ፈዴሳ ሹማ ይባላል። ተወልዶ ያደገው በቄለም ወለጋ ሲሆን በከተማው ውስጥ በኤሌክትሪክ ጥገና ሙያውም ብዙዎች ያውቁታል፡፡ ሥራው ጥገና እንደመሆኑ የመብራት መጥፋትና መቆራረጥ ሥራውን ብዙ ጊዜ ያስተጓጉልበታል።
ችግር ብልሃትን ይወልዳል እንዲሉ ወጣቱ መላ በመዘየድ ከብዙ ጥረት በኋላ አንድ ግዜ ቻርጅ ተደርጎ እስከ አንድ ዓመት ድረስ አገልግሎት መስጠት የሚችል ቴክኖሎጂ እውን አደረገ። ቴክኖሎጂውንም ይበልጥ አዘምኖ መሥራት ችሏል።
ቴክኖሎጂው የመብራት አገልግሎት ከመስጠቱ ባለፈ ሞባይል፣ ለቴሌቭዥን፣ ፍሪጅና የትኛውንም ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ መጠቀሚያዎችን ቻርጅ የሚያደርግ፣ የሚያንቀሳቅስና በገመድና ገመድ ዓልባ ቴክኖሎጂ መጠቀም እንዲቻል ተደርጎ የተሠራ ነው።
አንዴ የያዘውን ኃይል ሪሳይክል እያደረገ ራሱን ቻርጅ ከማድረግ አልፎ ለረዥም ጊዜ ኃይል ማመንጨት የሚችለው ይህ ቴክኖሎጂ በሀገራችን የኃይል አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።
ከ300 ዋት ጀምሮ እንደ ተጠቃሚው አቅምና ፍላጎት የሚዘጋጀው ይህ ድምፅ አልባ ጄኔሬተር አንድ ጊዜ ቻርጅ ተደርጎ ከአንድ ዓመት በላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚችል ነው ወጣቱ የገለፀው።
በዚህም ወጣቱ ፌዴሳ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በሀገራችን በቤቱ መብራት የማይጠፋበት ብቸኛው ሰው ነው ተብሏል። ወጣቱ ቴክኖሎጂው በስፋት ተመርቶ ለህብረተሰቡ እንዲደርስ እየሰራ ሲሆን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና እገዛ እየተደረገለት እንደሆነም ተነግሯል። (ኢቢሲ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
yednekachew says
invest in such a genius