የቤተ-ክርስቲያን መስኮት ሰብረው ከሙዳየ ምፅዋት ገንዘብ ሰርቀው ሊሰወሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ። በጉራጌ ዞን በሶዶ ወረዳ ጊሚሴ ቀበሌ ቤተክርስቲያን ሰብረው ገንዘብ የዘረፉ ግለሰቦች በሁለት ወንድማማች እና በአከባቢው ህብረተሰብ ትብብር ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጋቸውን ወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። ትዛዙ ፍቅሬና አብርሀም ሞላ የተባሉት ተጠርጣሪዎቹ መድሀኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን መስኮት ሰብረው ከሙዳየ ምፅዋት ውስጥ ገንዘብ ሰርቀው ሊሰወሩ ሲሉ በመቅቡል መሀመድ፣ በሀይሩ መሀመድ እና በአካባቢው ማህበረሰብ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ ተይዘው ለህግ አካል እንዲቀርቡ መደረጉን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አለማየሁ ደነቀ ተናግረዋል። ወንጀለኛ አብርሀም ሞላ ከዚህ በፊትም ነጌሳ ስላሴ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ የተቀመጠ ጤፍ በመዝረፍ ክስ ቢመሰረትበትም እድሜው አልደረሰም … [Read more...] about ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ
Archives for May 2022
ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ
አርሶ አደር ዳንኤል ሾጦጦ ይባላሉ፤ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ ወረዳ የሺጋዶ ቀበሌ ነዋሪ ናቸዉ። ባላቸው አነስተኛ መሬት ላይ ቋሚና ጊዜያዊ ሰብሎችን በማምረት ይተዳደራሉ።አርሶ አደሩ ማሳቸውን አቋርጣ የሚታልፍ አነስተኛ ወንዝ በመጥለፍ ባዘጋጁዋቸዉ ገንዳዎች ዓሣ የማልማት ሀሳብ ይዘዉ ወደ ተግባር ገቡ፤ በእነዚህ የዉኃ ገንዳዎች 6 ሺህ የዓሳ ጫጩቶችን ወደማርባት ተሸጋገሩ።በአሁኑ ወቅት የሚያረቡትን የዓሣ ጫጬት ብዛት እስከ 80 ሺህ ማድረስ ችለዋል። የገንዳዎቹንም ቁጥር ወደ 3 አሳድገዋል። (ቲክቫህ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ
ተስፋቢሱ ቴድሮስ
በዕውቀት ማነስ የሚሰቃየውና ሐኪም ሳይሆን የዓለምን የጤና መሥሪያቤት እየመራ ያለው ቴድሮስ አድሃኖም ተስፋው የተበተነ ይመስላል። በነ ቢል ጌትስና ወዳጆቻቸው ድጋፍ ያለብቃት አናት ላይ ላይ የተቀመጠው ቴድሮሰ አድሃኖም አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፈው የተቀጠረበትን መሥሪያቤት በማገልገል ሳይሆን እንደ ፍንዳታ ስልኩ ላይ ተጥዶ ማኅበራዊ ሚዲያውን በማሰስ ነው። ነጋጠባ ትግራይ ትሰርዕ እያለ የሚፖስተው ቴድሮስ ከዱሮ የተጠናወተው ሰካራምነት አሁን ብሶበታል። በድጋሚ እንዳይመረጥ ዘመቻ ተከፍቶበት የነበረ ቢሆንም ጌቶቹ በቀጣይ ዓመታት የሚጠርግላቸው ቆሻሻ ስላለ አርፈህ ቀጥል ብለውታል። እርሱም ተስፋ ቆርጦ በመጠጥ መደንዘዙን ቀጥሎበታል። በትግራይ ከተደረገው ውጊያ በፊት ጀምሮ ትግራይን ልክ እንደ አገር በማስመሰል በማኅበራዊ ሚዲያ ሲታትር የነበረው ቴድሮስ አንዳንዴ ቀጥተኛ ሌሎች … [Read more...] about ተስፋቢሱ ቴድሮስ