የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትህ ሚኒስቴር በሽግግር ፍትህ ዙርያ ያሉ የፖሊሲ አማራጮችን ለውይይት መነሻ እንዲሆኑ የቀረቡበትን የፖሊሲ ማዕቀፍ አማራጮች ሰነድ ይፋ አድርጓል። በዚህም ተጠያቂ የሚሆኑ አጥፊዎች በሚለዩበት መንገድ ላይ ኹለት አማራጮች የቀረቡ ሲሆን፣ የመጀመሪያው አማራጭ በወንጀል ክስ ሂደቱ ዋና ጥፋት ፈፃሚዎችን፣ ትዕዛዝ የሰጡ፣ ያቀዱ፣ የመሩ እና ከፍተኛ ሀላፊነት ኖሮባቸው ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉ ግለሰቦች ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ ክስ እንዲመሰረት ማድረግ የሚል ነው፡፡ ኹለተኛው አማራጭ ደግሞ፤ የወንጀል ክስ ሂደቱን በማንኛውም ደረጃ በጉልህ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተሳተፉ ሰዎችን በማካተት እንዲከናወን ማድረግ የሚል ነው፡፡ በፖሊሲ አቅጣጫ አማራጮች መሰረትም የትኞቹ ጉዳዮች እንደሚያስከስሱ፣ በተቋማዊ ጉዳዮች፣ እውነትን … [Read more...] about የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ
Right Column
ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ
በ2014 ዓ.ም. ብቻ ከኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ላይ በተሰረቀ 756 ቶን ብረት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ እንዳጋጠመው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ። በተቋሙ የምስራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እንድሪያስ እንደገለጹት፥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሚያስተዳድራቸው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ ተደጋጋሚ ስርቆት እየተፈፀመ ነው። በ2014 ዓ.ም ብቻ 24 የሚደርሱ ከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ የብረት ማማዎች ሙሉ ለሙሉ ተቆርጠው የወደቁ ሲሆን የብረትና የኮንዳክተር ዘረፋ እንደተፈጸመባቸው እና በቁጥር 30 ሺህ 257 የሚሆኑ የተለያዩ የታወር ብረቶች ደግሞ በቁማቸው ካሉ ማማዎች ተፈትተው መወሰዳቸውን ገልጸዋል። ከወደቁትና በቁማቸው ከተዘረፉት ማማዎች 756 ቶን ብረት መሰረቁን የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ በዚህም በገንዘብ ሲሰላ … [Read more...] about ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ
በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ
በሰላም ንግግሩ በተደረሰው ስምምነት መሠረት ተዓማኒ የሆነና ግልጽነት ያለው የሽግግር ፍትሕ የሚፈፀም መሆኑን የፍትሕ ሚኒስቴር ገለጸ። በሰላም ስምምነቱ በተደረሰው ስምምነት መሠረት ተዓማኒ የሆነና ግልጽነት ያለው የሽግግር ፍትሕ ከአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ፍትሕ የፖሊሲ ማዕቀፍ ጋር በተጣጣመ መልኩ የሚፈፀም መሆኑን የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶክተር) ገልፀዋል። በተደረሰው ስምምነት መሠረት ግልፅ እና ተዓማኒ የሆነ የሽግግር ፍትሕ ለማስፈን እንደሚሠራ የገለፁት ሚኒስትሩ፤ ለዚህም ከያዝነው ወር ጀምሮ ሰፊ የሆኑ ሥራዎች ሁሉንም አካላት ባሳተፈ መልኩ እንደሚሠራ ነው የገለጹት። ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃሳባቸው በሚሰማበት እና ወደ ሽግግር ፍትሕ ለሚደረገው ሂደት የበኩላቸውን ተሳትፎ በሚያደርጉበት ሁኔታ በሚያረጋግጥ መልኩ ተዓማኒነት ያለውና ሁሉን አቀፍ … [Read more...] about በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ
በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት መምህራን አያስፈልጉም
የትምህርት ሚኒስቴር አካሄዱኩት ባለው የዳሰሳ ጥናት፣ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከ30 በመቶ በላይ መምህራን እንደማያስፈልጉ መታወቁን ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የተቋማቸውን የ2015 ዓ.ም. ሩብ ዓመት አፈጻጸም ማክሰኞ ኅዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ለፓርላማ ሲያቀርቡ፣ ዩኒቨርሲቲዎች በአማካይ በሴሚስተር አራት ኮርስ ወይም 12 ክፍለ ጊዜ መያዝ እንዳለባቸው ቢጠበቅባቸውም፣ ብዙዎቹ መምህራን በሴሚስተር አንድ ኮርስ አስተምረው የሙሉ ጊዜ መምህራን ተብለው እንደሚጠሩ ተናግረዋል፡፡ በዚህም የተነሳ የዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ መሆን ከበጀታቸው ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል የመምህራን ቁጥር በመያዝ፣ በልካቸው ሊራመዱ እንደሚገባ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎች ከሌሎች የገንዘብ ምንጮች በሚያገኙዋቸው ገቢዎች ተወዳዳሪና ተመራጭ … [Read more...] about በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት መምህራን አያስፈልጉም
ሃብታቸውን ያላስመዘገቡ ኃላፊዎችን የጠቆመ ከሃብቱ 25% እንዲያገኝ ይደረጋል
ሀብት ያላስመዘገቡ አመራሮችንና ባለሙያዎችን የጠቆመ ሰዉ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ ይደረጋል ሲል የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ። ሀብት በማስመዝገብና በማሳወቅ ሂደት፤ አመራሮችንና ባለሙያዎች ሳያስመዘገቡ የቀሩትን ሀብት የጠቆመ ዜጋ ከተጠቆመው ሀብት ላይ 25 በመቶ እንዲያገኝ እንደሚደረግ የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል። ለዚህም ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ በፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስ እና መረጃ አስተዳደሥ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ፈርዳ ገመዳ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም በአዋጅ ቁጥር 668/2002 በግልፅ መስፈሩን ተናግረዋል። ኮሚሽኑ እስካሁን 763 የመንግስት አመራሮችን ቢለይም፤ እስካሁን ሀብታቸውን ያስመዘገቡት 20 በመቶው ብቻ መሆናቸው ተጠቅሷል። እስካሁንም 2 ሺሕ 272 የፌደራል … [Read more...] about ሃብታቸውን ያላስመዘገቡ ኃላፊዎችን የጠቆመ ከሃብቱ 25% እንዲያገኝ ይደረጋል
ስብሃት ነጋ የመንቀሳቀስ መብቴ ተነፍጓል በማለት ክስ መሠረተ
ለህክምና ወደ ውጭ ሀገር ልሄድ ስል በፌደራል ፖሊስ ከኤርፖርት ታግጃለው ሲሉ ስብሐት ለፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ክሱን ያቀረቡት በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የመሰረታዊ መብቶች ጉዳዮች ችሎት ነው። አቶ ስብሐት ነጋ በከፍተኛ ህመም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ህክምና አድርገው ለመመለስ ወደውጭ ሀገር ሊሄዱ ሲሉ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከኤርፖርት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ለችሎቱ በቀረበው ክስ ላይ ተጠቅሷል። በዚህ በቀረበ ክስ ኢትዮጲያ በአለም አቀፍ ደረጃ የፈረመቻቸውን ህጎችን እና በህገመንግስቱ የተቀመጡ የዜጎችን የመቀሳቀስ መብት በሚጣረዝ መልኩ ፍርድ ቤት ባላዘዘበት ሁኔታ ፖሊስ ከስልጣኑ ውጪ የጉዞ እግድ መጣሉና አቶ ስብሐትን ከኤርፖርት እንዲመለሱ ማድረጉ የህግ አግባብ የሌለው ነው ሲል ጠበቃቸው ታደለ ገ/መድህን ለችሎቱ … [Read more...] about ስብሃት ነጋ የመንቀሳቀስ መብቴ ተነፍጓል በማለት ክስ መሠረተ
የአማራ ሕዝብ በይፋ ይቅርታ ሊጠየቅ ይገባዋል!
አሸባሪው ትህነግ ትጥቅ ይፍታ ተብሏል። አባላቱና ደጋፊዎቹ ትጥቅ አንፈታም እያሉ ነው። እፈታለሁ ቢል እንኳን ትህነግ ትጥቅ ዘርፎ ሲደብቅ የኖረ ድርጅት ነው። የትህነግ ዋናው ትጥቅ ግን የጦር መሳርያ አይደለም። የትህነግ የነፍስ መከፍ፣ የቡድን፣ ከባድ መሳርያው ፀረ አማራ ጥላቻ ነው። እስካሁን የፈፀመው ውድመት በፀረ አማራ ትርክት የተፈፀመ ነው። 1) አሸባሪው ትህነግ ተመስርቶ፣ የጎለመሰው በአማራ ጥላቻ ነው። በግላጭ አማራን የሚረግም ማንፌስቶ አርቅቆ፣ አባላቱን ብቻ ሳይሆን ህዝብን ወዝ የጠገበ ጥላቻ አስታጥቋል። ይህን ትጥቅ መፍታት አለበት። ይህ ትጥቅ የሚፈታው የአማራን ህዝብ ይቅርታ በመጠየቅ ነው። 2) የትህነግ ፀረ አማራ ጥላቻ ለአማራ ህዝብ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ፀረ ኢትዮጵያም ነው። የኢትዮጵያ ታሪክን ከአማራ ጥላቻ ጋር አጋምዶ ኢትዮጵያን ቅኝ ገዥ አድርጓ … [Read more...] about የአማራ ሕዝብ በይፋ ይቅርታ ሊጠየቅ ይገባዋል!
ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ ተያዘ
በአዳማ ከተማ ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ መያዙን የከተማዋ ፖሊስ መመሪያ አስታወቀ። አሽከርካሪው የተያዘው ኮድ 3/89158 ኢ.ት በሆነ ሎቤድ መኪና ገንዘቡን ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ በስውር ደብቆ ሲያጓጉዝ ነው።በአዳማ ከተማ ዳቤ ክፍለ ከተማ ዳቤ ሶሎቄ ልዩ ቦታው ኬላ ፍተሻ ላይ የተያዘው የገንዘብ መጠንም 302ሺህ 400 የአሜሪካን ዶላር መሆኑን 2015የመመሪያው የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል እንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ ገልጸዋል።በብሔራዊ ደህንነትና በአዳማ ከተማ የፀጥታ ሃይሎች ትብብር በ23/2/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ላይ የተያዘው ይሄ ገንዘብ ወደ ውጭ ሃገር በሚጓዝ የኮንቴይነር ጭነት ስር በስውር ቦታ ተደብቆ መሆኑንና አሽከርካሪውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ነው ያስረዱት። (Tikvah) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ300 ሺህ ዶላር በላይ ወደ ውጭ ሃገር ለማስወጣት የሞከረ አሽከርካሪ ተያዘ
ባለፉት ሦስት ወራት የተያዘ ህገ ወጥ ሲሚንቶና ነዳጅ
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በህገ ወጥ መልኩ ሲዘዋወር የነበረ ከ71 ሺህ ኩንታል በላይ ሲሚንቶ እና 500,153 ሊትር ነዳጅ ተይዟል። በዚህም መሰረት፦- በአዲስ አበባ 54,976 ኩንታል ሲሚንቶ- በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት 14,094 ኩንታል ሲሚንቶ፣ እና 49,520 ሊትር ነዳጅ- በአማራ ክልላዊ መንግስት 1,914 ኩንታል እና 39,8505 ሊትር ነዳጅ- በሶማሌ ክልላዊ መንግስት 530 ኩንታል እና 12,560 ሊትር ነዳጅ- በደቡብ ምዕራብ 39,568 ሊትር ነዳጅ በድምሩ 71,514 ኩንታል ሲሚንቶ እና 500,153 ሊትር ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተገኘቶ በህገ ወጥ አካላት ላይም አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ በዚህ ህገ-ወጥ ድርጊት ላይ ተሳተፎ ባደረጉ አካላት ላይ ድርጅት የማሸግ እንዲሁም ምርት የመውረስ … [Read more...] about ባለፉት ሦስት ወራት የተያዘ ህገ ወጥ ሲሚንቶና ነዳጅ
ሳሚ ዶላር አንዱ ነው፤ ሌሎቹስ ዶላር አጣቢዎች? ምነው ዝም ተባሉ?
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ብርቱ ክትትል በህገ-ወጥ መንገድ ከ5.1 ቢሊዮን ብር (ከአምስት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር) በላይ ሲያንቀሳቅስ የነበረ ግለሰብ ከ25 ግብረ-አበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን ገለፀ፡፡ ዜናውን የሰሙ “በነካ እጃችሁ ወኪሎቹ ጋር ጎራ በሉ” ሲሉ ተደምጠዋል። በወንጀሉ የተጠረጠረው ሳሙኤል እጓለ አለሙ በቅፅል ስሙ ሳሚ ዶላር የሚባል ሲሆን ነዋሪነቱን በአዲስ አበባ ከተማ በማድረግ ወደ አሜሪካን ሀገር በተደጋጋሚ የሚመላለስ የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች፣ የቤት እና የቢሮ እቃዎችእንዲሁም ተዛማጅ መገልገያዎች የችርቻሮ ንግድ ፍቃድን ሽፋን በማድረግ ሕገ-ወጥ የውጭ ምንዛሬና በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ተጠርጥሮ በራሱና ዮዲት እጓለ አለሙ ከተባለች እህቱ ጋር በመሆን በስማቸው በተለያዩ ባንኮች … [Read more...] about ሳሚ ዶላር አንዱ ነው፤ ሌሎቹስ ዶላር አጣቢዎች? ምነው ዝም ተባሉ?