
“ዛሬ መጻሕፍት የሚያነቡ ህፃናት ነገ አይሰርቁም፤ በሙስና እና በሌብነት ቀንበር ስር አይወድቁም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
“መጻሕፍት የህይወት ዘመን ጓደኛ ናቸው” እንዳሉት ከተሽከርካሪ ነፃ (car free) መንገድ ያስፈልጋል፤ ከሀሳብ እና ከመጻሕፍት ነፃ የሆነ ጎዳና ግን ሊኖር አይገባም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት ከመደበኛ ስፍራው ባለፈ በአዲስ አበባ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ ለታዳጊ ህፃናት መጻሕፍት ያቀርባል ደግሞም ያነባል፤ ያስነብባልም። ዛሬ መጻሕፍት የሚያነቡ ህፃናት ነገ አይሰርቁም፤ በሙስና እና በሌብነት ቀንበር ስር አይወድቁም ሲሉም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ታነባለች ጎዳናዋም በመጻሕፍት ተሞልቶ ይትረፈረፋል።
“እኛ ኢትዮጵያውያን ካለብን ችግር የምንወጣው ንባብን ልክ እንደ አረንጓዴ አሻራ ዕለት በዕለት ስንተክል ነው“ ብለዋል። ዛሬ ለልጆች እና ለንባብ የምንሰጠው ቦታ የነገይቷን ኢትዮጵያ ፍንትው አድርጎ ያሳየናልም ብለዋል።
ዛሬ ያላነበበ ህፃን፤ መፃህፍት የማይወድ ህፃን፤ ነገ አገር መምራትም ሆነ ብቁ ተተኪ ዜጋ መሆን አይችልም በማለት አስረድተዋል።
መጻሕፍት ማንበብ የመንግስት እና የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን ነገ ከዓለም ጋር የምንቀመጥበት፣ እንዲሁም ዓለምን የምናይበት መነፅር ነው ሲሉም አመላክተዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
ይህን ካሉ ባለስልጣኖቻቸው ያውም በርሳቸው የተመረጡና የተሾሙት በሙስና፤ በዝርፊያና በብልሹ ስነምግባር የተዘፈቁ ያላነበቡና ያልተማሩ ስለሆነ ነው። ወይስ የመስተዳድራቸውና የአገዛዛቸው አልፋና ኦሜጋ መርህ ስለሆነ? ለምሳሌ በቅርቡ ዶክተር ነኝ ያለ የርሳቸው ባለስልጣን አይደለም እንዴ ከሕገ ወጥ ድሕነት አውጥተን ሕጋዊ ድሐ አርገናቸዋል ያለው፤ ያውም በመንግስታቸው መገናኛ ብዙሐንመድረክ ላይ። ይህ ሰው መፁሐፍ ሳያነብ ነው ዶክተር የሆነው? መልሱን ለርሱና ለርሳቸው እንተወው።
ሰፊው ሕዝብና ገበሬው እንደሆነ መጽሐፍ ባያነብም ስሮቆንና ሙስናን ይፀየፋል። ሌብነት በእምነትም፤ በስነምግባርም ውጉዝ ስለሆነበት በእጅጉ ይፀየፈዋል። የርሳቸው ባለስልጣናት አብዛኞቹ በትምሕርት ዶክተሮችና ማስትሬቶች፤ በእምነት ፕሮቴስታንቶችና ዋቄ ፈታዎች እና መፁሐፍ አንበናል እያሉ የሚመፃደቁት ባለስልጣናት አይደሉም እንዴ በስርቆ፤ በሙስና፤ በዘርኝነትና በደም የተጨማለቁት።
በኢትዮጵያም ይሁን በዓለም ሙሰኝነትንና ስርቆን መመሪያና ሕገወጥ መበልፀጊያ ያደረጉ መፁሐፍ ያነበቡና ስልጣን ጥመኛ የሆኑ ባለስልጣናትና ዘረኞች ናቸው። መፁሐፍ አንባቢ መሆን በራሱ ሌባ፤ ሙሰኛና ዘረኛ ከመሆን አያድንም። ጠቅላዩ ወጣቶች መፁሐፍ እንዲአነቡ መገፋፋታቸው ግን ይበልብለናል።
ጠ/ሚንስትሩ ሌብነት ዘሚያስተምርም መጽሃፍ መኖሩን ያውቁ ይሆን_