የአርሲ ዞን ሙኔሣ ወረዳ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ቤተክርስቲያን ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብር እና 20 የቀንድ ከብቶች አሰባስበው አበርክተዋል። በወረዳው የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ለዘመናት በመከባበር እና በመቻቻል በፍቅር አብረው እየኖሩ መሆኑን የሁለቱ ሃይማኖቶች ተከታዮች ገልጸዋል። የሁለቱም እምነት ተከታዮች አንዳቸው ለሌኛው በየተራ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ተባብረው እያሠሩ በክፉ እና በደጉ አብረው ቆመው እስከ አሁን ደርሰዋል። የሁለቱ እምነት ተከታዮች አንዱ ለአንዱ ቤተ እምነት መሥራት የቆየ ከአባቶቻችን የወረስነው እሴት ስለሆነ እኛም ይህንኑ እያስቀጠልን ነው ብለዋል። የሥርዓት ለውጥም ሆነ የፖለቲካ ችግር ሀገሪቷን በገጠማት ወቅት ምንም ዓይነት የሃይማኖት ግጭት በወረዳው ተከስቶ አያውቅም ያሉት ነዋሪዎቹ፣ … [Read more...] about በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ
christianity
ዳያስፖራና “Halloween”
አገራችንን ለቅቀን ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ በባዕድ አገር በርካታ የምንማራቸው፤ የምንለምዳቸው ባህሎች አሉ፡፡ የዚያኑ ያህል መማር የሌለብን ወይም እንዳልተማርን መሆን ያለብንም አሉ፡፡ በተለይ በአሜሪካ ከበርካታዎቹ ሸግዬ ባህሎች መካከል የምስጋና ቀን “Thanksgiving Day” የሚጠቀስ ነው - ወደ ታሪኩና ዝርዝሩ ሳልገባ እንደው በደፈናው ማመስገን መልካም ነው፤ ለዚያም ቢያንስ በዓመት አንዴ ቀን መመደብ ተገቢ ነው በሚለው እሳቤ ብቻ፡፡ ከማማረርና ማጉረምረም አንዳንዴም ባርኮትን ቆጥሮ (ጥቂትም ቢሆን) ማመስገን ሸጋ ነው - ምስጋናው ደግሞ ለፈጣሪ ብቻ ሳይሆን፤ ለወላጅ፣ ለቤተሰብ፣ ለፍቅረኛ፣ ለትዳር ጓደኛ፣ ለልጆች፣ ለወገን፣ ላገር ልጅ፣ … ማብቂያ የለውም፡፡ ታዲያ “ሃሎዊንስ”? የመሰልጠናችን፣ የፈረንጁን ባሕል የመልመዳችን፣ ከኋላ ቀርነት የመላቀቃችን፣ … ምልክት ስለሆነ ይሆን … [Read more...] about ዳያስፖራና “Halloween”