ሩስያ የክፉ ቀን ወዳጄ ላለቻት ኤርትራ ድሮኖችን በድጋፍ የሰጠችው ለቀጠናው ሰላም ኤርትራ ወሳኝ ሃገር በመሆኗ እና ሩስያ ቀጣይ በኤርትራ ከምጽዋ 40 ኪ/ሜ ርቅት ላይ በኣፍኣቤት ለምትገነባው የጦር ሰፈር እንደ መጀመርያ ግብአትነት በመቁጠር ነው። የድሮን ድጋፉ የተሰጣት ኤርትራ ለአለፉት 3 ወራት በሩስያ ስልጠና የተሰጣቸውን 26 የድሮን ባለሙያዎቿን ጭምር አቀባበል በማድረግ ዛሬ በባፃ የድሮን ጣብያ በድምቀት ተቀብላለች። በዚህ ርክክብ ወቅት የተገኙት የኤርትራው ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአደረጉት ንግግር "ይህ ከሩስያ የተደረገልን ድጋፍ የኤርትራን የጦር ኃይል በጥራት፣ በልምድ፣ በእውቀትና በታጠቀው የጦር መሳርያ በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ያደርገዋል" ሲሉ ተደምጠዋል። ባለፈው ወር የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኦስማን ሳሌህ ሩሲያን በጎበኙት ወቅት የሩሲያው ውጭጉዳይ … [Read more...] about ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች
Archives for May 2022
ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ
በሴቶች ጭፈራ ደምቆ በወንዶች የሚታጀበው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራን ለማስተዋወቅ የሁለት ቀን ፌስቲቫል በደሴ ከተማ ተካሂዷል። እራሷን ተሰርታ ወለባ ስጋለች፣ እንሶስላ ሙቃ ሎሚ ጨብጣለች፣ ያች ያገሬ ልጅ እሷዉ ትሆናለች። ሲሉ ጨዋታውን ደመቅ ያደርጉታል የወሎ ወይዛዝርት። ታዲያ በዚህ ጭፈራ ጊዜ ወንዶቹ ሴቶቹን ተቀላቅለው ጭፈራውን ደመቅ ያደርጉታል። አኾላሌ በሃይማኖታዊና ሃይማኖታዊ ባልሆኑ ክብረ በዓላት የሚከናወን ብዙ ጊዜ ጥር ወር ላይ በአርሶ አደሩ የዕረፍት ወቅት፣ በመተጫጫና ጋብቻ እንዲሁም የመዋቢያ ጊዜ የሚከናወን ባህላዊ ጨዋታ ነው። በአብዛኛው በወሎ በተለይም በተውለደሬ የሚከወነው ተዉኔት አዘል ባህላዊ የወጣቶች ጭፈራ ሃይማኖት ሳይለይ በክርስትናም በእስልምና ተከታዮችም ይካሄዳል። አሆላሌ ባህላዊ ጨዋታ የራሱ የኾነ የመከወኛ አጋጣሚዎች እና ወቅቶችም … [Read more...] about ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ
በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ
በወልዲያ ከተማ ለሶስት ወራት ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ የፋኖ አባላት ተመርቀዋል በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር ዳዊት መለሰ ፋኖ ተገኝተው “የመንግሥትን ጥሪ ተቀብሎ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመሰለፍ በርካታ ውጤቶችን አምጥቷል” ሲሉ ተናግረዋል። ፋኖ ምሬ ወዳጆ በበኩሉ “የተጋረጡብነን ችግሮች ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በአንድነት እንወጣዋለን” በማለት መልዕክት አስተላልፏል። (የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ
“ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው
ሠራዊታችን እንደ አገር ሊቃጣብን የሚችልን ማንኛውም ትንኮሳና ጥቃት በብቃት መመከት በሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ተናገሩ። የትህነግ ቡድን ከጀሌዎቹ ጋር በማበር የከፈተውን አገር የማፍረስ እቅድ መከላከያ ሰራዊቱ በውስብስብ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ማክሸፍ መቻሉን ያስታወሱት ጀኔራል ጌታቸው ከዘመቻ በኋላ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም በመጠቀም ተቋሙ በሞራል፣ በሰው ሃይል፣ በብቃትና በማቴሪያል የተሟላና ግዙፍ ኃይል እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ሠራዊታችን እያንዳንዷን ሰዓት በስልጠና ላይ በማዋል መቺና ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ እንዲደርስ ማድረግ ተችሏል ያሉት ጄነራል መኮንኑ አገራችንን ለመድፈር በሚያስቡ አካላት ላይ መንግስት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሰረት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ … [Read more...] about “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው
ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ
ግምቱ 64 ሚሊዮን ብር የሆነ ወርቅ በህገ-ወጥ መንገድ ደብቆ ኬላ ጥሶ ለማለፍ የሞከረው አሽከርካሪ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፤ የጉምሩክ እና በአካባቢው በነበሩ የኦሮሚያ ክልል የሚሊሻ ኃይል ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ። ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ከቀኑ በ11:30 በኦሮሚያ ክልል ነጌሌ ቦረና ከተማ ዶሎ በር ኬላ ሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ-3-ኢት AA 03775 የሆነ ትዮታ ደብል ፒክአፕ ላንድ ክሩዘር ከነጋሌ ከተማ ወደ ሶማሌ ክልል ለመሄድ ቀጥታ በጉምሩክ ኬላ በኩል መጥቶ ለፍተሻ ሲያስቆሙት ፊቃደኛ ባለመሆን በኬላው ጎን ባለው የእግረኛ መንገድ በመጠቀም ጥሶ ለማለፍ ሲሞክር ለማስቆም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ጥይት ቢተኩሱም ሳይቆም በማምለጥ ላይ እያለ የጉምሩክና የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አባላት በአካባቢው ለነበረው ኮማንድ ፖስት መረጃውን በፍጥነት ማስተላለፉን … [Read more...] about ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ
አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ
"የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሥልጣን" የለውም ክርስቲያን ታደለ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የንቅናቄውን ህግ ጥሰዋል በሚል 10 አባላቱን ከአባልነት አገደ፡፡ አብን ባወጣው መግለጫ ከድርጅት ህገ-ደንብ እና አሰራር ውጭ በመሆን አፍራሽ ድርጊቶችንና የዲሲፕሊን ጥሰቶችን በፈፀሙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰኑን ገልጿል፡፡ የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አደረኩት ባለው አስቸኳይ ስብሰባ በፓርቲው መዋቅር የተለያዩ የሃላፊነት እርከኖች ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ የዲሲፕሊን እና ድርጅታዊ መርህ ጥሰቶችን በፈጸሙ አባላቱ ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ የንቅናቄው ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሳለ አፍራሽ ተልዕኮን ሲያረራምዱ ተገኝተዋል በሚል … [Read more...] about አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ
ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ
የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ይድነቃቸዉ ተክሉ በወልቂጤ ከተማ በጉብሬ ክፍለ ከተማ አባፍሯንሷ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪ ነዉ። ከ10 በላይ የተለያዩ የሳይንሰና የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች ስራ ባለቤት ሲሆን ከነዚህ የፈጠራ ስራዎች መካከል የእናቶች ጉልበትና ጊዜ ማስቀረት የሚያስችል የእንጀራ መጋገሪያ ቴክኖሎጂ ፈጥሯል። ይህ የእንጀራ መጋገሪያ ቴክኖሎጂ እራሱ ያቦካል ፣ እራሱ ያሟሻል፣ እራሱ ይጋግራል እንዲሁም እንጀራዉ ሲደርስ እራሱ ከምጣዱ ላይ ያወጣል። የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ባዘጋጀዉ 3ኛዉ ዙር የሳይንስና የሒሳብ ትምህርቶች ቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽንና ዉድድር ላይ እናቶችን ከጭስ የሚገላግለዉ የእንጀራ መጋገሪያዉና ሌሎችም በርካታ ቴክኖሎጂዎች ይዞ የቀረበዉ የአባ ፍሯንሷ ፈርጥ ይድነቃቸዉ ተክሉ በውድድሩ 1ኛ ደረጃ በመውሰድ … [Read more...] about ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ
በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ
በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 19 ህጻናትንና 6 አዘዋዋሪ ሴቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። እድሜያቸው ከ5 እስከ 10 የሚገመቱ ህጻናቶችን አዘዋዋሪዎቹ ማዳበሪያ በማልበስ አፍነው ሲያጓጉዟቸው እንደነበር የገለጹት የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ እንስፔክተር ሸምሱ ጠቁመዋል። ህጻናቱ ወራቤ ከተማ ሲደርሱ ባሰሙት ጩሀት መነሻ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተከታትሎ ከተማ አስተዳደር ህጻናቱንና አዘዋዋሪ እናቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጸዋል። አዘዋዋሪ እናቶች በሰጡት አስተያየት በዚህ ተግባር ተሳታፊዎች ቁጥር በርካቶች መሆናቸውን ገልፀው በጠዋቱ ክፍለጊዜ ህጻናትን የጫነ አንድ መኪና ወደ አዲስ አበባ መጓዙንም ተናግረዋል። የዚህን መሰል የወንጀል ተግባራትን ከጸጥታው አካል ጎን በመሆን ሊከላከልእንደሚገባም እንስፔክተሩ ጥሪ … [Read more...] about በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ
በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ
የአርሲ ዞን ሙኔሣ ወረዳ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ቤተክርስቲያን ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብር እና 20 የቀንድ ከብቶች አሰባስበው አበርክተዋል። በወረዳው የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ለዘመናት በመከባበር እና በመቻቻል በፍቅር አብረው እየኖሩ መሆኑን የሁለቱ ሃይማኖቶች ተከታዮች ገልጸዋል። የሁለቱም እምነት ተከታዮች አንዳቸው ለሌኛው በየተራ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ተባብረው እያሠሩ በክፉ እና በደጉ አብረው ቆመው እስከ አሁን ደርሰዋል። የሁለቱ እምነት ተከታዮች አንዱ ለአንዱ ቤተ እምነት መሥራት የቆየ ከአባቶቻችን የወረስነው እሴት ስለሆነ እኛም ይህንኑ እያስቀጠልን ነው ብለዋል። የሥርዓት ለውጥም ሆነ የፖለቲካ ችግር ሀገሪቷን በገጠማት ወቅት ምንም ዓይነት የሃይማኖት ግጭት በወረዳው ተከስቶ አያውቅም ያሉት ነዋሪዎቹ፣ … [Read more...] about በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ
በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ
በትግራይ እናቶች "ልጆቻችሁን አምጡ" እየተባሉ በትህነግ ሰዎች እየታሰሩና እየተገደሉ ነው። ዘምተው የሞቱ ልጆቻቸውንም ሳይቀር "ውሸት ነው አልሞተም ልጅሸን አምጭ" እየተባሉ ችጋር ከሚጠብሳቸው ሌላ በየቀኑ ግፍ ይፈጸምባቸዋል። የወንበዴው ቡድን ዋና ግፍ ፈጻሚ አግአዚን ሲመራ የነበረውና በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮምዩኒኬሽን ኤሌክትሮኒክስ ሳይበር ዋና መምርያ ኃላፊ በነበረበት ጊዜ ከሰሜን ዕዝ ጋር የነበረውን ወታደራዊ የሬዲዮ ግንኙነት እንዲቋረጥ ያደረገው ገብረመድህን ወይም እነሱ ወዲ ነጮ እያሉ የሚጠሩት ቀብር አዲስ አበባ በተፈጸመበት ወቅት ደጋፊ ትህነጎች ወጥተው ትግራይ ትስርር እያሉ ሲጮሁ ነበር። አሸባሪ የተባለን ቡድን በአደባባይ በመደገፍ ይህንን ያህል ሰው ድምጹን ካሰማ ፈርቶ ዝም ያለውና ቀን የሚጠብቀው ምን ያህል ይሆን። በቂ የቪዲዮና የመንገድ ላይ ካሜራ … [Read more...] about በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ