• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች”

May 26, 2022 08:19 am by Editor 1 Comment

በሙያቸው ብቃት እና በስነ ምግባራቸው በሠራዊታችንም ሆነ በሰቪል ማህበረሰቡ ዘንድ ተመስግነው የማያልፍ ታሪክን ሰርተው ህዝብና ሀገርን አኩርተዋል።

በዋሉበት አውድ ሁሉ በፅናትና በጀግንነት ከጦር ሠራዊቱ ጋር ፊት ለፊት በመሰለፍ ሠራዊቱን አክመዋል ባስ ሲል ደግሞ ጠመንጃቸውን አንስተው ጠላትን እያፍረከረኩ ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ድርብ ኃላፊነት በጀግንነት ተወጥተዋል።

ሰራዊቱ ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር በሚል ቁልፍ እሴት በተግባር ተቃኝቶ በህዝብና በሀገር የመጣን ጠላት ሲፋለም መተከያ የሌላትን ህይወት ለመታደግ እና ከደረሠበት ጉዳት ድኖ ወደ ግንባር እንዲመለስ በማድረግ ጀብዱ ፈፅመዋል ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ዶክተሮች።

ሌ/ኮ ዶክተር ጌታሁን የሻነው እና ሻ/ል ዶክተር ውበት ደምሴ ይባላሉ።

ሻ/ል ዶክተር ውበት ደምሴ የምዕራብ ዕዝ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ናቸው። ከህግ ማስከበር እስከ ዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት ድረስ ሠራዊቱን እና በአካባቢው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዴት አገልግሎት ሲሰጡ እንደነበረ ይናገራሉ።

አሸባሪው የህውሃት ቡድን በሰሜን ዕዝ የሠራዊት አባላት ላይ ጥቃት ባደረሰ ማግስት የምዕራብ ዕዝ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል አባላት ከወትሮ በተለየ መልኩ ዘመቻውን ለመደገፍ የሚያስችል አደረጃጀት አድርገን ወደ ግንባር አቅንተናል።

ሠራዊታችን እለት ከእለት ድልን እያስመዘገበ እና የጠላትን ሃይል አከርካሪውን እየሰባበረ ወደ ፊት በሚገሰግስበት ጊዜም ተንቀሳቃሽ ሆስፒታሉ በፍጥነት ከሰራዊቱ ጋር በመንቀሳቀስ የሚጠበቅበትን የጦር ሜዳ አገልግሎት ሠጥቷል።

ተዋጊው ሃይላችን ከተማዎችን እየተቆጣጠረ ወደ ፊት ሲገሰግስ በከተማዎቹ ይኖሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ በማድረግ ህይወታቸውን መታደግ ችለናል። በዚህም ከራስ በፊት ለህዝብ እና ለሀገር የሚለውን ዕሴታችን በተግባር ማሳየት ችለናል።

በማይጠብሪ ግንባር እና በወሎ ግንባር ስንገባም እንደተለመደው ለሠራዊቱ የህክምና አገልግሎት በመስጠት የማድረግ አቅሙን፣ ሞራሉ እና ወታደራዊ ስነ ልቦናው እንዲጠበቅ በማድረግ ሠራዊቱ ወደ ግንባር ተመልሶ ጠላትን እንዲደመስስ ማድረግ ችለናል።

የተለያዩ ከመንግስትና ከሲቪል የህክምና ተቋማት የመጡ ባለሙያዎችም ከእኛ ጋር በግንባር በመሰለፍ ሠራዊቱን በሙያቸው አገልግለዋል። ከልጆቹ እና ከእለት ጉርሱ ቀንሶ ለእኛ ያካፈለን ደጀን ለሆነን ህዝባችን እና በሙያቸው ላገለገሉን የጤና ሙያተኞች ምስጋና አቅርቧል።

ሻ/ል ዶክተር ውበት ደምሴ በምዕራብ ዕዝ በተዘጋጀው የሜዳይ ሽልማት ላይ የሁለተኛ ደረጃ ሜዳይ ተሸላሚ በመሆኑ ደስታኛ ነው። ሽልማቱ ቀጣይ ለሚጠብቀው ግዳጅ ሞራል እና ተነሳሽነትን እንደፈጠረለትም ገልጿል።

ሌላኛው የምዕራብ ዕዝ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል አባል ሌ/ኮ ዶክተር ጌታሁን የሻነው፥ ውትድርና ብዙ የሙያ መስኮች የሚገኙበት እና በሀገራችን ህዝቦች ዘንድ ደግሞ ተወዳጅ የሆነ የሙያ ዘርፍ መሆኑን በመግለፅ ተቋሙ ባስተማረው እና ባበቃው የዶክተርነት ሙያ አሸባሪው የህውሃት ቡድን በሰሜን ዕዝ የሠራዊት አባላት ላይ ጥቃት ባደረሰበት ጊዜ ከባልደረቦቼ ጋር በመሆን ሠራዊታችንን በሙያችን በማገልገል የድል ባለቤት እንዲሆን የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ችለናል።

ጀግናው ሠራዊታችን የሚያደርገውን የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ በመከታተል እና ምሽግ ድረስ በመጓዝ ጤንነቱ የተጠበቀ እና የማድረግ አቅሙ የላቀ እንዲሆን የምዕራብ ዕዝ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል አሁንም ያልተቆራረጠ ክትትል እያደረገ ይገኛል።

ዕዛችን በተንቀሳቀሰበት የግዳጅ ቀጣናዎች ሁሉ ሠራዊቱ ጉዳት ደርሶበታ ሲመጣ ተኝቶ እንዲታከም በማድረግ እና በፍጥነት አገግሞ ወደ ግዳጁ እንዲመለስ ያደረጉ የግል እና የመንግስት ሆስፒታሎችን ከልብ ማመስገን እወዳለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ሌ/ኮ ዶክተር ጌታሁን የሻነው በነበራቸው የላቀ ግዳጅ አፈፃፀም ከሻለቃ ማዕረግ ወደ ሌ/ኮ ማዕረግ ከፍ እንዲሉ ተደርጓል።

ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ዶክተሮች ቀናቶችን በተጋድሎና በጀብዶቻቸው እያደመቁ በፈታኝ እና ውስብስብ ግዳጆች ሳይበገሩ በሌላ ተልዕኮ ሌላ ገድል ለመፈፀም እራሳቸውን አዘጋጅተዋል። (ዘገባና ፎቶ ፍፁም ከተማ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: endf, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Comments

  1. gi says

    May 26, 2022 12:35 pm at 12:35 pm

    ሁሉም በተሰጠው ሙያና ሃላፊነት በፅናት ከሰራ ብሔራዊ ግዴታውን ስለተወጣ ከጀግኖችና በመልካም ታሪክ ይመዘገባል።
    ከሌቦች ኮሌጅ ተመርቀው እንደ አይጥ እየተዟዟሩ የሕዝብ ሓብት ሲዘርፉ የነበሩ ግን ሌቦች በሚል ታሪክ ስማቸው ይመዘገባል። ኢትዮጵያ የተለያዩ ልጆች ወልዳለች በጀግንነት የሚሞቱላት፣ በንቃት የሚጠብቋትና የሚንከባከብዋት፣በደር ቁጭ ብለው የሚመለከትዋትና ኣሰልፈው ለጠላት የሚሰጥዋት ናቸው።
    አገር ወይሞ ሞት የተባለበት ዘመን ነበር። ዛሬ ግን ብር ወይም ሞት ሆኖኣል።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule