• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ

May 6, 2022 09:35 am by Editor 2 Comments

የአርሲ ዞን ሙኔሣ ወረዳ የእስልምና እምነት ተከታዮች ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ቤተክርስቲያን ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብር እና 20 የቀንድ ከብቶች አሰባስበው አበርክተዋል።

በወረዳው የእስልምና እና የክርስትና እምነት ተከታዮች ለዘመናት በመከባበር እና በመቻቻል በፍቅር አብረው እየኖሩ መሆኑን የሁለቱ ሃይማኖቶች ተከታዮች ገልጸዋል።

የሁለቱም እምነት ተከታዮች አንዳቸው ለሌኛው በየተራ መስጂድ እና ቤተክርስቲያን ተባብረው እያሠሩ በክፉ እና በደጉ አብረው ቆመው እስከ አሁን ደርሰዋል።

የሁለቱ እምነት ተከታዮች አንዱ ለአንዱ ቤተ እምነት መሥራት የቆየ ከአባቶቻችን የወረስነው እሴት ስለሆነ እኛም ይህንኑ እያስቀጠልን ነው ብለዋል።

የሥርዓት ለውጥም ሆነ የፖለቲካ ችግር ሀገሪቷን በገጠማት ወቅት ምንም ዓይነት የሃይማኖት ግጭት በወረዳው ተከስቶ አያውቅም ያሉት ነዋሪዎቹ፣ በወራዳችን ሃይማኖት የመቻቻል እና የአብሮነት ምንጭ እንጂ የግጭት መንሥኤ ሆኖ አያውቅም ብለዋል።

የክርስትና እምነት ተከታዮች በበኩላቸው የሙስሊም ማኅበረሰብ ላደረጉላቸው ድጋፍ አመስግነው፣ ይህን የቆየ የአባቶቻችንን እሴት አጠናክረን እናስቀጥላለን ብለዋል።

የሙኔሣ ወረዳ አስተዳዳር አቶ አማን ሻቁሮ ደግሞ በወረዳዋ መቀመጫ ቀርሣ ከተማ የመጀመሪያው መስጅድ የተሠራው በክርስትና እምናት ተከታይ የሀገር ሽማግሌ ነበር ብለዋል።

የከተማው ትልቁ መስጅድ መርካዝ የሚባለውም በክርስትና እምነት ተከታዮች ትብብር የተሠራ ነው።

ይህ በየተራ ቤተ እምነት አንዱ ለአንዱ የመሥራት ባህልም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ማለታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: Arusi, christianity, Islam in Ethiopia

Reader Interactions

Comments

  1. Semaneh T. Jemere says

    May 9, 2022 05:31 pm at 5:31 pm

    ምስጋና ለጎልጉል ድረ ገጽ አዛጋጆች በሙሉ፤

    ከሁሉ በማስቀደም በአንድ ቀን ቢዘገይም እንኳን ለዓልም የሴቶች ቀን አደረሳችሁ። ጨርሶ ከሚቀር ዘግይቶ መደረጉ ክፋት የለውም ይላል እንግሊዝ (better late than never)።

    ከሃገር ቤት መልካም ዜና መስማት እጅግ በናፈቀን ስዓት አልፎ አልፎ መልካም ስንሰማ የምንፈነድቅ ብዙዎች ነን። በተለይ እውነትም ሆነ ሃሰት እንደ ቆሎ የሚዘገንበት ዮቱብ እንዳሸን የፈሉት ሁሉ ግራ ተጋብተው ጋር በተጋባንበት ጊዜ ጎልጉል የተባለው የመረጃ መድረክ በድረ ገጹ ላይ የሚከተሉትን መልካም ዜናዎች አብስሮልናል።

    አንደኛው ዜና “ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ ” በአንድ ወጣት ተማሪ የተገኘውን የፈጠራ ግኝት በዓለም የእናቶች ቀን ሲነግረን እጅግ አስደስቶናል። ይህ ፈጠራ የእናቶችን ድካም ብቻ ሳይሆን የሚቀንሰው፤ የደን መጨፍጨፍን የቀንሳል፤ የእናቶችን ጤንነት ያሻሽላል፤ ባህላዊ አሰራርን ያዘምናልና ወደ ተግባር የሚውልበትን ቀንና ጊዜ ብታሳውቁን ደስ ይላል።

    የህዳሴው ግድብ ሃይል ማመንጨት በጀመረበት ጊዜ በመምጣቱ ፈጠራውን ወቅታዊ ያደርገዋል። በተለይ እኛ በዳያስፖራ የምንገኝ ሰዎች ማሽኑን እየገዛን አነስተኛ ገቢ ላላቸው እናቶች በስፖንሰርሽፕ ይሁን በስጦታ መልከ ገዝተን ማበርከት የሚቻል ይመስለኛልና አጣርታችሁ አሳውቁን። ሌላው ይህ ወጣት ዓላማውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚፈልገው እርዳታ ካለ ብታሳውቁ ብዙ መርዳት የሚፈልጉ ሰዎችና ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ።

    ይህ ፈጠራ በቀላሉ እንዳይታለፍና የአንድ ሳምንት ዜና ማሞቂያ ሆኖ እንዳይቀር አስፈላጊው ሁሉ ጥንቃቄ ይደረግበት። እንደዚህ ጻሐፊ እይታ ከሆነ የወጣቱ የምርምር ውጤት በመንግስት ደረጃ እውቅና ቢቸረው መልካም ነው። አነስታይን ፈጠራውን ወደ ተግባር በመቀየር ነው ዓለምን የቀየረው። የዚህ ወጣት ፈጠራም እንዲሁ ከተበረታታ ውጤቱና ጥቅሙ ለወጣቱ፤ ለሕዝባችንና ለሃገር ነውና እንደግፈው። እራስን በራስ የመቻል ማሳያም ነውና በቸልታ መታለፍ የለበትም።
    ኢትዮጵያ ለማያስፈልግ ሰው ሰራሽ ጸጉር ከውጪ ለማስገባት የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ሲታሰብ ያስደንግጣል። ይህን ከንቱ ወጪ ወደዚህ ፈጠራ አዙራ ብታስፋፋውና በተግባር ብታውለው ጠቀሜታው ለሃገሪቱ እንጅ ለማንም አይደለምና ይታሰብበት።

    በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ድረገጻችሁ”በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ ” የሚል ዜና አስነብቦናል።

    እኛ ስለሃገራችን በየእለቱ የምንጨነቅ በተለይ በውጭ ሃገር ለምንገኝ ዳያስፖራዎች ትልቅ ዜና በመሆኑ የዚህ ኣይነቱን ዜናና መረጃ ያብዛልን። ኢትዮጵያችን በበቂ ደምታለች። ሳያስፈልግ ተስቃይታለች። በሚአሳዝን ሁኔታ ተፈትናለች። ዛሬ ታመመች፤ ነገ ፈረሰች እያልን የምጨነቅ ብዙዎች ነን። ስለዚህ የኢትዮጵያንና የኢትዮጵያዊያንን መከራ እንቀንሰው።

    በተለይ የዩ ክሬን ሁኔታ ያየ፤ የታይዋንን ጭንቀት በየቀኑ የሰማ፤ የሶሪያን ቀውስና ውድምት በዓይኑ ያየ ትምህርት መውስድና ስህተትን ማስተካከል አያቅተውም። ሌላው አማራጭ የውድመትና የጥፋት ነውና ሁላችንም አድብ እንግዛ።
    እስላምናና ክርስቲያን ተቻችሎ በሚኖርባት ኢትዮጵያ እንዴት የሃይማኖት ግጭትና ቀውስ ሃገራችንን ይፈትናት። እውነት ለመናገር ይህን ቀውስ፤ ችግርና ፈተና በሕዝባችንና በሃገራችን ላይ የሚአደርሱት እጅግ ትቂቶች ናቸው። ከ92% በላይ የሚሆነው ሕዝብ ቀውስን፤ የጎሳና የሃይማኖት ጠብንና ትርምስን እንደማይፈልገው ያለፉት ሃምሳ ዓመታት የፖለቲካ ጉዟችን ዋቢ ምስክሮች ናቸው።

    ለማንናውም እንዚህን ሁለትት ጥሩ ዜናዎች ያጋርን ጎልጉል ድሕረ ገጽ ሰፊ ምስጋን ይድረሰው። ለወድፊቱም እንደዚህ ሕዝብን ሊአቀራርቡ የሚችሉ የመልካም ዜናዎችን አፈላልጋችሁ እንደምታሰሙን ተስፋ በምድረግ ለአሁን ፈጣሪ አብዝቶ ይስጥልን።

    ከአክብሮት ምስጋን ጋር፤
    ሰማነህ ታምራት ጀመረ
    ኦታዋ ካናዳ
    ሰኞ፤ ሚያዝያ1 ቀን 2014

    Reply
    • Editor says

      May 10, 2022 11:46 pm at 11:46 pm

      ውድ ሰማነህ ታምራት ጀመረ

      በቅድሚያ ጊዜዎን ወስደው ይህንን የመሰለ ምላሽ ስለላኩልን ከልብ እናመሰግናለን። እርስዎ እንዳሉትም ሁለቱም የዜና ዘገባዎች በጣም ጠቃሚና የሚያስደስቱ ናቸው።

      የሚያሳዝነው እጅግ መልካም እና የሚያስደስት እሴት ያላት አገራችን ብዙ ሊወራላት የሚገባ ነገር እያላት ጠላቶቻችን በሚሰጡን አጀንዳ እርስበርስ እየተናቆርን መጥፊችንን በግድ የምንደግስ መሆናችን ያሳዝናል። ሆኖ ደግሞ እንደ እርስዎ ያለ እሾኹን ብቻ ሳይሆን አበባውንም የሚያይ አንድ ሰው መገኘቱ እጅግ ተስፋ የሚሰጥ ነው።

      በእርግጥ እርስዎ በዚህ ልክ ጻፉልን እንጂ በዝምታ ደግሞ ያገራቸውን ሁኔታ የሚከታተሉና መልካሟን የሚመኙ እንደ እምነታቸው የሚጸልዩ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ እናቶች፣ አባቶች፣ እህቶችና ወንድሞች አሏት። ለዚህ ነው ኢትዮጵያ የተዓምር አገር የሆነችው።

      ለመልካሙ አስተያየትዎ በድጋሚ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

      አርታኢ

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሤራ አክሻፊው ጎንደር ለሦስተኛ ጊዜ ታሪክ ሠራ May 10, 2023 09:25 am
  • ማር በከፍተኛ ደረጃ የኮንትሮባንድ ሰለባ ሆኗል May 9, 2023 09:24 am
  • ኦነግ በኦሮሚያ ሪፈረንደም እንዲካሄድ መጠየቁ ለሰላም ንግግሩ ዕንቅፋት ሆነ May 4, 2023 01:12 am
  • መረጃ ቲቪ ያጋራው አሳሳች መረጃ May 2, 2023 12:37 pm
  • “ከፈጣሪ በታች መከላከያ የሁላችን ዋስ ጠበቃ ነው፤ ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን” April 13, 2023 10:19 am
  • በትግራይ የ”ልጆቻችን የት ናቸው?” ጥያቄ እየተሰማ ነው April 13, 2023 08:56 am
  • በትህነግ የፈረሰው የአክሱም ኤርፖርት ያስከተለው ዘርፈብዙ ኪሣራ April 13, 2023 03:21 am
  • “የከተማው ነዋሪ በመሰላቸቱ ተፈናቃዮች ከፍተኛ የምግብ ችግር” ገጥሟቸዋል April 12, 2023 09:23 am
  • ከዕድሜ ልክ እስከ 20 ዓመት ቅጣት ተበይኖባቸዋል April 11, 2023 02:58 pm
  • የኡጋንዳ የክልሎች ሚኒስትር በቆርቆሮ ሌብነት ተጠርጥረው ታሰሩ April 10, 2023 03:59 pm
  • ታከለ ከተነሳ በኋላ የመዐድን ሌቦች እየተያዙ ነው April 6, 2023 02:53 pm
  • አገር ለማተራመስ ያለመ የምሁራን፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አክቲቪስቶች ህቡዕ ቡድን ተያዘ April 4, 2023 10:07 am
  • በ10 ዓመት ውስጥ ከ44 ቢሊየን ዶላር በላይ ሸሽቷል April 4, 2023 09:26 am
  • አየር ጨብጦ አሁን ያለውን መንግሥት ከሥልጣን ልቀቁ አይሆንም March 29, 2023 09:47 am
  • ሦስት ትውልድ የበላ የሐሰት ትርክት! March 23, 2023 11:59 am
  • “ሽብርተኝነቱን ማንሳቱ በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለማቋቋም ይረዳል” – ዶ/ር ጌዲዮን March 22, 2023 05:05 pm
  • አስነዋሪ ተግባር ሲፈጸምባቸው የነበሩ የምሽት ክለቦች ተዘጉ March 22, 2023 12:57 pm
  • ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ March 22, 2023 12:06 pm
  • የኡጋንዳ ፓርላማ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን በእስር የሚያስቀጣ ወንጀል የሚያደርግ ረቂቅ ሕግ አጸደቀ March 22, 2023 12:44 am
  • በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ March 21, 2023 11:01 pm
  • በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ March 19, 2023 03:45 am
  • ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው March 19, 2023 02:44 am
  • እየተገባደደ ያለው የምስራቅ አፍሪቃ የትራንስፖርት ኮሪደርና ለውጥ የናፈቃት ኤርትራ March 15, 2023 04:44 pm
  • በባዶ እግር በሮም አበበን ለመድገም March 15, 2023 01:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule