በዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው እና በቀን እስከ 35 ወይም በሳምንት ለ100 ያህል ዜጎች አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል። ማዕከሉ በዳግማዊ ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል ዓለም ዐቀፍ ደረጃውን ባሟላው አዲስ ህንፃ ላይ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ነው የተገለፀው። በኩላሊት ህመም ለሚሰቃዩ ወገኖች ትልቅ እፎይታ ይሰጣል የተባለለት ማዕከሉ የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች በነፃ አገልግሎቱን በመስጠት ተስፋ እንደሚሆንም ተጠቁሟል። ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ማዕከሉ በዛሬ ዕለት (ሰኞ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ይመረቃል። (አዲስ ሚዲያ) ማስተካከያ፤ ይህ ዜና በተለጠፈበት ቀን እጥበት ማዕከሉ በሳምንት … [Read more...] about በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ
Archives for May 2022
የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ለ69ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን “የጥቁር አንበሳ” ዕጩ መኮንኖችን አስመረቀ። ተመራቂዎቹ “የጥቁር አንበሳ” መባላቸው በምዕራባዊያንና በውስጡ ነበሩ በተባሉ “ካሃዲዎች” የተበተነውን ታላቁን የኢትዮጵያ መከላከያ ያስታወሰ መሆኑ ልዩ ስሜት የሚሰጥ እንደሆነ ምርቃቱን ተከትሎ አስተያየት ተሰጥቷል። “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም በሚል ቁጭት ነው ኢትዮጵያን የሚመጥን የመከላከያ ኃይል ለመገንባት እየሠራን ያለነው” በማለት የጦር ኃይሎች ም/ጠ/ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ በተናገሩ ማግስት፣ አዳዲስ መኮኖች መመረቃቸው፣ ጀነራሉ በንግግራቸው የሚገነባው ኢትዮጵያን የሚመስልና የሚመጥን ሰራዊት ዘመናዊና ቴክኖሎጂን የተላበሰ፣ በምሁራን የተገነባ እንደሚሆን ካመላከቱት ጋር ተያያዥ ሆኗል። ተመራቂዎቹ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው፣ በራሳቸው ተነሳሽነት ከሲቪል … [Read more...] about የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ
“ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው
“ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!" በሚል ቁጭት ነው ኢትዮጵያን የሚመጥን የመከላከያ ኃይል ለመገንባት እየሠራን ያለነው። ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ። እጅግ በሚያስደንቅ ብቃት፣ ክህሎት፣ ቴክኖሎጂ፣ በምድር፣ በባሕር፣ በአየር እየተገነባ ያለውና በአሁኑ ጊዜ አፍ በሚያስይዝ ቁመና ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የት እንደደረሰ በቅርቡ የሚታይ ሐቅ ይሆናል። ይህም ለዜጎቿ ኩራት፣ ለአፍሪካም ክብር ነው። የውስጥና የውጪ ጠላቶች ይህንን ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው አገራችንን ለማፍረስ እየሠሩ ያሉት። ሕልማቸው ዕውን ባይሆንም ከውስጥ የሚሰማቸውና የሚምናቸው እስካለ መጠነኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ። ነገርግን የትም ቢንፈራገጡ ኢትዮጵያን ማፍረስ አይደለም ለማፍረስ ማሰብ አይችሉም። ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው
“ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ
በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አዘጋጅነት “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መሪ ሃሳብ ለክልሉ አርሶ አደሮች የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች ርክክብ መርሐ ግብር ተካሂዷል። የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች በክልሉ የቴክኖሎጂ አቅርቦት ውስንነትን ለመቅረፍና የግብርና ሥራን በዘመናዊ መንገድ በመከወን ምርታማነትን ለማሳደግ ያግዛሉ ተብሏል። በተካሄደው ርክክብ÷ ትራክተር፣ ኮምባይነር፣ አነስተኛ መውቂያ መሳሪያዎች እንዲሁም የውሃ መሳቢያ ፓምፖች እንደሚገኙበትም ነው የተመላከተው። በዛሬው ዕለት 136 ትራክተሮች በክልሉ ግብርና ቢሮ በኩል ለስርጭት የቀረቡ ሲሆን÷ ከጥር ወር ጀምሮም 324 ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች ማስተላለፍ መቻሉ በመርሐ ግብሩ ተገልጿል። በርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ÷ ያለንን የግብርና … [Read more...] about “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ
ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል
ራሱን ኢትዮ 360 ብሎ ስለሚጠራው ቡድን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በመረጃ ማንነቱን እና ለማን እንደሚሠራ አጋልጠናል። የትህነግ ተከፋይ ቡድን መሆኑን ከሁለት ዓመት በፊት በማስረጃ ተናግረናል። ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች ይመልከቱ። “ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳየበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረውየ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ በዚህ ቡድን ውስጥ ያሉት ግለሰቦች ሲሻቸው መንፈሣዊ ሆነው በመቅረብ የሰውን ቀልብ ለመሳብ ይሞክራሉ። ሃብታሙ አያሌው አንዱ ተጠቃሽ ሲሆን ዘመድኩን በቀለ … [Read more...] about ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል
“እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ጭልጋ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ፈለቀ የ55 ዓመት ጎልማሳ ሲሆኑ በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚነሱት ግጭቶች ተረጋግተው እንዳይኖሩ ሲያደርጓቸው እንደቆዩ ይገልጻሉ። በሌሎች ጊዜያት ከተነሱት ግጭቶች በላይ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 2013 ዓ.ም የተነሳው ግጭት አቶ ሀብታሙን ከመኖሪያ ቀያቸው እንዲፈናቀሉ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል። ሚያዚያ 2013 ዓ.ም ግጭት ተነስቶ ንብረት ሲወድምና የሰው ህይወት ሲጠፋ አቶ ሀብታሙ አካባቢውን ለቀው ለመሄድ መነሳታቸውን ይናገራሉ። አቶ ሀብታሙ የአማራ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ ቤት ንብረታቸውን ለቅማንት ብሔረሰብ ተወላጁ ጓደኛቸው አስረክበው ወደ ጎንደር ከተማ እንደመጡ ለአል ዐይን አማርኛ ገልጸዋል። ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በተደጋጋሚ ሲነሳ የነበረው ግጭት በማንነት ምክንያት ሆኖ ሳለ የአማራ ብሔር ተወላጅ … [Read more...] about “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ
ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን
ትግራይ የሸመቀው የወንበዴና አሸባሪ ቡድን ረቡዕ ስብሰባ አካሄድኩ ብሎ በሚዘውራቸው ሚዲያ ዘግቦ ነበር። በስብሰባው ላይ የ4 ወር የሥራ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን ደብረጽዮን ትግራይን ራስገዝ አገር እናደርጋለን ብሏል። “ተልዕኳችን” ሲል አገርን የማፍረስ ዕቅዱን የተናገረው ደብረጽዮን ዓላማችን ትግራይን አገር ማድረግ ነው ብሏል። ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሰበሰባቸው ደካሞች እጅግ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ ሲናገር “የምንገኝበት ምዕራፍ በውይይት እና በጦርነት ሊቋጭ የሚችልበት ሁኔታ የሰፋ ነው” ብሏል። ደብረጽዮን አገር አደርጋታለሁ በሚላት ትግራይ እጅግ በርካታው ሕዝብ አጥንትን ዘልቆ በሚገባ ችጋር ውስጥ የተሸማቀቀ ሲሆን ሠርቶ የሚያበላው ልጆቹን ለጦርነት ገብሯል፤ ለዐቅመ ሔዋን ያልደረሱ ሴቶች ልጆቹን ደግሞ ለሴተኛ አዳሪነት እየሸጠ ነው። ደብረጽዮንና ወንበዴ ጓደኞቹ ይቺን ትግራይ … [Read more...] about ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን
“ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች”
በሙያቸው ብቃት እና በስነ ምግባራቸው በሠራዊታችንም ሆነ በሰቪል ማህበረሰቡ ዘንድ ተመስግነው የማያልፍ ታሪክን ሰርተው ህዝብና ሀገርን አኩርተዋል። በዋሉበት አውድ ሁሉ በፅናትና በጀግንነት ከጦር ሠራዊቱ ጋር ፊት ለፊት በመሰለፍ ሠራዊቱን አክመዋል ባስ ሲል ደግሞ ጠመንጃቸውን አንስተው ጠላትን እያፍረከረኩ ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን ድርብ ኃላፊነት በጀግንነት ተወጥተዋል። ሰራዊቱ ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር በሚል ቁልፍ እሴት በተግባር ተቃኝቶ በህዝብና በሀገር የመጣን ጠላት ሲፋለም መተከያ የሌላትን ህይወት ለመታደግ እና ከደረሠበት ጉዳት ድኖ ወደ ግንባር እንዲመለስ በማድረግ ጀብዱ ፈፅመዋል ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ዶክተሮች። ሌ/ኮ ዶክተር ጌታሁን የሻነው እና ሻ/ል ዶክተር ውበት ደምሴ ይባላሉ። ሻ/ል ዶክተር ውበት ደምሴ የምዕራብ ዕዝ ተንቀሳቃሽ ሆስፒታል ሜዲካል … [Read more...] about “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች”
ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ
በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ ለአሸባሪው ሕወሀት ቡድን ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር መያዙን የአስተዳደሩ ሰላምና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። "ከአሸባሪው ሕወሀት ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 20 ሰርጎ ገቦች” በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ተናግረዋል። የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ አቶ ሸጌ መንግስቴ ከግንቦት 12 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በተደረገ የተቀናጀ ጥረትም ለሕወሀት የሽብር ቡድን ሊደርስ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር መያዙን ገልጸዋል። ገንዘቡን ለሽብር ቡድኑ ሊያደርሱ የነበሩ 20 ተጠርጣሪዎች በጸጥታ ኀይሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን አመልክተዋል። በሌላ በኩል “ከአሸባሪው ሕወሓት ቡድን የጥፋት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 20 ሰርጎ ገቦች” በከተማ አስተዳደሩ በቁጥጥር ስር … [Read more...] about ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ
የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች
የገጠመን ጠላት ጦርነትን እንደኦክስጅን የሚቆጥር ያለጦርነት መሽቶ የማይነጋለት ደመ-ቀዝቃዛ ኃይል ነው። በፍፁም የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ያለው ወያኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ፣ ቀጠናውን ለማተራመስ እረፍት የለውም፡፡ ምክንያቱም በአንድ በኩል የት*ግሬን ወጣት ሊመግበው የሚችለው በዘራፊነት አሰማርቶ ብቻ ነውና፡፡ የወያኔ ሠራዊት ዘራፊና ወሮ-በላ (pillager) ሠራዊት ነው፡፡ ወሮ-በላ ሠራዊት ደግሞ ዓይኑን ጨፍኖ ለመዝረፍ የሚመጣ ኃይል ነው፡፡ መዝረፍ፣ ማውደም፣... ግብሩ ነው። ቆቦ፣ ወልድያ፣ ሐይቅ፣ ደሴ፣ ኮምበልቻ፣ ከሚሴ፣ ሸዋሮቢት፣ ንፋስ መውጫ፣... ዐቢይ ማሳያ ሆነው ይቀርባሉ። ከሐምሌ-ታህሳስ በዘለቀ የወሎ፣ ከፊል ሸዋና ጎንደር የጦር ወረራው ከዶሮ እንቁላል እስከ ፋብሪካ ማሽነሪ፤ ከአልባሳት እስከ ቀንድ ከብት፤ ከማህበራዊ የልማት ተቋማት እስከ እርሻ … [Read more...] about የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች