• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል

May 16, 2022 08:30 am by Editor Leave a Comment

50 ሚሊዮን ሕዝብ የሚኖርበት የአማራ ክልል ዓመታዊ በጀት ሰማኒያ ቢሊዮን ነው

በትግራይ ክልል ለአምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። እስካሁን ወደ ትግራይ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ይዘው ከሄዱ አንድ ሺህ 626 ከባድ ተሽከርካሪዎች የተመለሱት ተሽከርካሪዎች 596 ብቻ እንደሆኑ አመልክተዋል። ክልሉን የሚያስተዳድረው ትህነግ በበኩሉ የሚገባው እርዳታ ከሚፈለገው አንጻር በቂ እንዳልሆነ ገልጿል። ዕርዳታ ጭነው የሚገቡትን ከባድ ተሽከረካሪዎች ለምን እንደሚያግታቸው ምክንያት አላቀረበም።

የኢትዮጵያ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቀው፤ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑና መድኃኒት እንዲሁም የትራንስፖርትና የጥሬ ገንዘብ ዝውውርን ጨምሮ ለአምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን የትግራይ ሕዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተሰጠ መሆኑንን ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በተለያዩ ድርጅቶች አማካኝነት እንዲደርሳቸው በማድረግ በኩል ሥራው የተሠራና ተፈቅዶ እንዲሄድ እየተደረገ ያለው በኢትዮጵያ መንግሥት እንደሆነ አቶ ደበበ ገልጸዋል። በዚህም በአሁን ወቅት በክልሉ ድጋፍ ለሚሹ አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።

ሰብዓዊ ድጋፉ በርካታ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን ያካተተ እንደሆነ፤ በዚህም በርካታ የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድጋፍ ላይ የተሰለፉ አጋር አካላት ምግብን ጨምሮ መድኃኒትና ሌሎች ድጋፎችን ለክልሉ ዜጎች በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

አቶ ደበበ እንዳሉት፤ እስከ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በጥሬ ገንዘብ ለአስተዳደርና ለፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚሆን አንድ ነጥብ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ክልሉ እንዲላክ ተደርጓል። ይሄንንም የሚያስፈጽሙት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ አጋር ድርጅቶች ናቸው።

202 ሺህ 79 ኪሎ ግራም የተለያዩ መድኃኒቶች በተለያዩ አጋር ድርጅቶች ሰብዓዊ ድጋፍ በአየር ትራንስፖርት ወደ ክልሉ መጓጓዙንም አቶ ደበበ ገልጸዋል።

ከዚህም ባሻገር በተለያዩ ድርጅቶች የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት 406ሺህ 403 ኪሎ ግራም የተመጣጠነ ምግብ እና 91ሺህ 558 ኪሎ ግራም ምግብ ነክ ያልሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶች በአየር ትራንስፖርት እንደተጓጓዘ ተናግረዋል።

እንደ አቶ ደበበ ገለጻ፤ በሚያዚያ ወር 2014 ዓ.ም 401 ሺህ 29 ሊትር ነዳጅም ተጓጉዟል። እስካሁን ይህንን በመጓጓዝ ደረጃ በየብስ ላይ መቀሌ የደረሱ ከባድ ተሽከርካሪዎች አንድ ሺህ 626 ናቸው። ከዚህ ውስጥ የተመለሱት ተሽከርካሪዎች 596 ብቻ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

አቶ ደበበ፤ እስካሁን ለሰብዓዊ አገልግሎት 221 የአየር በረራ መከናወኑን ጠቅሰው፤ ሌሎች ክልሎች እየተላከ ካለው በበለጠ 83 ድርጅቶች በትግራይ ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እየተረባረቡ እንደሚገኙ ነው የገለጹት።

ከሐምሌ 2013 ጀምሮ 50 ሺህ 921 ሜትሪክ ቶን ምግብ፤ እንደ ውሃ፣ መጠለያ፣ ቁሳቁስ፣ ንጽህና መጠበቂያ የመሳሰሉ ዘጠኝ ሺህ 563 ሜትሪክ ቶን ተጨማሪ ቁሳቁሶች በተለያዩ አጋር ድርጅቶች ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት አማካኝነት በየብስ ትራንስፖርት ለክልሉ ዜጎች መጓጓዙን አስታውቀዋል።

ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ የመናገርና አጠቃላይ መረጃ መስጠት የሚቻለው በኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ ነው። በተለይ በሚዲያዎች በኩል ከግለሰብ ጀምሮ የሚሰሙ ነገሮችን ተመርኩዞ መናገር አስቸጋሪ ነገር ነው ሲሉም አቶ ደበበ ተናግረዋል።

ወደ ትግራይ ክልል እየገባ ያለው የዕርዳታ አቅርቦት ከሚያስፈልገው አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ሞትና ረሃብ እየተስፋፋ እንደሚገኝ የትግራይ ክልል የግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ መሆናቸውን የገለጹት ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ፣ በቅርቡ ለቪኦኤ ተናግረዋል፡፡

ወደ ክልሉ ለሚደረገው የዕርዳታ አቅርቦት ማነስ የትግራይ ክልል አመራሮች እና አንዳንድ የረድኤት ድርጅቶች መንግሥትን ተጠያቂ አድርገዋል። ሃላፊው መንግስት በቁጥር፣ በቀን፣ በመለክያና በስም ለይቶ አንድ በአንድ ወደ ትግራይ የገባውን እርዳታ፣ እንዲሁም 76 ቢልዮን ብር አስመልክቶ ቪኦኤ ቃል በቃል ጥያቄ አላቀረበም። የቪኦኤ የትግራይ ዘጋቢ በደፈናው ሃላፊው መንግስትን እንደወነጀሉ ነው ያስታወቀው። መንግስት ውንጀላውን እንደይቀበለውም አመልክቷል።

76 ቢሊዮን ብርና እርዳታ የሚላክለት የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ ትህነግ በስሌት ደረጃ በአገሪቱ ካሉ ክልሎች በላይ ሃብት እየተላከለት መሆኑንን መረጃው ያሳያል። እስከ ግንቦት አንድ ቀን 2014 ድረስ ለማስፈጸሚያ ወደ ትግራይ የተላከው 76 ቢልዮን ብር ከአማራ ክልል ዓመታዊ በጀት ጋር ሲነጻጸር በአራት ቢሊዮን ብቻ ነው የሚያንሰው። 50 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያለው አማራ ክልል በጀቱ ሰማኒያ ቢሊዮን መሆኑ ይታወቃል። በጀቱ ተጨማሪውን ሳያካትት ሲሆን ለማሳያነት ለመጠቀም እንጂ ሌላ ዓላማ የለውም። (ኢትዮ 12)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, News, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule