አገራችንን ለቅቀን ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ በባዕድ አገር በርካታ የምንማራቸው፤ የምንለምዳቸው ባህሎች አሉ፡፡ የዚያኑ ያህል መማር የሌለብን ወይም እንዳልተማርን መሆን ያለብንም አሉ፡፡ በተለይ በአሜሪካ ከበርካታዎቹ ሸግዬ ባህሎች መካከል የምስጋና ቀን “Thanksgiving Day” የሚጠቀስ ነው - ወደ ታሪኩና ዝርዝሩ ሳልገባ እንደው በደፈናው ማመስገን መልካም ነው፤ ለዚያም ቢያንስ በዓመት አንዴ ቀን መመደብ ተገቢ ነው በሚለው እሳቤ ብቻ፡፡ ከማማረርና ማጉረምረም አንዳንዴም ባርኮትን ቆጥሮ (ጥቂትም ቢሆን) ማመስገን ሸጋ ነው - ምስጋናው ደግሞ ለፈጣሪ ብቻ ሳይሆን፤ ለወላጅ፣ ለቤተሰብ፣ ለፍቅረኛ፣ ለትዳር ጓደኛ፣ ለልጆች፣ ለወገን፣ ላገር ልጅ፣ … ማብቂያ የለውም፡፡ ታዲያ “ሃሎዊንስ”? የመሰልጠናችን፣ የፈረንጁን ባሕል የመልመዳችን፣ ከኋላ ቀርነት የመላቀቃችን፣ … ምልክት ስለሆነ ይሆን … [Read more...] about ዳያስፖራና “Halloween”