
አገራችንን ለቅቀን ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ በባዕድ አገር በርካታ የምንማራቸው፤ የምንለምዳቸው ባህሎች አሉ፡፡ የዚያኑ ያህል መማር የሌለብን ወይም እንዳልተማርን መሆን ያለብንም አሉ፡፡ በተለይ በአሜሪካ ከበርካታዎቹ ሸግዬ ባህሎች መካከል የምስጋና ቀን “Thanksgiving Day” የሚጠቀስ ነው – ወደ ታሪኩና ዝርዝሩ ሳልገባ እንደው በደፈናው ማመስገን መልካም ነው፤ ለዚያም ቢያንስ በዓመት አንዴ ቀን መመደብ ተገቢ ነው በሚለው እሳቤ ብቻ፡፡ ከማማረርና ማጉረምረም አንዳንዴም ባርኮትን ቆጥሮ (ጥቂትም ቢሆን) ማመስገን ሸጋ ነው – ምስጋናው ደግሞ ለፈጣሪ ብቻ ሳይሆን፤ ለወላጅ፣ ለቤተሰብ፣ ለፍቅረኛ፣ ለትዳር ጓደኛ፣ ለልጆች፣ ለወገን፣ ላገር ልጅ፣ … ማብቂያ የለውም፡፡ ታዲያ “ሃሎዊንስ”? የመሰልጠናችን፣ የፈረንጁን ባሕል የመልመዳችን፣ ከኋላ ቀርነት የመላቀቃችን፣ … ምልክት ስለሆነ ይሆን የምናከብረው? እየፈራን ስለምናስፈራ፤ እያስፈራራን ስለምንፈራ …?
ከላይ እንዳልኩት በዚህ የውጪ አገር ብዙ ነገሮችን ከመማራችን የተነሳ ምርቱን ከግርዱ መለየት ያቃተን ይመስላል፡፡ አገር ቤት ሳለን ፈጽሞ የማንነካውን የአሳማ ሥጋ እዚህ መጥተን ከነቆዳው እናስነካዋለን፡፡ እኛ እንኳን ባናደርገውም ልጆቻችን ከአሳማ ሥጋ እስከ አምባዛ፣ ሽሪምፕ፣ … ባገኙት ቦታ – ትምህርት ቤት፣ ምግብቤት፣ … እንዲመገቡ ከመፍቀድ አልፈን ሃይማኖታችን እና የምናነበው መጽሐፍ (በእስልምናም ሆነ በክርስትና) እንደማይፈቅድ እያወቅን “እነርሱ እዚህ ስለተወለዱ ነው፤ ባሕላቸው ነው፤ … ” የሚሉ ሰንካላ ምክንያቶች እየሰጠን ይህ ሥልጣኔ መስሎን የተሸወድን ጥቂቶች አይደለንም፡፡ ሌላው የተሸወድንበት ደግሞ ይኸው ከጥቂት ቀናት በኋላ የኦክቶበር ወር ሲያልቅ የሚከበረው “ሃሎዊን” የተባለውን በዓል በማክበር ነው፡፡ ለመሆኑ ሃሎዊን ምንድነው? እንዴት ተጀመረ? ታሪካዊ አመጣጡስ ምን ይመስላል? ከተለያየ ቦታ የቃረምኩትን ባጭሩ እንዲህ ላቅርበው፡፡ በነገራችን ላይ የሃሎዊን ትክክለኛ አመጣጥና አከባበር ዝርዝር በምሁራን ዘንድ እስካሁን ስምምነት ላይ ያልተደረሰበት አጨቃጫቂ ጉዳይ መሆኑን ሳልጠቁም አላልፍም፤ አጠቃላይ ስምምነት የተወሰደበት ታሪክ ግን ይህንን ይመስላል፡፡
አሁን አየርላንድን፣ እንግሊዝን እና ሰሜን ፈረንሳይን በሚያካልለው ስፍራ ከመካከለኛው ዘመን በፊት ይኖር የነበረ “ሴልቲክ” የሚባል ህዝብ ነበር፡፡ ሴልቲኮች ወቅቶቻቸውን አሁን እንዳለው ሳይሆን በሁለት ነበር የተከፈሉት – በጋውን “ግማሽ ብርሃን” ክረምቱ ደግሞ “ግማሽ ጨለማ” በማለት፡፡ እነዚህ ሁለቱ ወቅቶች የሚቀያየሩት ደግሞ ኦክቶበር 31 ነበር – በጋው የሚያበቃበትና የቀኑ ብርሃን አጭር በሆነውና በሞት በሚመሰለው የክረምት ወራት የሚተካበት፡፡ በሴልቲኮች እምነት ወራቶቹ ሲቀያየሩና ብርሃን በጨለማ ሲተካ ኦክቶበር 31ቀን የሕያዋን ምድርም ሆነ የሙታን ምድር በብዥታ የተሞላ ይሆናል፤ ሙታንም ነፍሳትን ለመጎብኘት ወደዚህ የህያዋን ምድር ይፈልሳሉ፡፡ እነዚህ የሙት መናፍስት ጉብኝታቸውን ሲያደርጉ ለመደበቅና ላለመታወቅ የሚፈልጉት ሴልቲኮች ጭምብል (ማስክ) በማድረግና ራሳቸውን በመቀየር ለማምለጥ ሙከራ ያደርጋሉ – (trick the ghosts)፡፡ እንዲያውም የሴልቲክ ካህናት ለሕዝቡ የሚሰጡት ምክር ነበር – ነዋሪው ሁሉ በየቤቱ እየሄደ ከሰዉ ሁሉ ጣፋጭ ምግቦችን እንዲሰበስብና ጭራቅ፣ አጋንንት፣ መናፍስት፣ ወዘተ በመምሰል ሊጎዷቸው ለሚመጡት የሙታን መናፍስት ጣፋጩን በመስጠት እንዲያባብሏቸው፡፡ አለበለዚያ መናፍስቱ በሚገባው ካልተስተናገዱ በሰዉ ላይ የማታለል ተግባር (trick) እንደሚፈጽሙ … ምን ያስታውሳችኋል? ባሁኑ ጊዜ ሃሎዊን ሲከበር ለልጆች ከረሜላ ሲሰጥ ምንድነው የሚባለው – (trick or treat) – ነገሮች ከምንም አይጀመሩም፡፡
ሌላው በዚህ የወቅት መለወጫ ጊዜ “የብርሃን ዘመን” መጠናቀቁን ለማወጅና መናፍስቱ ከመጪው የክረምት ወራት ሕዝቡን እንዲታደጉ የችቦ ደመራ ይበራል – ጭለማው የክረምት ጊዜያት የበራ እንዲሆን በመመኘት፡፡ በዚህ ምሽት በርካታ ጥንቆላ፣ ከአጋንንት የመነጋገር ተግባራትም ይፈጸማሉ፡፡ ሰዎች የሞቱባቸውን ዘመዶቻቸውን በመናፍስቱ አማካኝነት ይጠራሉ፤ መጪው የሰብል ዘመን ምን እንደሚሆን ይጠይቃሉ/ያስጠነቁላሉ፤ መስተፋቅር ይጠየቃል፤ ሴቶች መስታወት ፊት ሻማ ይዘው በመቆም የወደፊት የትዳር ጓደኛቸውን በመስታወቱ ውስጥ ብቅ ሲል ለማየት ጭለማ ውስጥ ያፈጥጣሉ፡፡ ሌሎችም እጅግ በርካታ መናፍስትን የመጥራትና ከአጋንንት ጋር የመገናኘት ተግባራት ይከናወናሉ፡፡
“የሰይጣን ዱባ”
በሃሎዊን ጊዜ በዋናነት ጥቅም ላይ የሚውለው ዱባ (እኔ ለዚህ ጽሑፍ ስል “የሰይጣን ዱባ” ያልኩት) ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ሴልቲኮች የሙት መናፍስት እንዳይጎዷቸው ከእነርሱ ለማራቅ ከሚጠቀሙት ብልሃቶች መካከል አንዱ ይህ ነበር፡፡ ዱባውን በቅርጽ በማውጣት ውስጡን በሻማ በማብራት መናፍስቱን ለማስፈራራት ይጠቀሙበታል፡፡ ሌሎች ደግሞ “የኩራዙ ጃክ” (“Jack of the Lantern”) በሚባለው አፈታሪክ መሠረት አንድ ጃክ የተባለ ግለሰብ ለዲያቢሎስ አንዳንድ ቀልዶች በመንገር ሰይጣንን በልጦ ለመገኘት ባደረገው ሙከራ ዲያቢሎስ በመናደዱ ጃክ ዕድሜውን በሙሉ የበራ ኩራዝ ይዞ እንዲዞር በማድረግ ሰዎች ዲያቢሎስን እንዳያታልሉ የማስጠንቀቂያ መማሪያ እንዲሆን ብሎ ያደረገው ነው ይላሉ፡፡
ሃሎዊን ክርስትና ውስጥ እንዴት ሰርጎ ገባ?
በቀደምት ክርስቲያኖች ዘንድ “የሁሉም ቅዱሳን ቀን” ተብሎ በዘመናት ሰማዕት የሆኑ የሚዘከሩበት (ሰማዕታቱ “ዘክሩን” ብለው ባይጠይቁም) ቀን ነበር – የሚከበረው ኖቬምበር 1ቀን ነው፡፡ ከዚህ ቀን በፊት ያለው የዋዜማ ቀን “የቅዱሳን ዋዜማ ቀን” ወይም በእንግሊዝኛው “All Hallows Eve” እየተባለ መጠራት ሲጀምር አንዱ አላስፈላጊ በዓል ሌላ በጣም አላስፈላጊ የሆነ በዓልን እየፈጠረ መጣ፡፡ ይኸው “All Hallows Eve” የተባለው በዓል ስሙ ሰብሰብ፣ አጠር ተደረገና “Hallow-e’en,” ሲባል ቆይቶ በመጨረሻ “Halloween” እነሆኝ አለ!
ክርስትና ወደ ምዕራብ አውሮጳ ግስጋሴ ሲያደርግ በርካታ የአረማውያንን ሃይማኖቶች በመንገዱ ሲጋፈጥ ቆይቷል፡፡ ያገኛቸውንም “እነዚህን የጣዖት አምልኮዎችን አስወግዱ” በማለት ሕዝቡን ወደ አዲስ እምነት ከማምጣት ይልቅ “እናንተንም ሆነ ባዕድ አምልኳችሁንም እናጠምቃለን (ክርስትና እናነሳለን)” በማለት ጣዖት አምልኮ ወደ ቤ/ክ ሰተት ብሎ እንዲገባ በር ተከፈተ፡፡ የሳምንቱ ቀናት ተቀየሩ፣ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው የባዕድ አምልኮዎች የክርስትና ስም እየተሰጣቸው ወደቤ/ክ ገቡ፡፡ ገና፣ ፋሲካ፣ … በዚሁ መልክ ነው ወደ ቤ/ክ ሰጥመው በመቅረት ክርስቲያናዊ በዓላት ሆነው የቀሩት፡፡
ከላይ የተጠቀሱት ሴልቲኮች ጣዖት አምላኪ አረማውያን ስለነበሩ የመኸር ወራት ተጠናቅቆ የክረምቱን ወራት ከመጀመራቸው በፊት ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ ሰብላቸውን ይሰበስባሉ፣ ክረምቱን ለማለፍ የሚያቅታቸውን እንስሳት ያርዳሉ፣ … ህይወት ዝግ እያለ ይመጣል፤ ቀኑ ያጥራል፤ ሌሊቱ ይረዝማል፤ የእርሻው መሬት እዳሪ ይሆናል፤ … ይህ ሁሉ በሞት፣ በአፅም፣ በራስ ቅል አፅም፣ በጥቁር ቀለም፣ … እየተመሰለ ከመሄድ አልፎ የዘመኑ ሃሎዊን ሲከበር ቀዳሚውን ቦታ የሚይዝ ሆነ፡፡ ከዚሁ በዓል ጋር ተያይዞ የሚደረጉትን ሌሎች አጋንንት የመጎተት፣ መናፍስትን የመጥራት፣ ጥንቆላ፣ ወዘተ ተግባራት በመዘርዘር አላፈላጊ ወደሆነ አጀንዳ ውስጥ ለመግባት አልፈልግም እንጂ ይህንን መሰል እጅግ በርካታ ተግባራት ይፈጸሙ ነበር፡፡
የበዓሉ አመጣጥና ትርጉም ይህ ሆኖ ሳለ እኛ ኢትዮጵያውያን ለመሆኑ ከየትኛው አስተሳሰባችን፣ ባህላችን፣ አኗኗራችን ጋር ተዛምዶ ነው ለዚህ በዓል ይህንን ያህል ክብር በመስጠት የምናከብረው? ወይስ ሥልጣኔ ነው? ምዕራባዊነት? ፈረንጅ ካደረገው ትክክል መሆን አለበት-ነት? በነገራችን ላይ የሰሜን አሜሪካው ገበያ ከዚሁ በዓል 3.3 ቢሊዮን ዶላር ይሰበስባል ተብሎ ይጠበቃል – እኛም ተሳታፊ ነን፡፡
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም “ሥልጣን፤ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካና ምርጫ” በሚለው መጽሐፋቸው በርካታ አጥፊ ባህሎች እንዳሉን ይጠቅሳሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በየቦታው በሥልጣን ላይ የሚገኙ ሰዎች (በመንፈሣዊውም ሆነ በፖለቲካው) የሚሠሩትን ጥፋትና በሕዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በደል እያነሳን እንደምንነጋገርባቸውና እንደምንነቅፍ ይጠቅሳሉ፡፡ በአንጻሩ ግን የራሳችን ጥፋትና በደል እንደማይታየን በዚሁ መጽሐፋቸው ላይ ይናገራሉ፡፡ “በየቤቱ በሚስቶችና ልጆች ላይ የሚደርሰው ጭቆናና ግፍ፤ በየቤቱ ሠራተኞች ያላቸው ሰዎች በሠራተኞቻቸው ላይ የሚፈጽሙት ጭቆናና ግፍ በጥሞና ካየነው ባለሥልጣኖቻችን ከሚያደርሱብን ግፍና ጭቆና ጋር የባህርይ ልዩነት የለውም” ይላሉ፡፡ ይህንን የመሳሰሉ አጥፊ ባህሎች ከእኛ መወገድ እንዳለባቸው በመምከር “በዘመናት ፋይዳቸው የማይለወጥ ለጨዋነትና ለመተማመን መሠረት የሚሆኑትን” ባህሎቻችንን እንድናዳብር ያሳስቡናል፡፡ ለኢትዮጵያውያን “የባህል ምሶሶ” ናቸው የሚሏቸውን አራቱን፡- ክብርና ኩራት፤ ቆራጥነትና ጀግንነት፤ መተዛዘንና መረዳዳት፤ ጨዋነት፣ አደራ አክባሪነትና ሃይማኖተኛነት፤ በመጥቀስ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ልናነበው፣ ልንለማመደው፣ ለልጆቻችን ልናወርሰው የሚገባ ምክር ነው፡፡
ስለሆነም መማር ያለብንና የሌለብንን እንወቅ፤ እንደ መልካም ባህል የሙጥኝ ያልናቸውን – ሰው ምን ይለኛል፣ ይሉኝታ፣ አድመኝነትን፣ ዘረኝነትን፣ ጠባብ ወገንተኝነትን፣ … አጉል ባህሎች አውልቀን በመጣል ግልጽነትን፣ የሌላውን መብት (ከማሰብ ጀምሮ እስከ መናገር) ማክበርን፣ ትህትናን፣ ቅንነትን፣ … በየዕለቱ ህይወታችን፣ በንግግራችን፣ በፓልቶክ ውይይታችን፣ በስብሰባችን፣ በቴሌኮንፍራንሶች፣ ወዘተ እንለማመድ፡፡ ሥልጣን ላይ ባሉት የሰላ ሒስ ስንሰነዝር እኛም በሌሎች ላይ ሥልጣናችንን እንዴት እንደምንለማመድ እንጠይቅ፡፡ ዕብጠትን፣ ከኔ በላይ ላሳር-ነትን እናስወግድ – የባህል ለውጥ እናካሂድ፡፡ ጥራዝ ነጠቅ አንሁን፡፡ ከምዕራቡ ዓለም ብዙ የምንማረው ባህል አለ፡፡ ሃሎዊንና የመሳሰሉት ግን ቢቀሩብን የሚቀርብን ምንም ነገር የለም፡፡
ለጽሁፌ ጥንቅር በዋቢነት የሚከተሉትን ድረገጾች ተጠቅሜያለሁ፡-
http://www.gty.org/Resources/Articles/1126
http://amazingdiscoveries.org/the-origins-of-halloween
It is good observation. But u missed ze truth/reality.U hav 2 read,ask,refere…
bfr u write.10qs
the most ridicules article i ever read. በመሰረቱ, የግንቦት ልደታና እዚህም እዚያም አድባር ሲያከበርና ሲለማመን ለኖረ ኢትዮጵያዊ “Halloween” እንግዳ በአል አይደለም:: ቢሆንስ? የልጆቹንና የራሱን ዜግነት ለመቀየር ቀን አልደርስ እያለዉ እንደ እርጉዝ ሴት ቀን ለሚቆጥር ዥንጉርጉር ኢትዮጵያዊ “Halloween” እንዳያከበር መምከር ዘሩን በድንጋይ ላይ ዘርቶ ምርት ለመሰብሰብ ጆንያዉን ተሸክሞ እንደሚወጣ ጅል ገበሬ ያስቆጥራል:: ባህል አገር አለዉ: ሃለዊን ደግሞ አሜሪካዊ ነዉ: እነዚህ እርሶ ዳያስፖራ ያሏቸው ሰዉችም ኢትዮጵያ አገሬ አይደለችም ያሉና አሜሪካዉ የሆኑ ናቸዉ:: ሰለዚህ ሃለዊንና የእርሶ ዲያስፖራዎች ሁለቱም አሜሪካዊያን ናቸዉ::ስለዚህ እነዚህ ዥንጉርጉር ኢትዮጵያዊያን አገሬ ነሽ ብለዉ በሰዉና በህግ ፉት ለማሉላት አገር ባህል ቢገዙ ምኑ ነዉ የሚያስገርመዉ? ይልቁንስ እኔን የሚያስገርሙኝ ፓስፖርቷን መያዝ ለማይፈልጉ: እዛች አገር ዉስጥ ለሚሆነዉ ክፉም ሆነ ደግ ምንም ግድ የማይሰጣቸዉ ግን ልጆቻቸዉን ከሚኖሩባትና አገሬ ብለዉ ከሚጠሯት አገር ባህልና አስተሳሰብ በመነጠል ልጆቻቸዉን ባህል አልባ ስለሚያደርጉ ዥንጉርጉር ኢትዮጵያዊያን ወላጆች ነዉ:: ደግሞም ኢትዮጵያዉነትና ኦርቶዶክሳዊነትን የማምታታት አባዜ መቼ ድረስ ነዉ የሚዘልቀዉ?:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የአሳማ ስጋን ጨምሮ ብዙ ነገሮችን ይከለክላል: ያማለት ግን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በዚህ ህግ የታሰሩ ናቸዉ ማለት አይደለም:: ጸሃፊዉ ምናልባት የአዲስ አበባ ሱፐር ማርኬቶቼን የመጎብኝት እድል አልገጠማቸዉ ይሆናል እንጂ የአሳማ ስጋ በአዲስ አበባቸን መሸጥ ከጀመረና ኢትዮጵያ ዉስጥ ከተለመዱ ምግቦች መካከል ከሆን ሰንበትበት ብሎላ::
@Tsinat
ብዙ መልካም ነገሮችን አንስተዋል፡፡ ሆኖም እርስዎ በሁለት የከፋፈሏቸው ኢትዮጵያውያን እኮ ሙሉ በሙሉ የአሜሪካውን ወይም የአውሮጳውን ባህል በመያዝ ኢትዮጵያዊ ባህላቸውን እርግፍ አድርገው አልተዉቱም፡፡ ጉዳዩ ፓስፖርት የመያዝና ያለመያዝ ወይም ዜግነት የመቀየርና ያለመቀየርም አይደለም፡፡ ፓስፖርት ሲያዝ ወይም ዜግነት ሲቀየር ቆዳችን አይነጣም ባህላችንም የፈረንጅ አይሆንም፡፡ እርስዎ የሚያቋቸውና ዜግነታቸውን የቀየሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን አማርኛ ወይም የትውልድ ቋንቋቸውን መናገር ያቆሙ ወይም እንጀራ መብላታቸውን የተዉ ወይም የኢትዮጵያውያን ቀን ሲባል በዚያ መገኘታቸውን ያቆሙ ወይም በቤታቸው አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ያሉት ሲኒ፣ ሰሃን፣ የግድግዳ ስዕል፣ የቁልፍ መያዣ፣ … ያስወገዱ አይመስለኝም፡፡ ስለሆነም ጉዳዩ የዜግነት መቀየርና አለመቀየር አይደለም ለማለት ነው፡፡ ሌላው እኔ በጽሁፌ ውስጥ የትም ቦታ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን በስም አልጠራሁም “ክርስትና” ነው ያልኩት ምክንያቱም ክርስቲያኑ ዓለም በሙሉ የሚከተለው መጽሐፍቅዱስ ላይ አሳማ መብላት እንደማይገባ በግልጽ ተቀምጦዋል፡፡ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ ሆነው የአሳማ ሥጋ የሚበሉ በርካታዎች በምዕራቡ ዓለምም ሆነ ኢትዮጵያ (አዲስ አበባ) አሉ፡፡ በተመሳሳይ ደግሞ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሆነው ፈጽሞ የማይበሉ አሉ፡፡ ይልቅ እርስዎ ለምን የኦርቶዶክስን ሃይማኖት ጠቅሰው እኔ እንዳልኩት ለማስመሰል ወይም እኔ ኢትዮጵያዊነትን ከኦርቶዶክስ ጋር እንዳመሳሰልኩት አድርገው እንዳቀረቡት አልገባኝም፡፡ ምናልባት በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሃይማኖቶች ሲባል “ኦርቶዶክስና እስላም” ብቻ ካልሆነ የሚያውቁት፡፡ ለማንኛውም የአሳማ ሥጋንም ሆነ በአጠቃላይ የሚበሉና የማይበሉ እንስሳትን ዝርዝር የሰጠው የኦርቶዶክስ ሰይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ነው – በእስልምናው ደግሞ ቁርዓን ነው፡፡ በነገራችን ላይ አሣማን (እርያን) ማርባት፣ መሸጥም ሆነ መብላት ለኢትዮጵያ አዲስ ነገር አይደለም፡፡ በአዲስ አበባ ቀድሞ ይሸጡበት የነበሩትን ጥቂት ቦታዎችና አሁን ደግሞ የተጨመሩትን ሱፐርማርኬቶች መዘርዘሩ የዚህ ጸሁፍ አላማ ስላልሆነ አልገለጸኩትም እንጂ የዘነጋሁት ጉዳይ አይደለም፡፡ ዋናው የጽሁፉ ዓላማ ሃሎዊን ሥልጣኔ ወይም ዕድገት ወይም ፈረንጅ-ነት አይደለም፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትም እንዳልሆነ ሁሉ፡፡ ከምዕራባውያን የምንወስደውን ባህል እንወቅ፤ ብልህ እንሁን፤ በሃይማኖትም ሆነ በባህል መልክ የያዝናቸውን መልካም ነገሮች ሥልጣኔ እየመሰለን አንተዋቸው፤ መልካሞቹን አጥብቀን እንያዝ፤ መጥፎዎቹን ደግሞ እንተዋቸው፤ ግን በሃሎዊን አንቀይራቸው፡፡ አይረባንም፡፡
አቶ መክብብ መልስ ሊጽፉልኝ ቸኩለዉ መሆን አለበት እንጂ እኔ በሁለት የከፈልኳቸው ኢትዮጵያን የሉም:: እኔም እርሶም ያወራነዉ እርሶ ዺያስፖራ ስላሏቸዉ ግሩቦች ነዉ:: የእኔ መከራከሪያ እርሶ አስፈላጊ ባልሆን ጉዳይ ላይ ጊዜዎትን አጠፉ ነዉ:: ምናልባት የሃለዊንን ታሪክ የሚተርክ ጽሁፍ አግኝተዉ አንብበዉ ሊያካፍሉን ፈልገዉ ካልሆነ በቀር ሃለዊን አገራችን ዉስጥ ከሚዘወተሩት የግንቦት ልደታ, በየዛፍ ስር ከሚደረጉ የአድባር ስረአቶች እምብዛም የራቀ አይደለም:: ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ከዛ ይልቅ የሚያሳስቡ ችግሮች ያሉባቸው ስለሆን ጉልበታችንና እዉቀታችን ተገቢና አንገብጋቢ በሆኑ ጉዳያዮች ላይ ብናዉለዉ ጥሩ ነዉ:: እንደዉ በጠቅላላዉ ስለ ሃለዉንና የበኣሉ መጥፎ ጎን በተመለከታ መናገር ፈልገዉ ከሆነ ደግሞ በጠራ እንግልዝኛዎ ለባለ ባህለኞቹ እባካቹ ይህንን ባህላቹ አስተካክሉ ካልሆን ለመንግስተሰማያት እንቅፋት ይሆንባቹሃል ቢሏቸዉ ጥሩ ይመስለኛል:: ሌላዉ የአሳማ ስጋን ስለመብላትና ስላለመብላት ያነሱት በተመለከተ ክርስቶስ አንድም ቦታ ላይ ይህን ብሉ ያን አትብሉ ብሎ ያስተማረበት የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል እንዳለ አላዉቅም:: ካለም ቢያካፍሉን መልካም ነዉ:: ይልቅስ ያችን አገር ከአይሁድ ስረአት ጋር እግር ተወርች ባንጠፍራት ጥሩ ነዉ:: በነገራችን ላይ ሙስሊሞችና አንዳንድ ሰዎች በግላቸዉ የአሳማ ስጋ የማይበሉበት ምክንያት የአሳማ “ሜታቦሊዝም” በሚገባ አይሰራም ስለሚባል ስለዚህም ስጋዉ ንጹህ አይደለም ተብሎ ስለሚታመን ነዉ:: ሌላዉ አስገራሚው ለኢትዮጵያዊነት እንደ መከራከሪያ ያነሷቸዉ እንድ እንጀራ መብላት እና አማርኛ መናገር… ደግሞ ከመቼ ጀምሮ ነዉ እነዚህ መለኪያዎች የሆኑት? አዲስ አበባ እየኖሩ እንግልዝኛ ቅልጥፍ አድርገው የሚናገሩ ኪሳቸዉ ካልደረቀ በቀር “በርገርና ሃት ዳግ” ምርጫቸዉ የሆነና ያአሜሪካን ባንዲራ እንደ ሻሽ አስረዉ የሚዞሩት የኛዎቹ ባተሌዎች አሜሪካዊ ሊሏቸዉ ነዉ?? ስለ ባህል እያወሩ “ስለዜግነት አይደለም” የሚሉት መከራከሪያስ ምን የሚሉት ነዉ? ሌላዉ የኦርቶዶክስ እምነት የአሳማ ስጋ መብላት እንደሚከለክል የማያዉቁ ከሆነ እኔ ልንገሮት(አደራ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ነዉ ወይም አይደለም ብሎ መከራከር እዚህ ቦታ እንዳይጀምሩ አደራ):: ምናልባት በስህተት በልተዉም ከሆን ለንስሃ አባቶት መንገር አይርሱ:: በመጨረሻ የተዉልኝ ምክር በጣም ግሩም ቢሆንም የእርሶ ጽሁፎት ማእከል ያደረገዉ ዲያስፖራዎችን እንጂ ኢትዮጵያዊያን ስላልሆነ ያምክር ዲያስፖራዎችን አይመለከተም የሚል ግንዛቤ ነዉ ያለኝ:: እኔ በበኩሌ ግን ሰምቼዎታለሁ:: Hopefully this will be my last comment in the topic::
Tsinat – I admire your scholarship and sense of humor. You really made me laugh! ከጨዋታው በተጨማሪ ብዙ ጉዳዮችን አንስተዋል:: ምላሽ እየተሰጣጣን መቀጠል ይቻል ነበር ግን … ምናልባት ወደፊት እንወያይባቸው ይሆናል:: ዕድሜና ጤና ይስጠን! እርስዎም እንዳሉት ላሁኑ በዚሁ ይበቃናል ብዬ እኔም አምናለሁ:: ቸር ይግጠመን::
Yes, Halloween is pagan religion. It is an artistic form of cajoling or traping evil spirit. St. Paul asket, “And what concord hath Christ with Belial? or what part hath he that believeth with an infidel?”
I am not sure wether it would help but I want to share what any Christian Church can learn from the way our immigrant church tried to handle the situation.
In order to avoid such unholly alliance with Satanic calture, our Ethiopian Evangelical Church in Washington, DC approached the issue proactively. In the past few years, we have replaced Halloween by “Halleluja Night”. Now Our kids celebrate october 31 as “Hallelujah Night” on which they praise the Lord and receive different gifts from church members and family. Such an approach would reinforce Christian values and keep them firm in their faith. I hope somebody may benefit from this. Thank you for the article.
I agree with most of the contents of the article. But I am baffled by your mentioning of Easter and Christmas together with the so called ‘Halloween’, if its origin and the acts being done on the day is the way you expressed it (I have to admit I did not hear the word before) as St. Paul asserted that there is no relationship/unity between Christ with Belial by asking: “And what concord hath Christ with Belial? or what part hath he tha believeth with an infidel?” I ask what has Halloween got to do with Christmas and Easter?
@tikursew
Well said – but please don’t be baffled by what I mentioned about Easter and Christmas. When time allows I may write about both. But FYI – a quick search on Google about the origins of Christmas and Easter will tell you how the these holidays were introduced from Paganism and injected into Christianity. Now, don’t tell me that we are just celebrating the birth of Jesus and His resurrection. Let me just handle Christmas here – Do you really believe that Jesus was born on December 25th or January 7? Is that the exact date of his birth? Why this day is picked for celebration? I suspect that you have an inquisitive mind and let me challenge you with this idea – your Bible says that shepherds were out in the field tending (keeping watch) their flock BY NIGHT. (Luke 2:8) How is that possible to happen in winter or rainy season in the middle east (Israel)? A very simple search and logical reasoning will give you tremendous amount of insight to find the Truth.
@መክብብ ማሞ I am not going into the details of whether Jesus was born on either dates you mentioned. As you might have noticed from my comment, my concern is not on the dates on which Jesus Lord was born, I want to challenge the very point you mentioned ”don’t tell me ‘we are just celebrating the birth of Jesus and His resurrection”, rather your mingling of ‘Halloween’, which as you have asserted it to have originated from pagan practice, with Christian practice. I think it is fundamentally wrong. Besides, you did not point out why these days were picked (though it is irrelevant from the vantage point of my stance). Do you think Ethiopians have identity alienated from their religious practice? If not, hopefully you will agree with this, then which part of their identity is compromised by celebrating Halloween? I am afraid you are defeating your rather wonderful argument, which challenges the Diaspora and for that matter for all of us who are predisposed to emulate ‘ferenji’s’ practice without giving it a little scrutiny.
@tikursew
If you are the same person who posted both comments, in your first comment you asked me “what has Halloween got to do with Christmas and Easter?” In my reply I told you how these celebrations are introduced from paganism into Christianity. So to make it simple and understandable to you, the relationship between Halloween and Christmas and Easter is that they all are derived from paganism. In my study of Christian celebrations I have learned that what we are celebrating as “holidays” are all introduced from paganism as Christianity apostatized in the early days of its introduction to make it easy for new converts of pagan believers and their practices. Are we clear on that? If so, my next argument is – the Christian world, including Ethiopians, celebrate Christmas and Easter because they believe those are the days Jesus was born and resurrected from the dead. Even though these days of celebrations has got nothing to do with the birth and death of Christ, (as I said they are derived from paganism), it may be acceptable to celebrate them because they are in one way or another attached to Jesus. But what Halloween has got to do with any of Christian beliefs? Why do you celebrate death while you say that you believe in the LIVING GOD? Unless you take it as a sign of ሥልጣኔ or ፈረንጅነት. There are so many things that we should pick from the Western culture – I have mentioned those in my article. But Halloween has nothing to benefit Ethiopians both spiritually and culturally.