ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይታሰባል ተብሎ ባልተገመተ ሁኔታ የዓድዋ በዓል በኢትዮጵያዊነት መንፈስ በትግራይ የዓድዋ ከተማ ሶሎዳ ተራራ ሥር መከበሩን ኢፕድ ዘግቧል።
በበዓሉ ላይ ህፃናት ስለ ዓድዋ ድል የሚተርክ ህብረ ዝማሬ አቅርበዋል።
የከተማው ነዋሪዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በዓሉን ለመታደም ማልደው በሥፍራው ተገኝተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡና በአማርኛ የተጻፉ አስደማሚ መፈክሮች በበዓሉ ሰልፍ ላይ ታይተዋል።
ትህነግ በግፍ በሚገዛት ትግራይ ይህ ዓይነት አከባበር መከሰቱ ለክልሉ ሕዝብ የነጻነት ተስፋ የፈነጠቀ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
gi says
ትሕነአግ በእውነተኛ ኢትዮጵያዊነት ልብና አዕምሮ አገራችንን ሕዝባችንን፣ባንዲራችንን የጋራ ክብራችንን ከመጀመሪያ ትግል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አክብሮ ቢሆን ኢትዮጵያ ዛሬ የአፍሪካዋ ካፒታሊስት አገር በሆነች ነበር ነገር ግን ለመሳሪያ ግዥ ፣ለጦርነትና በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጭ የወጣውና ወደ ውጭ የሸሸው ገንዘብ ኢትዮጵያን 5 አመታት ያለምንም ስራ ማኖር የሚችል ሐብት ነው። አሁንም የትግራይ መሪዎች ልብ ከገዙ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞችና እህቶች ጋር በመሆን አገር መገንባት ይቻላል። መገንጠል የሚሉት በሽታ ደግሞ ጀምረው ሌሎችን መገነጣጠል ዓለማ ላይ ካሉ ደግሞ አድዋን ለመቁረጥ ከፈለጉ አሁንም በቀደሙት ጠላቶች አጅ ወድቀው የአድዋ ምስጥር ከናካቴው እንዳይጠፋ አደሬ እንላቸዋለን።