በአላማጣ ከተማ አሸባሪው ህወሓት ለታጣቂዎቹ አከማችቶት የነበረው ከ3 ሺሕ ኩንታል በላይ የእርዳታ እህል ተገኝቷል። አሸባሪውና ወራሪው የወያኔ ቡድን ለራያ አላማጣ ህዝብ የሚመጣውን የእርዳታ እህል ለህዝቡ ሳያደርስ ለታጣቂዎቹ ቀለብ እንዲውል በየ መጋዝኖቹ እና ወፍጮ ቤቶች አከማችቶት መገኘቱን ነው መረጃው ያመለከተው። ተከማችቶ የተገኘው የእርዳታ እህልም ከ2 ሺሕ 500 ኩንታል በላይ የዩ ኤስ አይዲ የተፈጨ የስንዴ ዱቄት፣ ከ400 ኩንታል በላይ ከረጢት የታሸገ ስንዴ፣ ከ100 ኩንታል በላይ ብስኩቶች እና ኃይል ሰጪ ምግቦች መሆኑም ተገልጿል። የሽብር ቡድኑ ካለፈው 1 ዓመት ከ4 ወር በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ለሰብዓዊ እርዳታ እንዲውል የሚገባ የትኛውንም አይነት ድጋፍ ከህዝቡ እየነጠቀ ለታጣቂዎቹ ሲያከማችና ሲቀልብ እንደነበር የአላማጣ ከተማ ነዋሪዎች ምስክርነታቸውን … [Read more...] about አንድ ጣሳ ማሽላ በ250 ብር በሚሸጥበት አላማጣ ተከማችቶ የነበረ ከ3 ሺሕ ኩንታል በላይ የእርዳታ እህል ተገኘ
Right Column
በአራዳ ክፍለ ከተማ ዜጎች የስፖርት ሜዳ አገኙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ በአዲስ መልክ የተገነባውን የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራ መርቀው ከፍተዋል። በተለምዶ "15 ሜዳ" ተብሎ የሚጠራው የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፋራ ከዚህ ቀደም ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ምቹ እንዳልነበር ተጠቁሟል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አነሳሽነት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በአዲስ መልኩ ተገንበቶ በመጠናቀቁ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል። የስፖርት ማዘውተሪያው ግንባታ ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሚያመች መልኩ የተገነባ በመሆኑ የቀደመ አግልግሎቶቹን እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራው ግንባታ የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮጀክት አካል መሆኑም ተገልጿል። (አዲስ ማለዳ) በዘመነ ት ህነግ አዲስ አበባ ውስጥ ወጣቶች ምንም ዓይነት … [Read more...] about በአራዳ ክፍለ ከተማ ዜጎች የስፖርት ሜዳ አገኙ
የጃል መሮ “ሚስት” አዲስ አበባ ታየች
ሚዲያ ኃይል ነው፤ ሚዲያ አራተኛው የመንግሥት ክንፍ ነው፤ ሚዲያ … ያነሳል ይጥላል፤ ሚዲያ መልካሙን ስም ያዋርዳል፤ ሚዲያ የተበላሸ ስም ይቀድሳል፤ ሚዲያ ነፍሰ ገዳዩን ቅዱስ ያደርጋል፤ ሚዲያ ብርቱ ነው። በተለይ በውጪ መንግሥታት እየተደገፉ ወደ አገራችን የሚተላለፉት የቋንቋ ሚዲያ አውታሮች ውስጥ የሚሠሩት ስብዕናቸውን የሸጡና በሚከፈላቸው ዳረጎት ልክ ራሳቸውን አዋርደው፤ አንገታቸውን ደፍተው የሚኖሩት ሚዲያውን የከፈቱን ታማኝ ሎሌዎች፣ የፍላጎታቸው ማስፈጸሚያዎች ናቸው። ይህንን ስል ግን ለሙያቸው ያደሩና እንከን የማይወጣላቸው ስመጥር የሚዲያ ሰዎች መኖራቸውን ሳልዘነጋ ነው። ጃል መሮ የተባለውን ነፍሰ በላ ወንበዴ፤ መሣሪያ ታጥቆ ምስኪን ገበሬ፣ እናቶችንና ሕጻናትን የሚያርድ በላዔ ሰብ አሁን ላለበት ቁመና ያበቃው በሚዲያ ውስጥ የሚገኙ ስንኩላን ናቸው። አንዳንዶቹ ልዩ ተልዕኮ … [Read more...] about የጃል መሮ “ሚስት” አዲስ አበባ ታየች
ኢትዮጵያን “በእኛ ትውልድ ማንም ተነስቶ እንዲፈነጭባት አልፈልግም” ምክትል ፲ አለቃ በዝናሽ ወዳጆ
ኢትዮጵያ ታፍራ እና ተከብራ እንድትኖር የተሠጠኝን ግዳጅ በጀግንነት እወጣለሁ ትላለች ምክትል ፲ አለቃ በዝናሽ ወዳጆ። በሰቆጣ ግንባር የአሸባሪውን የህወሓት ታጣቂ ዶግ አመድ ካደረጉት ጀግኖች መካከል አንዷ ናት ምክትል አስር አለቃ በዝናሽ ወዳጆ። ምክትል አስር አለቃ በዝናሽ ወዳጆ እንደተናገረችው ኢትዮጵያን ተላላኪ የሽብር ቡድን ሰላሟን እንዳያደፈረስ ላፍታም ቢሆን ሳልዘናጋ የተሠጠኝን ግዳጅ በጀግንነት እወጣለሁ። አባቶች በመስዋትነታቸው ያስረከቡንን ሀገር በእኛ ትውልድ ማንም ተነስቶ እንዲፈነጭባት አልፈልግም። በተሰለፍኩበት ግንባር የሀገሬን ጠላት እስከ መስዋዕትነት ከፍዬ ግዳጄን በቁርጠኝነት እወጣለሁ ብላለች። (መከላከያ ሠራዊት) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ኢትዮጵያን “በእኛ ትውልድ ማንም ተነስቶ እንዲፈነጭባት አልፈልግም” ምክትል ፲ አለቃ በዝናሽ ወዳጆ
“ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም”
"ለዐማራነቴ፤ ለኢትዮጵያዊያነቴ ህይወቴን እሰጣለሁ" እንዳልህ ይኼው ደማህ፤ ልክ እንደ አድዋው ጀግና ፊታውራሪ ገበየሁ "ህወሓትን ፈርቼ ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ፤ ከፊት ለፊት ስፋለም ከወደቅሁ ግን ልጆቼን አደራ" እንዳልህ ክንድህ ላይ በፈሰሰው የደም ጠብታ ቃልኪዳንህን አፀናህ። ባለፈ ጊዜ ለእረፍት መጥቶ ሚስቱ "እባክህ በልጆችህ ልለምንህ አትሂድ" ስትለው "ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም" ነበር ያላት። በርግጥ ይህ የአባቶቻችን ውርስ ነው። ዐፄ ቴዎድሮስ መቅደላ አፋፉ ላይ ሽጉጣቸውን ከወገባቸው ላይ መዘው ሊጨልጡት ባሉበት ቅፅበት ልጃቸው ልዑል አለማየሁን የወለዱላቸው እቴጌ ጥሩ ወርቅ "እባክዎትን ለአንድ ልጅዎት ለልዑል ዓለማየሁ ሲሉ እንኳን ይህን ሀሳብዎን ትተው ይቆዩለት" ቢሏቸው "ልጅ አለማየሁ ከሀገሬ ከኢትዮጵያ አይበልጥም። አንዲት ኢትዮጵያ በዐይኑ እንደዞረች ሞተ … [Read more...] about “ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም”
የትህነግ አመራሮች ልጆቻቸውና የትግራይ ልጆች
የትህነግ አመራሮች ልጆቻቸው በጦርነት ውስጥ አያልፉም። እንቅፋትና ሾህ አያገኟቸውም ብቻ ሳይሆን ስለእሾህና እንቅፋት ኮንሴፕቱም የላቸውም። ልጆቻቸው በውጭ ዩኒቨርስቲዎች ተሞላቀው ይማራሉ፣ በዛው በውጭም ተንደላቀው ይኖራሉ። የራሳቸውን ልጆች በቅንጦት እያስተማሩና በድሎት እያኖሩ የትግራይ የደሃ ልጆችን ግን በመንግስት የሰላም አማራጭ ዕድል ተሰጥቷቸው (ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ) ሳለ ጦርነትን እንዲመርጡና እንደቅጠል እንዲረግፉ ያበረታታሉ። ይቀሰቅሳሉ። የትግራይ ሕዝብ የጀመረውን ተቃውሞ አጠናክሮ ሊቀጥል፣ የቀረበለትን የሰላም ዕድል ወደጎን ገፍቶ ለጋ ልጆቹን ሳይገብር በጦርነት ያገኘው ትርፍ እንደሌለና ለሰላምም ያለውን ጠንካ አቋም መግለፅ ይገባዋል። የትግራይ ሕዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን ለመምረጡ ዋናው ምልክት ደግሞ የትህነግን የጦርነት መንገድ … [Read more...] about የትህነግ አመራሮች ልጆቻቸውና የትግራይ ልጆች
መፍትሔ የራቀው የአሸባሪው ሕወሓት የዘረፋ ሱስ
ባሳለፍነው ሳምንት አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ሰብዓዊ ርዳታዎችን ለሚያመላልሱ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውልና በዓለም ምግብ ፕሮግራም መቀሌ መጋዘን የተከማቸ ነዳጅ መዝረፉ ይፋ መሆኑ አይዘነጋም። በወጣው መረጃም ቡድኑ 12 የነዳጅ ቦቴዎችን በአጠቃላይ 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉ ነው የተመላከተው። የፖለቲካና ፌዴራሊዝም ምሁሩ ሀይለየሱስ (ዶ/ር) አዲስ ልሳን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ አሸባሪው ሕወሓት ከጅምሩ አንስቶ የተለያዩ የስርቆት ወንጀሎችን ሲፈፅም የኖረ መሆኑን አውስተው፤ በተለይ በከፍተኛ የዕለት ደራሽ ድጋፍ ላይ ሲፈፅም የነበረው ዝርፊያ ህዝቡ በረሀብ እንዲያልቅ ከመፍረድ ለይተው እንደማያዩት ነው የገለፁት። አንድ ፓርቲ፤ አንድ ህዝብ የሚል አስተሳሰብ የቆየና ኮሚኒስታዊ አመለካከት እንደሆነ የሚያስረዱት ምሁሩ አክለው እንዳስገነዘቡት፤ አሸባሪ ቡድኑ አሁን ላይ … [Read more...] about መፍትሔ የራቀው የአሸባሪው ሕወሓት የዘረፋ ሱስ
ለአሸባሪው ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ተያዘ
ከበየዳ ወደ ስሃላ ወረዳ በቅብብሎሽ ለሽብርተኛው ህወሓት ሊደርስ የነበረ 1 ሚሊየን 253 ሺህ ብር መያዙን በአማራ ክልል ልዩ ኃይል የተከዜ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ጀጃው ፈረደ ገልጸዋል። አሸባሪው ቡድን ሰርጎ ገቦችን በማዘጋጀት ገንዘብና ቁሳቁስ እንዲሻገርለት ቢፈልግም በአማራ ክልል ልዩ ኃይልና በህብረተሰቡ ጥብቅ ክትትል ዕቅዱ ከሽፏል ብለዋል። ቡድኑ ሊጠቀምበት የነበረ 600 ሊትር አረቂ፣ 10 ጣቃ አቡጀዲ፣ 15 ሺህ 9 የሶላር መብራትና ከአምስት ኩንታል በላይ ጨው እና መሰል ቁሳቁስ ከእነተጠርጣሪዎቹ መያዙን የበየዳ ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል። (Fana) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ለአሸባሪው ህወሓት ሊተላለፍ የነበረ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ተያዘ
በምትኩ ካሳና ግብረአበሮቹ ላይ የሌብነት ክስ ተመሠረተ
የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ምትኩ ካሳ እና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ግብራበሮቹ ላይ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ በዛሬው እለት ክስ መስርቷል፡፡ ተከሳሾች 1ኛ አቶ ምትኩ ካሳ ጉትሌ (የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩ) ፣2ኛአቶ አራጋው ለማ (የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የፋይናንስ ዳይሬክተር)፣ 3ኛ አቶ የማነ ወ/ማሪያም (የኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደ ዴቭሎፕመንት አሶሴሸን ዋና ዳይሬክተር የነበሩ)፣ 4ኛ ዶ/ር ዮናስ ወ/ትንሳይ (የኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደ ዴቭሎፕመንት አሶሴሸን የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ በተጨማሪም 5ኛ አቶ ደመውዝ ኃይሉ (ኤልሻዳይ ሪሊፍ ኤንደ ዴቭሎፕመንት አሶሴሸን የፋይናንስ ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ) ፣6ኛ ወ/ሮ ሶፊያ ጀማል ሰላሙ (የ1ኛ ተከሳሽ የትዳር አጋር) … [Read more...] about በምትኩ ካሳና ግብረአበሮቹ ላይ የሌብነት ክስ ተመሠረተ
በኢሊባቦር ዞን ለዘረፋ የገባው አሸባሪው ሸኔ በጥምር ፀጥታ ሀይሉ መመታቱ ተገለፀ
በኢሊባቦር ዞን ዳሪሙ ወረዳ ዱጳ ከተማን ለማውደምና ለመዝረፍ አልሞ የመጣው የአሸባሪው ሸኔ ቡድን መመታቱን በስፍራው የሚገኘው የክ/ጦር ዋና አዛዥ ተናገረዋል። የዘራፊው ስብስብ ቡድን ሠላምና ፀጥታ በመንሣት አካባቢውን የሽብር ቀጠና ለማድረግ እና የህብረተሠቡን የተረጋጋ ኑሮ ለማወክ አቅዶ ቢመጣም ከክ/ጦሩ ጋር የተጣመረው የፀጥታ ኃይሉ በከፍተኛ ቁርጠኝነት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ አካባቢውን ከስጋት ነፃ ማድረግ መቻሉን ዋና አዛዡ ገልፀዋል። ዋና አዛዡ አክለውም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል እና ማህበረሰቡ ያደረገውን ተጋድሎ በማመስገን ለቀጣይም ጠንክረው ለአካባቢያቸው ሠላም ከፀጥታ አካላቱ ጋር ተባብረው እንዲሠሩ መልዕክት አስተላልፈው የአሸባሪውን ሸኔ ስብስብ በገባበት ገብተን ለመደምሰስ ቀን ከሌት እንሠራለን ብለዋል። ክፍለ ጦሩ እግር በእግር ተከታትሎ ከመታው የሸኔ ዘራፊ … [Read more...] about በኢሊባቦር ዞን ለዘረፋ የገባው አሸባሪው ሸኔ በጥምር ፀጥታ ሀይሉ መመታቱ ተገለፀ