• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ

May 9, 2022 08:58 am by Editor Leave a Comment

“የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሥልጣን” የለውም ክርስቲያን ታደለ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የንቅናቄውን ህግ ጥሰዋል በሚል 10 አባላቱን ከአባልነት አገደ፡፡

አብን ባወጣው መግለጫ ከድርጅት ህገ-ደንብ እና አሰራር ውጭ በመሆን አፍራሽ ድርጊቶችንና የዲሲፕሊን ጥሰቶችን በፈፀሙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰኑን ገልጿል፡፡

የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አደረኩት ባለው አስቸኳይ ስብሰባ በፓርቲው መዋቅር የተለያዩ የሃላፊነት እርከኖች ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ የዲሲፕሊን እና ድርጅታዊ መርህ ጥሰቶችን በፈጸሙ አባላቱ ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት የፓርቲው ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ የንቅናቄው ስራ አስፈጻሚ ሆነው ሳለ አፍራሽ ተልዕኮን ሲያረራምዱ ተገኝተዋል በሚል የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡

አቶ ክርስቲያን የተጣለባቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው በተለያዩ አፍራሽ ድርጊቶች ላይ የተሳተፉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ሁለት ጊዜ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ አቶ ክርስቲያን በንቅናቄው ሥራ አስፈፃሚነታቸውም ሆነ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው በጋራ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመሆን እና ንቅናቄውን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ አንጃዎች ጋር ሕብረት ፈጥረው ንቅናቄው የሃሳብና የተግባር አንድነት እንዳይኖረው በሚያደርጉ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ስለተገኙ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ተወስኗል ብሏል ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፡፡

አብን ከዚህ በተጨማሪም በፓርቲው መዋቅር ውስጥ በተለያየ የሃላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ የንቅናቄው መካከለኛ አመራሮችና አባላት የሆኑት አቶ አንተነህ ስለሺ መርዕድ፣ አቶ እሱባለው ሙላት ዘለቀ፣ አቶ ንጉሥ ይልቃል ያለው፣ አቶ ዓለሙ ወልዴ አከለ፣ ዶ/ር ጌታሁን ሣህሌ ወልዴ /የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል/፣አቶ የማነ ብርሃን ሙጬ፣ አቶ ጓዴ ካሴ ወልዴ፣ አቶ ስንታየሁ ተስፋው ስዩም፣ አቶ እስክንድር ለማ በቀለ እና አቶ ጌታነህ ወርቁ ይርዳው ከአባልነት እንዲታገዱ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

አባላቱ በድርጅት አመራርነት የተጣለባቸውን ሃላፊነት ወደጎን በመተው በፓርቲው ስራ አስፈጻሚም ሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴ ወይም ጠቅላላ ጉባኤ የጠቅላላ ጉባኤ ዝግጅትን በሚመለከት የተሰጣቸው ውክልና ሳይኖር፣ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካይ ነን በማለት ህገወጥ ቅስቀሳና አድማ መምራትና በንቅናቄው ውስጥ አንጃ መፍጠር፤ የጉባኤ አባላትን በተለያዩ አሉባልታዎች በማደናገር እና የተሳሳተ መረጃ በመስጠት ፊርማ ማሰባሰብ፣ ህገወጥ የጠቅላላ ጉባኤ ውክልና ይገባኛል መጠየቅና ድርጅታዊ ሥልጣን በእጅ አዙር ለመንጠቅ መሞከር፤ ከንቅናቄው እውቅና ውጭ የሆኑ የቴሌግራም ቡድኖችን በመክፈት አፍራሽ ቅስቀሳዎችን ማድረግ፤ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ ለመጥራት ምንም አይነት ስልጣን ሳይኖራቸው፣ ጉባኤ ጠርተን ሪፎርም እናካሂዳለን በማለት ከድርጅቱ እውቅና ውጭ ገንዘብ አሰባስበዋል የሚሉ ጥፋቶችን ጭምር ፈጽመዋል ተብሏል፡፡

እንዲሁም አባላቱ የድርጅቱን ደንብ ተላልፎና ከሚመለከተው ክፍል ፈቃድ ሳይኖር በየሚዲያው መግለጫ መስጠት፣ ድርጅታዊ ምሥጢር ማባከን በንቅናቄው ላይ መሰረተ ቢስ ክሶች በመሰንዘር እና በከፍተኛ አመራሩ ላይ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈታቸውንም ንቅናቄው ገልጿል፡፡

ፓርቲው አቶ ሀብታሙ በላይነህ መኮንን እና አቶ በቀለ ምንባለ አምሳሉ ለተባሉ አባሎቹ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠቱንም አክሏል፡፡

እነዚህ ሁለት የፓርቲው አባላት የንቅናቄው ቋሚ ኮሚቴዎች አባላትና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው እያለ በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አብረው ውሳኔ ያሳለፉበትን አጀንዳ በእጅ አዙር ለመቀልበስ አባላትን በማሳደም ፤ ለንቅናቄው የስብሰባና ሥነስርዓታዊ ህጎች፣ እንዲሁም ለዴሞክራሲያዊ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት ባለመገዛትና የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎችን ረግጦ በመውጣት ተደጋጋሚ ጥሰቶችን መፈፀማቸውን ፓርቲው በመግለጫው አስቀምጧል፡፡ (አል አይን)

አብን ለሰጠው ማስጠንቀቂያ ክርስቲያን ታደለ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል፤

“ለሚመለከተው ሁሉ፦
በአብን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስም የወጣውን መግለጫ ያየሁት ዘግይቼ ነው። ፍሬ ነገሩ ልክ ይሁንም፥ አይሁንም መሰል ውሳኔዎችን ለመወሰን ግን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሥልጣን የሌለው መሆኑን ለንቅናቄያችን አባላትና ደጋፊዎች መግለጽ እፈልጋለሁ። ንቅናቄው የተመሰረተባቸውን ሕዝባዊና አገራዊ ጥያቄዎች ከግብ እንዲያደርስ ሁላችንም በጎ ሚና እንድንጫዎት አደራ ማለት እፈልጋለሁ።”

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: Christian Tadele, nama, operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm
  • አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን March 15, 2023 08:52 am
  • ጠቅላላ ጉባኤን ያስተጓጎሉ ላይ ክስ እንዲመሰረት ምርጫ ቦርድ ጠየቀ March 15, 2023 08:48 am
  • በኦሮሚያ የተሽከርካሪ ፍጥነት መገደቢያ ገጠማ ያለ አግባብ ለአንድ ግለሰብ ተሰጥቷል ተባለ March 15, 2023 01:43 am
  • ምርጫ ለተወዳደሩና እውቅና ላላቸው ፓርቲዎችመንግሥት 106 ሚሊዮን ብር መደበ March 15, 2023 12:52 am
  • አረመኔና Transgender “ደፋር ሴቶች” ተብለው በተሸለሙበት መዓዛም ተሸለመች  March 10, 2023 10:45 pm
  • ዓድዋ 127 በዓድዋ ከተማ March 2, 2023 09:56 am
  • በምኒሊክ አደባባይ የአድዋ ድል በዓል አከባበር ላይ ምን ተፈጠረ? March 2, 2023 09:43 am
  • አውቶቡሶቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ ብር ነው የተገዙት February 24, 2023 10:44 am
  • በአውቶቡሶቹ ግዢ ቢያንስ 1 ቢሊዮን ብር ተሰርቋል፤ ዶ/ር ዐቢይ አስቸኳይ ማብራሪያ ጠይቀዋል February 24, 2023 08:39 am
  • የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ! February 24, 2023 08:19 am
  • “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ February 21, 2023 10:09 am
  • አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት ቋንቋ እንዲሆን የቀረበ ጥሪ February 21, 2023 10:01 am
  • በገፊና ጎታች ሤራ ከመፈንቅለ ሲኖዶስ እስከ መፈንቅለ መንግሥት February 17, 2023 06:39 pm
  • ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት February 17, 2023 12:35 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule