“ተላላኪ መንግስት አይኖርም” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለበርካታ ዓመታት የነጮ ተላላኪ በመሆን ያገለገለው እና ሞት እንደ ቡሽ ክዳን ያስፈነጠረው መለስ ዜናዊ በግፍ ኢትዮጵያን በገዛበትና ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ፈጽሞ ባልተሰማ ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለአገራቸው ያላቸውን ስሜት በግልጽ ተናግረዋል። ኢትዮጵያን ተቀጥሮ እንደሚያስተዳድራት መሪ “አገሪቱ” እያለ ሲጠራት ከኖረው መለስ ዜናዊ በኋላ ፍጹም በተጻረረና ልብን በሚያሞቅ የአገር ስሜትና ወኔ ከእንግዲህ በኢትዮያ ተላላኪ መንግሥት እንደማይኖር ነው ለሕዝባቸው በፓርላማው ውይይት የተናገሩት። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ “በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አይደረግም” ሲሉ ተጽዕኖ ለማሳደር ለሚሞክሩ አካላት ተናግረዋል። ዛሬ (ማክሰኞ) ለፓርላማ ባቀረቡት ንግግር … [Read more...] about “በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አልደራደርም”
Archives for March 2021
“ከዚህ በኋላ ህወሓት ማለት በነፋስ የተበተነ ዱቄት ነው” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
ዛሬ (ማክሰኞ) በተካሄደው 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሰጡት ማብራሪያ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፤ የኢኮኖሚው አጠቃላይ ገጽታ፤ የፍኖተ ብልጽግና እቅዳችን ያለፉትን 3 አመታት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፤የአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም መሰረታዊ አጀንዳዎቻችንየብድር ጫና መቀነስተጀምረው የቀሩ በርካታ ፕሮጀክቶች በፈጠነ መንገድ ማጠናቀቅየወጪ ንግዱን ማሻሻልና ማሳደግገቢን ማሻሻልገበያን ማረጋጋትና የዕድገት ቀጣይነትን ማረጋገጥ፤የህዳሴ ግድብ በነበረበት ችግር ምክንያት የአገር ኢኮኖሚ እግሩ ተፈትቶ መሄድ እንዳይቻል አድርጎ ነበር፤የወጪ ንግድም ትልቅ ችግር ውስጥ ነበር፤ ባለፈው አመት ለመጀመሪያ ገፊዜ መሻሻል አሳይቷል፤እነዚህን አጀንዳ ስንቀርጽ ኮቪድ … [Read more...] about “ከዚህ በኋላ ህወሓት ማለት በነፋስ የተበተነ ዱቄት ነው” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ
እነ ስብሃት ነጋ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆነ
እነ አቶ ስብሃት ነጋ ጉዳያችን በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ይታይልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበው ነበር። ይህን አቤቱታ ያቀረቡት ዛሬ (ማክሰኞ) በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው። በችሎት የተገኙት የጠቅላይ አቃቤ ህግ ቡድን በበኩሉላቸው የፌዴራል መንግስትን ስልጣን ለመጣል በሚል የሽብር አዋጁን በመተላለፍ በመላው ሀገሪቱ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በመጥቀስ ተጠርጣሪዎቹ መቀሌ ሆነው በሰጡት ትዕዛዝ ባህርዳር እና ጎንደርን በሮኬት ማስደብደባቸው አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል። በተጨማሪም ተከሳሾቹ ስልጣን ተከፋፍለው በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸመ ወንጀል ነው ያለው አቃቤ ህግ ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ሆነው አዲስ አባባ ቁጭ ብለው ሲፈጽሙ የነበረው ወንጀል አንድ ቦታ አለመሆኑን ማመላከቻ ነው ብሏል በምላሹ። ይህ … [Read more...] about እነ ስብሃት ነጋ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆነ
በርግጥ ኢትዮጵያ ዝናብ አዝንባለች?
በዛሬው (ማክሰኞ) የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈጥሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው፤ ዓለም ላይ ያላቸውን ደመናን ወደዝናብ የቀየሩ አገራት ጥቂት አገራት ናቸው፤ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ አየዋለሁ ብዬ ከምቀናባቸው ነገሮች አንዱ ይሄ የተከማቸ ደመና በተመረጠ ሁኔታ ማዝናብ መቻልን ነው፤ አሁን ኢትዮጵያ ይሄንን አቅም ገንብታለች፤ ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው፤ በግልጽ በሚቀጥሉት ሳምንታት እናስመርቀዋልን፤ ወይንም እናስጀምረዋለን፤ ኢትዮጵያ ደመናዋን ተጠቅማ ዝናብ ማዝነብ ችላለች” ብለው ነበር። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል። ይህን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ተጨባጭ ሳይንስ ነው? የብሄራዊ … [Read more...] about በርግጥ ኢትዮጵያ ዝናብ አዝንባለች?
አሜሪካ በሴናተሯ አማካይነት “ለቅሶ” ደረሰች
የፕሬዚዳንት ባይደን የቅርብ ወዳጅ የሆኑት ሴናተር ክሪስቶፈር ኩንስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ለማነጋግር አዲስ አበባ መጥተው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን አነጋግረዋል። የኋይት ሐውስ የፕሬዚዳንቱ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ጄክ ሱለቫን ባወጡት አጭር መግለጫ እንዳሰፈሩት በትግራይ አለ በሚባለው የሰብዓዊ መብት ገረጣና ሰብዓዊ ቀውስ ባይደን ያላቸውን ትልቅ ጭንቀት ሴናተር ኩንስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እንደሚያቀርቡ ነበር የጠቆሙት። በተጨማሪም ሁኔታው የአፍሪካ ቀንድን አለመረጋጋት ውስጥ ሊከተው የሚችል በመሆኑ ሴናተሩ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር እንደሚመክሩበት አማካሪ በመግለጫቸው አመልክተው እንደነበር ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በተገኙበት አቶ ደመቀ ተቀብለው አስፈላጊው ማብራሪያ እንደተሰጣቸው የውጭ ጉዳይ … [Read more...] about አሜሪካ በሴናተሯ አማካይነት “ለቅሶ” ደረሰች
ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ
ቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጃል መሮ በሚል ስም የሚታወቀውን ሽፍታ ሽፋን ሲሰጠው ስለምንነቱና በትክክልም እሱ ስለመሆኑ መረጃ ሰጥቶ አያውቅም። በቢቢሲ አማርኛና በቪኦኤ እንዳሻው ጊዜ መርጦ ወንጀሉን የሚያስተባብለው ጃል መሮ፤ ሲያሻው የሰጠውን ቃለ ምልልስ ስልክ ደውሎ እንዳይተላለፍ የሚያዝ ለመሆኑ ናኮር መልካ “ጃል መሮ ቃለ ምልልሱ እንዳይተላለፍ በጠየቁት መሠረት ትቼዋለሁ” ሲል ያረጋገጠው ሃቅ ነው። ቀደም ሲል በሃጫሉ ግድያ ኦነግ ሸኔ እጁ እንዳለበት በመታወቁ እጅግ የተቆጣውን ህዝብ ለማብረድ በናኮር መልካ አመቻችነት የቪኦኤ ዘጋቢ የሆነችው ጽዮን ግርማ ጃል መሮ በሬዲዮ ጣቢያው ቀርቦ ሳይፈተን እንዲፈነጭና ሃጢያቱን እንዲያራግፍ ፈቅዳለት እንደነበር ይታወሳል። ቢያንስ ማንነቱን መጠየቅ ሲገባ፣ ንጹሃንን በየቦታው እያደፈጠ ለሚጨፈጭፍ ሽፍታ፣ ሚዲያውንም ሌላ ጫካ በማድረግ … [Read more...] about ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ
ባልደራስና የአብን የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) በሀገሪቱ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሰፍን በጥምረት ለመስራት ያስችላል ያሉትን የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል። ትብብሩ በቀጣይ በአገሪቱ እንዲፈጠርና እንዲጎለብት የሚፈለገው የአገራዊ በጎ ሀይሎች ጥምረት መሰረት እንዲሆን ያለመ መሆኑም ተገልጿል። በመጪው አገራዊ ምርጫ የመራጮች የጋራ ፍላጎትና ራዕይ ለማሳካት ፓርቲዎቹ በጋራ ለመስራት በማሰብ የተመሰረ የፖለቲካ ትብብር መሆኑንም ነው ፓርቲዎቹ የገለፁት። በአገሪቱም ሆነ በዜጎች ላይ የተጋረጡ ፈተናዎች እንዳሉ የገለጹት ፓርቲዎቹ፣ ይህንን ከመቼውም ጊዜ በላይ በትብብር ለመታገል በቁርጠኝነት እንደሚሰሩና ትብብሩ ከምርጫው በኋላም እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። (ኢቢሲ) የባልደራስ መሪና በአሁኑ ጊዜ በእሥር ላይ የሚገኙት አቶ እስክንድር ነጋ ከአማራ ድርጅቶች በተለይ … [Read more...] about ባልደራስና የአብን የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም”
የቀድሞው ኢህአዴግ ካድሬዎች እና የህወሓት ጀነራሎች ሂሳብ አስተማሪው ኤርሚያስ ለገሰ ሆን ብሎ በቁጥር ሊጫወት ሞክሯል፡፡ አላማው ኢዜማ የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ሊያሸንፍ እንደማይችል አስመስሎ መሳል ነው፡፡ ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ሆኖበት ነው፡፡ ኤርምያስ ሹመት አስቦ የለውጡ ደጋፊ የነበረ ጊዜ የተናገረው የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም፡፡ ምናልባት እንዲገባው ከዚህ በፊት ከነበረው የተቃዋሚዎች ዕጩዎች ቁጥር በ11% እድገት አሳይተናል እንበለው ይሆን?? ምንም እንኳን [ለእንደዚ አይነቱ አውቆ አበድ መፍትሄው] ንቆ መተው ቢሆንም ያቀረበውን የተንኮል መረጃ እንደ እውነት ሊወስዱ የሚችሉ ቅኖችን ከስህተት ለማዳን ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ፡፡ ምርጫ የሚደረገው በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም”
በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ ነው – የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት በትግራይ ክልል የሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን አስታወቀ። ፅህፈት ቤቱ በክልሉ እየተደረገ ያለውን ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፥ በክልሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሰብአዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን አስታውቋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም እስካሁን በተመድ ስር በሚተዳደሩ ተቋማት የሚሰሩ 240 አባላት በክልሉ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሷል። ከዚህ ባለፈም ከሌሎች ተቋማትና ድርጅቶች የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ የድጋፍ ሰጪ አባላት በክልሉ ድጋፍ እያደረጉ ስለመሆኑም ገልጿል። እስካሁንም 900 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ሰብአዊ ድጋፍ ተደርጓልም ነው ያለው። ከተደረገው ድጋፍ ባሻገር ግን በክልሉ ሙሉ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ 400 … [Read more...] about በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ ነው – የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት
ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት ኦነግ በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ። ለሁለት ቀናት አጠቃላይ ጉባዔውን ያካሄደው ፓርቲው አዲስ ሊቀመንበርም መርጧል። ፓርቲው ባደረገው ጉባኤ የቡድኑን መሪ አራርሶ ቢቂላን የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል። አቶ ብርሃኑ ለማ እና አቶ ቀጄላ መርዳሳን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል። ጉባዔው 43 ቋሚ እና 5 ተለዋጭ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትንም መርጧል። በጠቅላላ ጉባኤው ህገ ደንቡን ያሻሻለው ፓርቲው የስነ ስርዓትና ቁጥጥር ኮሚቴም አቋቁሟል። ፓርቲው እራሱን ከምርጫ ማግለል እንደማይፈልግ የገለጸ ሲሆን የዕጩዎች መዝገባ ከመጠናቀቁ ጋር በተያያዘ ግን ምርጫ ቦርድ ከፈቀደ ወደ ምርጫው እንደሚገቡም አስረድተዋል። (ፋና) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት ኦነግ በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ