በሴቶች ጭፈራ ደምቆ በወንዶች የሚታጀበው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራን ለማስተዋወቅ የሁለት ቀን ፌስቲቫል በደሴ ከተማ ተካሂዷል። እራሷን ተሰርታ ወለባ ስጋለች፣ እንሶስላ ሙቃ ሎሚ ጨብጣለች፣ ያች ያገሬ ልጅ እሷዉ ትሆናለች። ሲሉ ጨዋታውን ደመቅ ያደርጉታል የወሎ ወይዛዝርት። ታዲያ በዚህ ጭፈራ ጊዜ ወንዶቹ ሴቶቹን ተቀላቅለው ጭፈራውን ደመቅ ያደርጉታል። አኾላሌ በሃይማኖታዊና ሃይማኖታዊ ባልሆኑ ክብረ በዓላት የሚከናወን ብዙ ጊዜ ጥር ወር ላይ በአርሶ አደሩ የዕረፍት ወቅት፣ በመተጫጫና ጋብቻ እንዲሁም የመዋቢያ ጊዜ የሚከናወን ባህላዊ ጨዋታ ነው። በአብዛኛው በወሎ በተለይም በተውለደሬ የሚከወነው ተዉኔት አዘል ባህላዊ የወጣቶች ጭፈራ ሃይማኖት ሳይለይ በክርስትናም በእስልምና ተከታዮችም ይካሄዳል። አሆላሌ ባህላዊ ጨዋታ የራሱ የኾነ የመከወኛ አጋጣሚዎች እና ወቅቶችም … [Read more...] about ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ