የዓለም ምግብ ፕሮግራም (ተመድ) የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን አስታወቀ።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፡- በትግራይ እና አፋር ክልሎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚሰራጨው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት የሰብዓዊ እርዳታ የያዙ ተጨማሪ 85 የጭነት ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን ነው የገለጸው፡፡
ከዚህ ባለፈም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 130 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እያቀኑ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ይህም በተያዘነው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ መቀሌ ከተጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳታ በመጠን ትልቁ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ በሰሜን አፋር አካባቢዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች በሚቀጥሉት ቀናት በዓለም የምግብ ፕሮግም የተዘጋጀው የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚሰራጭ ተጠቁሟል፡፡ (አዲስ ሚዲያ)
ትህነግ የዕርዳታ እህልን ወደ ጦር መሣሪያነት በመቀየር የትግራይን ሕዝብ ሲያሰቃይና ሲገድል የነበረ የወንበዴ መሆኑ በኩራት የሚዘፍንበት ጉዳይ ነው። ይኼኛውም ለተረጂው መድረሱ ማንም ማረጋገጥ አይችልም።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply