የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም የተለያዩ ነጥቦችን አንስተዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መነሳቱ ለሰላም ምክክሩ ገንቢ ሚና እንዳለው በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
ህወሃት ጸብ በመጫር የእርዳታ ስራውን እያስተጓጎለ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ከተመድ ጋር በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው የገለጹ ሲሆን በተግባር እያሳየ መሆኑን የተመድ ምክትል ጸሀፊ አሚና መሀመድ መናገራቸውንም አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ከታላቁ ህዳሴ ግድብና ከድንበር ጋር በተያያዘ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ውይይት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
የመተማ ገላባት መንገድ እንደቀደሙ ሁሉ ለዜጎች እንቅስቃሴ ክፍት እንዲሆን ከሱዳን መንግሥት ጋር ንግግር መደረጉንም ማንሳታቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል፡፡
የአማርኛ ቋንቋ የአፍሪካ ኅብረት የስራ ቋንቋ እንዲሆን እንቅስቃሴ ለመጀመር መታሰቡንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ ለማድረግ የተወጠኑ ብዙ ውጥኖች ነበሩ። አሁን በተለይ ኢትዮጵያ እንደገና የፓን አፍሪካ ንቅናቄ መሪ ሆና በገናናነት ብቅ ባለችበት ወቅት አፍሪካውያን የሚኮሩበትና የሚመኩበት የራሳቸው የሆነ ቋንቋ እንዳላቸው ማሳየት የምትችል ብቸኛ አገር ኢትዮጵያ ነች።
አምባሳደሩ እንዳሉት በመንግሥት ደረጃ ይህ እንቅስቃሴ መጀመሩ እነ መለስ እና የትግሬ ወንበዴዎች ለማስፈን ያቀዱትን ውጥን ድባቅ የሚመታና ኢትዮጵያ ውስጥ ለተንሰራፋው መረን የለቀቀ ወገንተኝነትና ዘረኝነት ጥሩ ፈዋሽ መድኃኒት ይሆናል ተብሎ ይገመታል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply