ዛሬ በተካሄደው የእንደራሴዎች ምክርቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ከጥያቄዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፤ 👉የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ከትምህርት ምዘና ይልቅ ፖለቲካዊ ቅርጽ እየያዘ አገራዊ አደጋ እየሆነ መጥቷል፤ ፈተናውን ኦንላይን ለመስጠት ምን ታስቧል፤👉 የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከአገር አልፎ ለአፍሪካ ኩራት የሆነ የተመሰከረለት ሰራዊት ነው፤ ለዓለም ሰላም ዋጋ ከፍሏል፤ ነገር ግን ዓለም ይሄንን ውለታ ክዷል፤👉 ምዕራባዊያን ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጎን ቆመዋል፤ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ገብተዋል፤ ይህ ለምን ይሆናል?👉 የሱዳን መንግስት ዜጎቻችንን ከሚጨፈጭፉ ቡድኖች ጋር ይተባበራል፤ ትእግስትም ልክ አለውና መንግስት የሱዳንን ወረራና ትንኮስ እንዴት እያየው ነው፤ በሲቃ ውስጥ ላሉ ለታፈኑ የትግራይ ዜጎች መንግስት ምን እገዛ እያደረገ ነው፤ ምን … [Read more...] about “ዛሬ ‘ኃያል ነን’ የሚሉ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ በሚዲያ /በመረጃ/፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይበር እና በተልእኮ የተቀነባበረ ‘ግራጫ ጦርነት’ እያካሄዱባት ነው” ጠ/ሚ ዐቢይ
Right Column
“የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ)ን ማንነት የማያውቅ አንድም በሟቾች ይሸቅጣል፤ በደማቸው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ይጣጣራል፤ ወይም ያወቀ መስሎት ይለፈልፋል፣ ይዘልፋል፣ ይዘፍናል። ትህነግ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ ምህረት የማያውቅ እንደሆነ "ነጻ አወጣሃለው" ባለው ሕዝብ ላይ ለዓመታት የፈጸመውን መመልከት በቂ ነበር። ስለምንረሳና እንደምረሳ ስለሚያውቅ ገድሎ ሙሾ አውራጅ ሆኖ ይመጣል። ጨፍጭፎን ስለ ሰላም ልደራደር ይላል። በወለጋ የተከሰተውንና መቼም የማይረሳውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ በትህነግ ልክ ያለ አካል እና እርሱ አቡክቶ ጋግሮ የሠራው ኦነህ ሸኔ ካልሆነ ማንም ሊያደርገው እንደማይችል መገመት የማይችል ገና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያልገባው የፖለቲካ ሕጻን ነውና አርፎ ተቀምጦ ይማር። ሌሎች ግን አሉ አዛኝ መስለው አጀንዳ የሚፈጽሙ። ባደባባይ ከሰቆቃው ሰለባ በላይ … [Read more...] about “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ
ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርና የስነ ጽሁፍና ፎክሎር መምህሩ ብርሃኑ አሰፋ (ዶ/ር) ሀገራችን ኢትዮጵያ ረዥም ዘመናትን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገሩ የመጡ በየአከባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው ባህላዊ የግጭት አፈታትና የእርቅ ተቋማት አሏት ብለዋል። ለአብነት በወሎ አከባቢ ያሉትን ብናነሳ በራያና አከባቢው ዘወልድ፣ በተሁለደሬና አከባቢው አበጋር፣ በምዕራብ ወሎ አማሬና በሀብሩ አከባቢ ሸህ ለጋን መጥቀስ ይቻላል ያሉት መምህሩ በየአከባቢው ያሉት የግጭት አፈታቶቹ እንደየአከባቢው ባህል፣ ልማድ፣ እምነት እና የአኗኗር ኹኔታ መጠሪያቸውና የአከዋወን ኹኔታቸው ቢለያይም ግጭትን የመፍታትና እርቅን የማውረድ እሳቤያቸው ተመሳሳይ ነው ብለዋል። እነዚህ የግጭት መፍቻ ተቋማት በማኅበረሰቡ እምነትና ስነ ልቦና ላይ የተመሰረቱና አስታራቂዎቹም … [Read more...] about ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ። ፕሮጀክቱ “አሉሙኒየም ፎርም ወርክ ቴክኖሎጂ” የተሰኘ ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ያዋለ ሲሆን÷ ኢትዮጵያውያን ሙያተኞች ቴክኖሎጂውን በማላመድ ግንባታውን በፍጥነት ያከናወኑበት መሆኑም ተገልጿል። ቴክኖሎጂው የግንባታ ጥራትና ፍጥነትን የሚያቀላጥፍ ሲሆን፥ ኮርፖሬሽኑ ይህን ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ በማዋል በ18 ወራት ጊዜ ውስጥ አስር ወለል ያላቸውን 16 ህንጻዎች ያየዘ የመኖሪያ መንደር መገንባት ችሏል። የመኖሪያ መንደሩ ዘመናዊ የደህንነት ጥብቃ ስርዓት የተገጠመለት፣ ከ800 በላይ መኪና ማቆም የሚያስችል ስፍራ፣ የጋራ መጠቀሚያ አዳራሽ፣ የተለያዩ ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ ካፌና ሬስቶራንት፣ መናፈሻ፣ አምፊ ቴአትር፣ የልጆች መጫወቻና መዋኛ ገንዳን ያካተተ መሆኑም … [Read more...] about የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ
በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ
በዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው እና በቀን እስከ 35 ወይም በሳምንት ለ100 ያህል ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። ማዕከሉ በዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን ባሟላው አዲስ ህንፃ ላይ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ነው የተገለፀው። በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ወገኖች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል የተባለለት ማዕከሉ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች በነፃ አገልግሎቱን በመስጠት ተስፋ እንደሚሆንም ተጠቁሟል። ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ማዕከሉ በዛሬ ዕለት (ሰኞ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይመረቃል። (አዲስ ሚዲያ) ማስተካከያ፤ ይህ ዜና በተለጠፈበት ቀን እጥበት ማዕከሉ በሳምንት … [Read more...] about በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ
ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ
በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ ለአሸባሪው ሕወሀት ቡድን ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር መያዙን የአስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። "ከአሸባሪው ሕወሀት ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 20 ሰርጎ ገቦች” በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል። የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ አቶ ሸጌ መንግስቴ ከግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በተደረገ የተቀናጀ ጥረትም ለሕወሀት የሽብር ቡድን ሊደርስ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር መያዙን ገልጸዋል። ገንዘቡን ለሽብር ቡድኑ ሊያደርሱ የነበሩ 20 ተጠርጣሪዎች በጸጥታ ኀይሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን አመልክተዋል። በሌላ በኩል “ከአሸባሪው ሕወሓት ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 20 ሰርጎ ገቦች” በከተማ አስተዳደሩ በቁጥጥር ስር … [Read more...] about ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ
በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ
አንድ የውጪ ሀገር ዜግነት ባለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር እና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ግለሰቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 24 ኮንዶሚኒየም ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለ 3 ወለል ፎቅ ተከራይቶ የሚኖር መሆኑን ገልጿል። ተጠርጣሪው ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የውጭ አገር ዜጎችን እየተቀበለ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራትን ሲፈጽም እንደነበር ከህብረተሰቡ ጥቆማ ማግኘቱንም ነው የገለጸው። ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ፤ጥቆማውን መነሻ በማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተቀናጅተው ባደረጉት ክትትል ግንቦት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በግለሰቡ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ በመኝታ ክፍል ውስጥ የተገኘ 5 ሺህ … [Read more...] about በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ
ሰብዓዊ እርዳታ ወደ መቀሌ መግባት መቀጠሉ ተገለጸ
የዓለም ምግብ ፕሮግራም (ተመድ) የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን አስታወቀ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው፡- በትግራይ እና አፋር ክልሎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሚሰራጨው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በዚህ መሰረትም በትናንትናው ዕለት የሰብዓዊ እርዳታ የያዙ ተጨማሪ 85 የጭነት ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን ነው የገለጸው፡፡ ከዚህ ባለፈም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 130 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እያቀኑ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይህም በተያዘነው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ መቀሌ ከተጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳታ በመጠን ትልቁ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በተመሳሳይ በሰሜን አፋር አካባቢዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች በሚቀጥሉት ቀናት በዓለም የምግብ ፕሮግም የተዘጋጀው … [Read more...] about ሰብዓዊ እርዳታ ወደ መቀሌ መግባት መቀጠሉ ተገለጸ
በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ
በማኅበራዊ ሚዲያ የትህነግን ጉይ እየተከታተለ መረጃ የሚያጋራው አስፋው አብርሃ በትግራይ ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ ካጋራው መረጃ ጥቂቱ እንዲህ ይነበባል፤ በትግራይ ልጁን ለወያኔ ያልሰጠ ወላጅ እየታሰረ ነው። አሁን ይኼ ውጪ አገር የሚኖር ልጅ ነው። በአንድ ወቅት "ወያኔ ቅዱስ ነው " ብሎ FB ላይ ለጥፎ ነበር። አሁን “ወላጅ እናቴ ታስራለች። በሽተኞችን ሳይቀር እየተሸከሙ ያስሯቸዋል” ይላል የባይቶናው ክብሮም በርሄ። ("ልጆቻችሁን ደብቃችኋል ፤አምጡ" እየተባሉ ነው የሚታሰሩት..) የትግራይ ወጣቶች የሚመዘኑበት መስፈርት “ታግሏል ወይስ አልታገለም” የሚል ብቻ ሆኗል። ልጁን ለወያኔው ትግል አሳልፎ ያልሰጠ የትግራይ ወላጅ ደግሞ ለእስር የሚዳረግበት ትልቅ ወንጀል ሆኗል። ይሄ ፅሑፍ ገራሚ ነው። ፅሑፉ ልጃቸውን አምጡ ተብለው ስለታሰሩ አንድ አባት የሚያትት … [Read more...] about በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ
ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ
በሴቶች ጭፈራ ደምቆ በወንዶች የሚታጀበው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራን ለማስተዋወቅ የሁለት ቀን ፌስቲቫል በደሴ ከተማ ተካሂዷል። እራሷን ተሰርታ ወለባ ስጋለች፣ እንሶስላ ሙቃ ሎሚ ጨብጣለች፣ ያች ያገሬ ልጅ እሷዉ ትሆናለች። ሲሉ ጨዋታውን ደመቅ ያደርጉታል የወሎ ወይዛዝርት። ታዲያ በዚህ ጭፈራ ጊዜ ወንዶቹ ሴቶቹን ተቀላቅለው ጭፈራውን ደመቅ ያደርጉታል። አኾላሌ በሃይማኖታዊና ሃይማኖታዊ ባልሆኑ ክብረ በዓላት የሚከናወን ብዙ ጊዜ ጥር ወር ላይ በአርሶ አደሩ የዕረፍት ወቅት፣ በመተጫጫና ጋብቻ እንዲሁም የመዋቢያ ጊዜ የሚከናወን ባህላዊ ጨዋታ ነው። በአብዛኛው በወሎ በተለይም በተውለደሬ የሚከወነው ተዉኔት አዘል ባህላዊ የወጣቶች ጭፈራ ሃይማኖት ሳይለይ በክርስትናም በእስልምና ተከታዮችም ይካሄዳል። አሆላሌ ባህላዊ ጨዋታ የራሱ የኾነ የመከወኛ አጋጣሚዎች እና ወቅቶችም … [Read more...] about ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ