በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ጭልጋ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ፈለቀ የ55 ዓመት ጎልማሳ ሲሆኑ በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚነሱት ግጭቶች ተረጋግተው እንዳይኖሩ ሲያደርጓቸው እንደቆዩ ይገልጻሉ። በሌሎች ጊዜያት ከተነሱት ግጭቶች በላይ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 2013 ዓ.ም የተነሳው ግጭት አቶ ሀብታሙን ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። ሚያዚያ 2013 ዓ.ም ግጭት ተነስቶ ንብረት ሲወድምና የሰው ህይወት ሲጠፋ አቶ ሀብታሙ አካባቢውን ለቀው ለመሄድ መነሳታቸውን ይናገራሉ። አቶ ሀብታሙ የአማራ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ ቤት ንብረታቸውን ለቅማንት ብሔረሰብ ተወላጁ ጓደኛቸው አስረክበው ወደ ጎንደር ከተማ እንደመጡ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል። ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበረው ግጭት በማንነት ምክንያት ሆኖ ሳለ የአማራ ብሔር ተወላጅ … [Read more...] about “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ
News
ዜና
ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን
ትግራይ የሸመቀው የወንበዴና አሸባሪ ቡድን ረቡዕ ስብሰባ አካሄድኩ ብሎ በሚዘውራቸው ሚዲያ ዘግቦ ነበር። በስብሰባው ላይ የ4 ወር የሥራ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን ደብረጽዮን ትግራይን ራስገዝ አገር እናደርጋለን ብሏል። “ተልዕኳችን” ሲል አገርን የማፍረስ ዕቅዱን የተናገረው ደብረጽዮን ዓላማችን ትግራይን አገር ማድረግ ነው ብሏል። ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሰበሰባቸው ደካሞች እጅግ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ሲናገር “የምንገኝበት ምዕራፍ በውይይት እና በጦርነት ሊቋጭ የሚችልበት ሁኔታ የሰፋ ነው” ብሏል። ደብረጽዮን አገር አደርጋታለሁ በሚላት ትግራይ እጅግ በርካታው ሕዝብ አጥንትን ዘልቆ በሚገባ ችጋር ውስጥ የተሸማቀቀ ሲሆን ሠርቶ የሚያበላው ልጆቹን ለጦርነት ገብሯል፤ ለዐቅመ ሔዋን ያልደረሱ ሴቶች ልጆቹን ደግሞ ለሴተኛ አዳሪነት እየሸጠ ነው። ደብረጽዮንና ወንበዴ ጓደኞቹ ይቺን ትግራይ … [Read more...] about ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን
“ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች”
በሙያቸው ብቃት እና በስነ ምግባራቸው በሠራዊታችንም ሆነ በሰቪል ማህበረሰቡ ዘንድ ተመስግነው የማያልፍ ታሪክን ሰርተው ህዝብና ሀገርን አኩርተዋል። በዋሉበት አውድ ሁሉ በፅናትና በጀግንነት ከጦር ሠራዊቱ ጋር ፊት ለፊት በመሰለፍ ሠራዊቱን አክመዋል ባስ ሲል ደግሞ ጠመንጃቸውን አንስተው ጠላትን እያፍረከረኩ ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ድርብ ኃላፊነት በጀግንነት ተወጥተዋል። ሰራዊቱ ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር በሚል ቁልፍ እሴት በተግባር ተቃኝቶ በህዝብና በሀገር የመጣን ጠላት ሲፋለም መተከያ የሌላትን ህይወት ለመታደግ እና ከደረሠበት ጉዳት ድኖ ወደ ግንባር እንዲመለስ በማድረግ ጀብዱ ፈፅመዋል ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ዶክተሮች። ሌ/ኮ ዶክተር ጌታሁን የሻነው እና ሻ/ል ዶክተር ውበት ደምሴ ይባላሉ። ሻ/ል ዶክተር ውበት ደምሴ የምዕራብ ዕዝ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል ሜዲካል … [Read more...] about “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች”
ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ
በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ ለአሸባሪው ሕወሀት ቡድን ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር መያዙን የአስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። "ከአሸባሪው ሕወሀት ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 20 ሰርጎ ገቦች” በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል። የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ አቶ ሸጌ መንግስቴ ከግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በተደረገ የተቀናጀ ጥረትም ለሕወሀት የሽብር ቡድን ሊደርስ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር መያዙን ገልጸዋል። ገንዘቡን ለሽብር ቡድኑ ሊያደርሱ የነበሩ 20 ተጠርጣሪዎች በጸጥታ ኀይሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን አመልክተዋል። በሌላ በኩል “ከአሸባሪው ሕወሓት ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 20 ሰርጎ ገቦች” በከተማ አስተዳደሩ በቁጥጥር ስር … [Read more...] about ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ
በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ
በቀጣይ በጀት ዓመት ደግሞ 20 ቢሊዮን ብር ተመድቧል የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር (300 ሚሊዮን ዶላር) ድጋፍ ለማድረግ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት ተፈራረሙ። ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የኤርትራ ዳይሬክተር ኦስማኔ ዶኔ ጋር ተፈራርመዋል። የድጋፍ ስምምነቱ በጦርነቱ በአማራ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችና ማህበረሰብ ለመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ስራዎችን በአስቸኳይ ለመደግፍ ያለመ ነው። ድጋፉ በተመረጡ የግጭት ተጎጂ ወረዳዎች የጤና፣ የትምህርትና የውሃ መሰረት ልማት መዘርጋት ብሎም ለፆታዊ ጥቃት የተጋለጡ ሴቶችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም ይውላል ተብሏል። የፌዴራል መንግስት … [Read more...] about በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ
በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ
የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ባደረጉት ክትትል በአንድ የእንጨት ስራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ከ3 ሺህ በላይ ጥይት ከእነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ሁለቱ ተቋማት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አዲሱ ገበያ ቀለበት መንገድ አካባቢ በሚገኝ አንድ የእንጨት ስራ ድርጅት ውስጥ ተደብቆ የተቀመጠ ጥይት ስለመኖሩ ከህዝብ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ሲከታተሉ ቆይተው፥ ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም በህግ አግባብ በድርጅቱ ውስጥ ባደረጉት ብርበራ በ4 ማዳበሪያ ተጠቅልሎ በድብቅ የተቀመጠ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተይዟል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ህብረተሰቡ ህገ … [Read more...] about በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ
በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ
አንድ የውጪ ሀገር ዜግነት ባለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ግለሰቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 24 ኮንዶሚኒየም ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ 3 ወለል ፎቅ ተከራይቶ የሚኖር መሆኑን ገልጿል። ተጠርጣሪው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎችን እየተቀበለ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ሲፈጽም እንደነበር ከህብረተሰቡ ጥቆማ ማግኘቱንም ነው የገለጸው። ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ፤ጥቆማውን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተቀናጅተው ባደረጉት ክትትል ግንቦት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በግለሰቡ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ በመኝታ ክፍል ውስጥ የተገኘ 5 ሺህ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ
አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል
50 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርበት የአማራ ክልል ዓመታዊ በጀት ሰማኒያ ቢሊዮን ነው በትግራይ ክልል ለአምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። እስካሁን ወደ ትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ይዘው ከሄዱ አንድ ሺህ 626 ከባድ ተሽከርካሪዎች የተመለሱት ተሽከርካሪዎች 596 ብቻ እንደሆኑ አመልክተዋል። ክልሉን የሚያስተዳድረው ትህነግ በበኩሉ የሚገባው እርዳታ ከሚፈለገው አንጻር በቂ እንዳልሆነ ገልጿል። ዕርዳታ ጭነው የሚገቡትን ከባድ ተሽከረካሪዎች ለምን እንደሚያግታቸው ምክንያት አላቀረበም። የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቀው፤ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑና መድኃኒት እንዲሁም የትራንስፖርትና የጥሬ … [Read more...] about አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል
ሰብዓዊ እርዳታ ወደ መቀሌ መግባት መቀጠሉ ተገለጸ
የዓለም ምግብ ፕሮግራም (ተመድ) የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን አስታወቀ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፡- በትግራይ እና አፋር ክልሎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚሰራጨው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት የሰብዓዊ እርዳታ የያዙ ተጨማሪ 85 የጭነት ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን ነው የገለጸው፡፡ ከዚህ ባለፈም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 130 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እያቀኑ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይህም በተያዘነው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ መቀሌ ከተጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳታ በመጠን ትልቁ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በተመሳሳይ በሰሜን አፋር አካባቢዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች በሚቀጥሉት ቀናት በዓለም የምግብ ፕሮግም የተዘጋጀው … [Read more...] about ሰብዓዊ እርዳታ ወደ መቀሌ መግባት መቀጠሉ ተገለጸ
የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ኢታማጆር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርኃኑ ጁላ ከዑጋንዳ የመከላከያ ሚኒስትር ጋር በወቅታዊ የሁለቱ አገሮች ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ ውይይታቸው የሁለቱ አገሮች የመከላከያ ዘርፍ ስምምነት ያለበት ደረጃ የተዳሰሰ ሲሆን በቀጣይ ስምምነቱን ለማደስ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ ይህም ሥምምነቱን የማደስ ሥራ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንዲፈፀም መመሪያ ተሰጥተዋል ተብሏል፡፡ ሁለቱ ኃላፊዎች በዋናነት ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘገብ ስለነበረውና አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የሥልጠናና ሌሎች ድጋፎችን በአሜሪካ፣በግብጽና በደቡብ ሱዳን በመታገዝ በዑጋንዳ አማካኝነት እገዛ እያገኘ ነው የሚለውን ወሬ የዑጋንዳ መከላከያ ሚኒስትር ፈፅሞ ከዕውነት የራቀ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሀገራቸው ኢትዮጵያን የአፍሪካ እናት … [Read more...] about የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ










