በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ጭልጋ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ፈለቀ የ55 ዓመት ጎልማሳ ሲሆኑ በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚነሱት ግጭቶች ተረጋግተው እንዳይኖሩ ሲያደርጓቸው እንደቆዩ ይገልጻሉ። በሌሎች ጊዜያት ከተነሱት ግጭቶች በላይ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 2013 ዓ.ም የተነሳው ግጭት አቶ ሀብታሙን ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። ሚያዚያ 2013 ዓ.ም ግጭት ተነስቶ ንብረት ሲወድምና የሰው ህይወት ሲጠፋ አቶ ሀብታሙ አካባቢውን ለቀው ለመሄድ መነሳታቸውን ይናገራሉ። አቶ ሀብታሙ የአማራ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ ቤት ንብረታቸውን ለቅማንት ብሔረሰብ ተወላጁ ጓደኛቸው አስረክበው ወደ ጎንደር ከተማ እንደመጡ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል። ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበረው ግጭት በማንነት ምክንያት ሆኖ ሳለ የአማራ ብሔር ተወላጅ … [Read more...] about “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ