖም ከሥልጣኑ መወገድ እንዳለበት የሚጠቁም ዘለግ ያለ ዘገባ አቅርበን ነበር። ሊንኩን በመጫን ዘገባውን ያንብቡ።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News, Politics, Social Tagged With: tedros, WHO

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    July 5, 2021 07:08 am at 7:08 am

    መቼውንም ቢሆን አሁን ባለንበት ዓለም ላይ ታማኝ የዜና አውታር የለም። ሁሉም እንዳሻው የፈጠራና ለፍጆታ የተቀመመ አፍራሽ ዜና ያናፋል። የህትመትም ሆነ የቀጥታ የዜና ስርጭት እንዲሁም የኢንተርኔት ዜናዎች መቶ በመቶ በሚባል ስሌት ዜና ነው ብለው የሚያወሩት በሃገራችን ቡና ላይ ሰው ተሰብስቦ ከሚወራው የሃሜት ወሬ አይሻልም። ጋዜጠኝነት ሞቶ ተቀብሯል። መልካቸው እንጂ ዜናቸው ዜና ሆኖ አያውቅም። አሁን እንሆ በወያኔና በኦሮሞ ጠባብ ብሄርተኞች ውዥንብር ውስጥ ገብታ ለመፈራረስ የምትንገዳገደው የሃበሻው ምድር ገመናዋ ዓለም አቀፋዊ እየሆነ ነው። የዓረቡ አለም ኢትዮጵያዊያን የተባሉትን ሁሉ በግፍ ሃብታቸውን እየቀማ ከሃገሩ በማስወጣት ላይ ይገኛል። ይህ ደግሞ የቆየ በሻቢያና በወያኔ የተለፈፈ ኢትዮጵያን የመጥላት ዘይቤ ፍሬ ነው። አሁን ወያኔ በመቀሌ ማረኳቸው በማለት አሰልፎ ባለህበት ሂድ የሚላቸውን ወታደሮች ሳይ በምንም ሂሳብ ምድሪቱ ወደ ተሻለ ሰላም ትደርሳለች ብሎ መገመት አይቻልም። በመሰረቱ ወገንህን ማረኩ ብለህ ጮቤ መርገጡ የእብደታችን ልክ ጣራ ላይ መውጣቱን ያሳያል። ሰው እንዴት ከስህተቱ አይማርም። አልፎ ተርፎ ወያኔ ያስቀመጠውን የሰላም ድርድር ቅድመ ሁኔታዎች ልብ ብሎ ለተረዳ “እስክንገነጠል እርዱን” ከዚያ በህዋላ አፍንጫችሁን ላሱ ነው። የሚያሳዝን ሁሉን አስለቃሽ ጊዜ ላይ ደርሰናል።
    ይህ የዓለም ጤና ድርጅት ባለስልጣን ከወያኔ የክፋት ስልቻ የወጣ እቡይ ሰው ነው። ኢትዮጵያው ውስጥ በነበረው የተለያዪ ስልጣኖች የፈጸመው ደባ ሰማይ ጠቀስ ነው። አሁንም ያው ባህሪው አለቀው ብሎ አፍቃሪ ቻይናነቱ ቻይና ውስጥ ተመርቶ ለአለም ለተዳረሰው ገዳኝ የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት እሱ የሚመራው መ/ቤት ድክመት እንደሆነ ጠቋሚ መረጃዎች አሉ። እልፍ የደቡብና የአማራ ህዝቦች በቆንጨራ እየተጨፈጨፉ ሲገደሉ ምንም ያላለው ይህ ክፉ ፍጡር ዘሩ ሲነካ ጩኽት ማሰማቱና ለአለም ህዝብ ድረሱልን ማለቱ የዘር ተሰላፊነቱን አጉልቶ ያሳያል። እንደ እነዚህ ያሉት ሙታኖች ተምረዋል ብሎ ማመን ውስልትና ነው። የሰው ልጅ ክብሩ ሰውነቱ እንጂ በዘሩ ወይም በቋንቋ ዙሪያ ብቻ ማላዘኑ አይደለም። ያው የምንሰማውንና የምናነበውን ሁሉ ለማመን ቢከብድም ዶ/ር ተብየው እንደገና ይመረጣል የሚለው ህሳቤ ባህር ውስጥ የሰጠመ እውነት ነው። አይመረጥም። ገና ብዙ ጉድ ይወጣል። እሱ የወያኔ አፈ ቀላጤ እንጂ የዓለም ጤና ጥበቃ ዳሬክተር ሆኖ ሰርቶ አያውቅም። መሞከር ሞክሯል። ግን ልቡ ያለው ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር በበረሃና በከተማ ነው። እንግዲህ አሁን መቀሌ ገቡ አይደል ሂዶ መጠቃለል ነው።
    ሌላው በእጅጉ የሚያሳዝነኝ ነገር ወያኔ መከላከያን አሸንፎ ነው ወይስ በመከላከያ እንደ ተነገረን ለትግራይ ህዝብ እርሻ ታስቦ ነው። የፓለቲካ ውስልትና በቀንም በማታም ነው። ወያኔ ተዋግቶ አላሸነፈም። ግን የአሜሪካና የሌሎች አፍቃሪ ወያኔ የአውሮፓ ሃገሮች ጫና እንዲሁም የትግራይ ህዝብ ከህዋላም ከፊት ከትራፊ ወያኔዎች ጋር በማበር ባደረጉት ግድያ/አፈና/ማስፈራራት ግፊት ተገዶ ነው ሰራዊቱ የወጣው። የኋላ ደጀን የሌለው ወታደር በጠላት ሰራዊት እንደተከበበ ሰራዊት ነው። ስለዚህ ወያኔም አላሸነፈም። መከላከያም ወዶ አይደለም የወጣው ተገዶ እንጂ። ስንቁና የሚጠጣው ውሃ በሚያቀርቡለት የሚመረዝበት ሰራዊት የኢትዮጵያ ሰራዊት ብቻ ነው። አሁን ወያኔ በመቀሌ እያነቀ የሚገላቸው የትግራይና የሌላ አካባቢ ተወላጆች ቁጥር እየበዛ መሄድ የአሜሪካን መንግስት ያሳሰበው ይመስላል። በትግራይ ለሚኖሩ ዜጎቹ ተሰባሰቡ ብሏል። ለእኛ ከተነገረን የተለዬ ሊመጣ ያለ ሌላ መከራ ይኖር ይሆን? ግብጽና ሱዳን ጦርነት ከወያኔ ጋራ አብረው ሊከፍቱ ይሆን? ትላንት የእርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ያለምንም ገደብ ይግቡ እያሉ ይለፈልፉ የነበሩት ነጮች አሁን ወያኔ መቀሌ ሲገባ ለህዝባቸው ለምን ተጨነቁ?
    ጉዳዬ ጠሊቅ ነው። ሊቢያን፤ ኢራቅን፤ የመንን፤ ሶሪያን፤ አፍጋንስታንን እንዳፈራረሱት ሁሉ አሁን የኢትዮጵያ ወረፋ ይመስላል። ይህም ኦነግና መራራ ጉዲና በቅርቡ ከሚለፉት የመገንጠል ጥይቄ ጋር አብሮ ይሄዳል። የማርሻል ቲቶን ሃገር ዪጎዝላቢያን ወደ ስድስት ሃገር የከፋፈላት የአሜሪካው ሴራ አሁን ኢትዮጵያ ላይ አተኩሯል። የሚያተርፉት ግን የቱ ላይ እንደሆነ አይታየኝም። በሃበሻው ምድር ዛሬ ከምናየው የላቀ ሰቆቃ ግን ይከተላል። ተ.መ.ድ በትግራይ ጉዳይ ተደጋጋሚ የጎንዪሽና የይፋ ስብሰባ ሲያረግ፤ የአሜሪካ ም/ቤት በትግራይ ጉዳይ ላይ ሲመክር ለእኔ የታየኝ አንድ ነገር ብቻ ነው። የከፋ ቀን እንደተዘጋጀልን። እንደ የመንና ሶማሊያ መሆናችን አይቀሬ ይመስላል። በዚህ ላይ የአረብ ራቢጣ ተሰብስቦ የግብጽን አቋም መደገፉና ኢትዮጵያዊያንን በተለይም ሳውዲ አረቢያ ማባረሯ መከራችን ለማባዛት ታስቦና ተሰልቶ የተፈጸመ ድርጊት ነው። ሱዳን ህዝቦቿ ዳቦና ነዳጅ ሌላ የፍጆታ እቃዎች አቅርቦት ጠፋ እያሉ ዜጎቿ ሰላማዊ ሰልፍ እያረጉ የኢትዮጵያን ድንበር መያዟ ከአሜሪካኖች በተሰጣት ትዕዛዝ ነው። ትርፉ ለግብጽ የሚሞተው ሃበሻና ሱዳን! ራሳቸው ዓለም አቀፋዊ አሸባሪዎች ሆነው ሌላውን አሸባሪ የሚሉ የፓለቲካ እብዶች እልፍ ናቸው። የኢራቁ ሳዳምን ሃገሩን አፍርሰው በገመድ ያንጠለጠሉት እነዚህ እኩዬች የሊቢያውን ሞሃመድ ጋዳፊን የስውር የመሳሪያ ማምረቻህን አስረክብ ብለውት ለአሜሪካ መንግስት ቢያስረክብም ከሰማይና ከመሬት በተወጣጣ ጦር ሃገሩን ከመናድ እሱን ከመግደል አልተመለሱም። አሁን ሊቢያ ጠበንጃ አንጋች የሚራወጥባት ፍርስርሷ የወጣ ምድር ሆናለች። ይህ የማይታየው አፍሪቃዊና ጥቁር ህዝብ ደንቆሮና እውነቱን ማየት የማይፈልግ የሰው እንስሳ ብቻ ነው፡፡
    በመጨረሻም የጠ/ሚር አብይ መንግስት የታሰሩ ወያኔዎችን ወደ መቀሌ በመላክ ሌሎችንም በማሰናበት ወያኔ የፈለገውን የመገንጠል ዘይቤ እውን እንዲያደርግ መተው ነው። ሌላው ሁሉ የሰላም ጥሪ የወያኔ ቅድመ ሁኔታዎች የልጆች ጫወታ ነው። ጠ/ሚሩ ካለፈው ስህተቱ መማር አለበት። የብር ለውጡ ሲደረግ ብሩ ከተራገፈላቸው በህዋላ ነው ጦርነት የከፈቱት። ወያኔ የሚታመን ድርጅት አይደለም። ሰላምን አያውቋትምና ! የዚሁ ቡድን አንድ አካል የዛሬው የዓለም የጤና ድርጅት ዳሬክተርም እጅ በደም የተነከረ ዲያብሎስ ነው። በምንም ሂሳብ ዳግመኛ ይመረጣል የሚል እምነት የለኝም። ሁሉንም ቆይተን እንይ! በቃኝ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule