በተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ ከሁለት መቶ በላይ የሞባይል ስልኮችን በህጋዊ ስም በተከፈቱ የንግድ ሱቆች ውስጥ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖለስ አስታውቋል፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ በህጋዊ የሞባይል ስልክ እና የቴሌቪዥን ጥገና ሱቅ ሽፋን ከግለሰቦች የተሰረቁ ስልኮችን እየገዙ ሲሸጡ ከነበሩ ግለሰቦች ሱቅ ውስጥ 215 ሞባይል ስልኮች መያዛቸው ታውቋል፡፡ የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል በወረዳ 3 ኤድናሞል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሞባይል ጥገና ስራ በሚሰሩ አራት የንግድ ሱቆች ላይ ትናንት ሃምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም በህግ አግባብ በተከናወነ ብርበራ ነው ከተለያዩ ቦታዎች ተሰርቀው የተከማቹ ሞባይል ስልኮች ሊያዙ የቻሉት፡፡ ከሞባይል ስልኮቹ በተጨማሪ የወንጀል ፍሬ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ እና በጥገና ቤቶቹ ውስጥ የተገኙ የተለያየ … [Read more...] about የተሰረቁ የሞባይል ስልኮች (215) በህጋዊ ስም በተከፈቱ የንግድ ሱቆች ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ