በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን መከፋፈልና ችግር በሐሃዋሪያት መንገድ መፍትሄ እንዲፈለግለት ወደ ስምምነት መደረሱ ተሰማ። ይህ የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሲኖዶስ አመራሮች ጋር መወያየት መጀመራቸውን ተከትሎ ነው። የቤተክርስቲያኗ አባቶች ዛሬ ረፋዱ ላይ ከመንግሥት ከፍተኛ አመራሮችና ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በቤተመንግሥት እየመከሩ ነው። ለስብሰባው ቅርብ የሆኑ ክፍሎችን ጠቅሰው ለአዲስ አበባ ተባባሪ ዘጋቢያችን ፍንጭ የሰጡ እንዳሉት፣ ችግሩን ከጣልቃ ገቦች አሳብ ነጥሎ በሐዋሪያት አግባብ ለመፍታት የመስማማት ፍንጭ አለ። በቡራኬ የተጀመረው ውይይት ላይ ሽምግልናውን ከሚመሩት ወገኖችና ከአባቶቹ መካከል አሳብ ሲሰጡ ያለቀሱ እንዳሉና ግልጽ ውይይት እየተደረገ መሆኑን፣ ዕረፍት ላይ ከመጀመሪያው የተለየ ስሜት መታየቱንም እነዚሁ ክፍሎች አስታውቀዋል። … [Read more...] about ውዝግቡን በሐዋሪያት መንገድ ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል
operation dismantle tplf
የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም – መልዕክት “ለመንፈሳዊው ቄሮ” መሪ ዘመድኩን በቀለ!
ጃዋር መሐመድ “የኦሮሞ ፕሮቴስት” ብሎ የጀመረ ሰሞን ብዙ የፌስቡክ ተከታታይ አልነበረውም። ወዲያው አገር ቤት ከኦህዴድ ጋር በነበረው ግንኙነት የተቃውሞ ሰልፎችንና የፖሊስ ግፎችን የሚያሳዩ ፎቶዎችን መለጠፍ ሲጀምር የተከታታዩ መብዛት ጀመረ።ዝግጅቱም፣ ትምህርቱም፣ ሥራውም፣ በሚዲያ ዙሪያ ስለነበር ሚዲያን እንዴት እንደሚቆጣጠርና የሕዝቡን ቀልብ እንዴት እንደሚስብ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር። በመሆኑም ከማኅበራዊ ሚዲያ እስከ ዋንኛ (mainstream) ያለውን በቀላሉ ተቆጣጠረው። ለመረጃ፣ ለዘገባ፣ ለዜና፣ … እንደ ምንጭ የሚጠቀስ ሆነ። ትልልቅ የሚባሉት የውጪዎቹ የሚዲያ አውታሮች እሱን ሳያናግሩ ዜና መሥራት አልታያቸው አላቸው። በፍጥነት ወጣ፣ ተመነደገ፣ ከፍ አለ! የዚያኑ ልክ እሱም እያበጠ መጣ። ዕብጠቱ ገና አፍላ በነበረበት ጊዜ ባደባባይ የዕብሪት ንግግር ለጠፈ። አሁን በማላስታውሰው … [Read more...] about የሚከተልህ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም – መልዕክት “ለመንፈሳዊው ቄሮ” መሪ ዘመድኩን በቀለ!
በሰማዕትነት ጥሪ ቤተመንግሥቱን ባቋራጭ መቆጣጠር
ይህ ለውጥ እውን ከሆነ በኋላ ሕዝብን ስሜታዊ የሚያደረጉ ተግባራት ናቸው በቅስቀሳ መልኩ የሚሰራጩት። ሰው ይገደልና ይሰቀላል። ተሰቅሎ ሲወገር ፊልም ይቀረጻል። ወዲያው ለሕዝብ ላይቭ ይለቀቃል። “እኔ ከእገሌ ብሔር አልተወለድኩም በል” እየተባለ ሰው በማንነቱ ሲገደል የሚያሳይ ፊልም በቅጽበት አየር ላይ እንዲውልና በብርሃን ፍጥነት እንዲሰራጭ ይደረጋል። ንጹሐን እንዲታገቱ ይደረግና እገታው በሚፈለገው መንገድ ተቀነባብሮ በማኅበራዊ ሚዲያ እንዲጎን ይደረጋል። ነፍሰጡር ስትሞት፣ ሕጻን እያየ አባት ሲገደል፣ ንብረት ሲቃጠልና ሌሎች በሟችና በሚወድመው ንብረት ሲዛበቱ የሚያሳይ ምስል በተቀናበረ ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይጦዛል። ይህ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በማራ፣ አፋር … ሆኗል። አሁን ደግሞ መልኩን ቀይሮ እየሆነ ነው። ሲሆን ንጹሐን ላይ የደረሰን ጉዳት ለፖለቲካ ገበያ ለማዋል … [Read more...] about በሰማዕትነት ጥሪ ቤተመንግሥቱን ባቋራጭ መቆጣጠር
የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ
ለዘመናት የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤትን ከኢትዮጵያ ለማንሳት እጅግ በርካታ ሙከራዎች ተደርገዋል። ይቀርቡ የነበሩት ምክንያቶች ውሃ የማይቋጥሩ ሆነው በመገኘታቸው ሁሉም ስኬት እንደናፈቃቸው መና ሆነው ቀርተዋል። ሙከራው ግን አላቆመም፤ አሁንም ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ የወንበዴ ቡድን ጋር ጦርነት የገጠመች ጊዜ ይኸው አጀንዳ ቀጠለ። ጦርነቱ ከነበረው በርካታ ድብቅ ዓላማዎች በዋነኛነት የሚጥቀሰው ይህ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይመሰክራሉ። በተለይ በኮቪድ ምክንያት የኅብረቱ ስብሰባ ለሁለት ዓመታት በመስተጓጎሉ በዚያው ከኢትዮጵያ ምድር ተረስቶ እንዲቀር ያልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም። በተለይ የሰሜኑ ጦርነት "በአገሪቱ መረጋጋት የለም" ለሚለው አመክንዮ እንደ ማሳያ ተቆጥሮ ስብሰባው እንዳይካሄድ ከፍተኛ ጫና፣ ግፊት ሲደረግ በነበረበት ወቅት … [Read more...] about የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ
የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው
ክርስቲያኗ ክስ መመሥረቷም ተሰምቷል በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ውስጥ የተፈጠረውን መከፋፍለ ተከትሎ አንደኛውን ወገን ለማውገዝ ተጠርቶ ከነበረው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ መካከል የባህር ዳሩ መሰረዙ ተገለጸ። “ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ጾመ ነነዌን ምክንያት በማድረግ በመላው ዓለም የሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ በጾምና በጸሎት ምሕላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት በመገኘት ወደ እግዚአብሔር ጾም፤ ጸሎትና ምሕላ እንዲቀርብ” ሲል ቅዱስ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት ነው “ጥር 28 በባሕር ዳር ከተማ እሑድ ጥር 28 ፡ 2015 ዓ.ም ባሕር ዳር መስቀል አደባባይ ሊደረግ የነበረው “ኦርቶዶክሳዊ” የተባለው ሰልፍ እና የምህላ ፀሎት መራዘሙ በመግለጫ የተገለጸው። “ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አስተላልፏል። ስለሆነም በቀጣይ … [Read more...] about የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው
የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል
የኮማንዶ ብርጌዱ የተሣካ የተልዕኮ አፈፃፀሙ ታይቶና ተገምግሞ በ1992 ዓ.ም በክፍለጦር ደረጃ ማደጉ ይታወቃል፡፡ ከ2009 ዓ.ም ወዲህ ከክፍለጦር በላይ ሆኖ መደራጀቱም እንዲሁ፡፡ በሀገራችን ላይ የሚፈፀም ማንኛውንም ትንኮሳ መመከት እና መደምሰስ የሚችል አደረጃጀት ለመፍጠር በማሰብ የልዩ ኃይልና የአየር ወለድ አሃዱዎችን በማሥፋት የኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ የሚለውን ስያሜ እና አደረጃጀት አሁን ላይም ይዞ ይገኛል፡፡ የሚሠጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በእምነት የሚፈፅምና በከፍተኛ ፅናት ዘብ የሚቆም እንዲሁም በተሰማራበት የውጊያ ውሎ የውጊያው ማርሽ ቀያሪ እና አይበገሬ ሠራዊት በመገንባት ባሳለፍናቸው ዘመቻዎች አኩሪ የጀግንነት ገድል እንደ ዕዝ በመፈፀም የላቀ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡ በኮማንዶ እና አየር ወለድ ዕዝ ሥር ካሉት ወታደራዊ የአቅም ግንባታ … [Read more...] about የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል
“አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው
በ2014 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከ50 በመቶ በላይ ያመጡት ተፈታኞች 3.3 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሪፖርት እና ዋና ዋና ግኝቶች ዙሪያ መግለጫ የሰጡት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ የዘንድሮው የ12 ከፍል ፈተና ውጤት አስደንጋጭ እንደሆነ እንረዳለን ብለዋል። በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለፈተና የተመዘገቡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በጠቅላላ 985ሺ 354 ተማሪዎች እንደነበሩ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ ከዚህ ውስጥም ለፈተና የቀረቡት ተማሪዎች 908ሺ ሺህ 256 (92.2%) ሲሆኑ 77ሺህ 98 ተማሪዎች ፈተና አልወሰዱም ተብሏል። በትምህርት ዘርፍ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከማህበራዊ ሳይንስ በተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ 31.63 ከመቶ … [Read more...] about “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከመሬት ምዝበራ ጋር በተያያዘ ሁለት አመራሮችና ስድስት ባለሙያዎች በጥቅሉ ስምንት በሙስና የተጠረጠሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። በቁጥጥር ስር የዋሉ አመራሮች፦ 1. አቶ መለሰ ጋሻው የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሃላፊ2. አቶ ፍቃዱ መለሰ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የመሬት ማኔጅመንት ፅ/ቤት ሃላፊ ሲሆኑ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፈፃሚዎች ደግም 3. አቶ ሄኖክ ፍቃዱ (የመሬት አገልግሎት መሻሻያ ዘርፍ አስተባባሪ)4. ሜሮን ማህረይ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)5. አቶ በላይህ ተፈሪ (የቤዝ ማፕ ባለሙያ)6. አቶ ፍቅሬ ብርሃኑ (ፋይል አደራጅ)7. ወ/ሮ ዘላለም በዛብህ (የሲአይ ኤስ ባለሙያ)8. አቶ ሃጎስ በርሄ (የሰነድ አጣሪ ባለሙያ) ናቸው፡፡ የተጀመረው ህግን … [Read more...] about በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ
ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በደንብ ማስከበር ባለስልጣን ቅንጅት በተከናወነ ኦፕሬሽን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለፀ፡፡ ሺሻ የማስጨስ እና ጫት የማስቃም አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና በተለያየ መልኩ ባደረገው ጥናት መነሻነት በየካ፣ በቦሌ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች ሺሻ በሚጨስባቸው ሆቴሎች እና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር በመቀናጀት በተከናወነ የኦፕሬሽን ስራ እርምጃ ተወስዷል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንደገለፀው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና ወረዳ 3 በተለያዩ አካባቢዎች በአጠቃላይ … [Read more...] about ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ
በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ
ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን በማለት ኅብረተሰቡን እያጭበረበሩ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃ እየተወሰደ እንደሚገኝ ተገለጸ። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለኢፕድ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት የደኅንነትና የሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አባል ነን የሚሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በተለያዩ መንገዶች ክትትል ሲደረግ ቆይቷል። ሰሞኑን በተደረጉ ጥብቅ ክትትሎችም ፈለቀ ዴብሳ ደማ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02፤አስፋው አዳማ ሙታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01፤ሳምሶን ገነነ መንገሻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5፤ተስፋ ሀተው ገምቴሳ … [Read more...] about በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ










