
አንድ የውጪ ሀገር ዜግነት ባለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
ግለሰቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 24 ኮንዶሚኒየም ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ 3 ወለል ፎቅ ተከራይቶ የሚኖር መሆኑን ገልጿል።
ተጠርጣሪው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎችን እየተቀበለ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ሲፈጽም እንደነበር ከህብረተሰቡ ጥቆማ ማግኘቱንም ነው የገለጸው።
ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ፤ጥቆማውን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተቀናጅተው ባደረጉት ክትትል ግንቦት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በግለሰቡ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ በመኝታ ክፍል ውስጥ የተገኘ 5 ሺህ 335 የአሜሪካ ዶላር፣ 380 ዩሮ፣ 1 ሺህ 435 የቻይና የን እና ሌሎች የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦችን ጨምሮ 71 ሺህ 635 የኢትዮጵያ ብር ተይዟል፡፡ (አዲስ ሚዲያ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply