
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ።
ለሁለት ቀናት አጠቃላይ ጉባዔውን ያካሄደው ፓርቲው አዲስ ሊቀመንበርም መርጧል።
ፓርቲው ባደረገው ጉባኤ የቡድኑን መሪ አራርሶ ቢቂላን የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል።
አቶ ብርሃኑ ለማ እና አቶ ቀጄላ መርዳሳን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር ሆነዋል።
ጉባዔው 43 ቋሚ እና 5 ተለዋጭ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትንም መርጧል።
በጠቅላላ ጉባኤው ህገ ደንቡን ያሻሻለው ፓርቲው የስነ ስርዓትና ቁጥጥር ኮሚቴም አቋቁሟል።
ፓርቲው እራሱን ከምርጫ ማግለል እንደማይፈልግ የገለጸ ሲሆን የዕጩዎች መዝገባ ከመጠናቀቁ ጋር በተያያዘ ግን ምርጫ ቦርድ ከፈቀደ ወደ ምርጫው እንደሚገቡም አስረድተዋል። (ፋና)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply