በወላይታ ዞን በተለያዩ ፈጠራ ሥራዎች የሚታወቅ ወጣት ከ6-10ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል BM-21 የተባለውን አዲስ ሮኬት ሰራ።
በወላይታ ዞን በተለያዩ ፈጠራ ስራዎች የሚታወቅ ወጣት ሳሙኤል ዘካሪያ 360° ዞር መምታት የሚችል BM-21 የተባለውን አዲስ ሮኬት ሰርቶ የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ እና የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በተገኙበት ለእይታ አቅርቧል።
ሮኬቱ ከስድስት እስከ 10 ኪሎ ሜትር መወንጨፍ የሚችል መሆኑን ወጣት ዘካሪያ በመገለጽ በአንዴ አራት ቀላዮችን የሚይዝና መወንጨፍ የሚችል ሮኬት መሰራቱን ገልጸዋል።
ያለሰው ንክኪ በራሱ ማዘዣ 360° ዲግሪ በመዞር በአየር ክልል የሚንቀሳቀስና ጥሶ የሚገባ የጠላት ዒላማን መምታት የሚችል ሮኬት መሆኑንም አስታውቆ ቦታው ከተመቻቸ በኋላ በሳምንታት ውስጥ የተሳካ የማስወንጨፍ ሙከራ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።
በቦታው የተገኙ የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዮሐንስ በየነ ወጣቱ ለሀገር መከላከያ ሠራዊታችን አቅም የሚሆኑና ለሀገራችን ህልውና የሚረዱ ሥራዎችን ከወዲሁ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በሀገራችንም ብዙ ፈጣራ ስራ የሚሰሩ ወጣቶች ቢኖሩም አልተጠቀምንም ያሉት አቶ ዮሐንስ ለሀገራችን አለኝታና መከታ የሚሆኑ እና ተስፋ የሚሰጡ ስራዎችን መሰራቱንም ገልጸዋል።
አዕምሮን ማስራት ከምንም በላይ ነው ያሉት አቶ ዮሐንስ ሁሉም ሰው በራሱ ጥራት ካደረግ ብዙ መስራት እንደሚቻል ይህ ማሳያ ነው ብለዋል።
ወጣቱ እየሰራ ያለው ፈጠራ የሚበረታታ መሆኑን በማድነቅ በፈጠራው ውጤታማና ተስፋ ያለ ስራ እንዲሰራ ከጎኑ ሆኖ ለሚያግዙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
በወጣቱ ጎን በመቆም የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ የዞኑ አስተዳደር ዝግጁ መሆኑንም በመገለጽ ወጣቱን መደገፍ ማለት ሳይንስና ቴክኖሎጂን እና አገርን መደገፍ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በቅርቡ ትበልጽጋለች ስንል የሚሠሩ እጆች፣ አርቀው የሚያስቡ ጭንቅላቶች፣ ደከመኝ ሠለቸኝ የማይሉ አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች እና ምቹ ሁኔታዎች በመኖሩና ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ የሚመጣ በሁሉም ዘርፎች ያለው ለውጥ በመሆኑ አገራችን እንድትበለጽግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply