• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በርግጥ ኢትዮጵያ ዝናብ አዝንባለች?

March 23, 2021 10:15 pm by Editor 2 Comments

በዛሬው (ማክሰኞ) የፓርላማ ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈጥሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው፤ ዓለም ላይ ያላቸውን ደመናን ወደዝናብ የቀየሩ አገራት ጥቂት አገራት ናቸው፤ እኔ ኢትዮጵያ ውስጥ መቼ አየዋለሁ ብዬ ከምቀናባቸው ነገሮች አንዱ ይሄ የተከማቸ ደመና በተመረጠ ሁኔታ ማዝናብ መቻልን ነው፤ አሁን ኢትዮጵያ ይሄንን አቅም ገንብታለች፤ ባለፉት ሳምንታት በሰሜን ሸዋ እና በጎጃም ያያችሁት ዝናብ የተፈሮ ሳይሆን እኛ ያዘነብነው ነው፤ በግልጽ በሚቀጥሉት ሳምንታት እናስመርቀዋልን፤ ወይንም እናስጀምረዋለን፤ ኢትዮጵያ ደመናዋን ተጠቅማ ዝናብ ማዝነብ ችላለች” ብለው ነበር።

ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል።

ይህን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ተጨባጭ ሳይንስ ነው?

የብሄራዊ ሚትሪዮሎጂ ድርጅት ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ክንፈ ኃይለማርያም ዛሬ ምሽት በነበረው የቢቢሲ ሬድዮ ስርጭት ፥ “… በቤጂንግ ኦሎምፒክ መክፈቻ ቀን ቻይና በዓሉን በብሩሃማ ቀን ለማክበር ብላ ተጠቅማበታለች። ያ ምን ማለት ነው ደመናማ ሆኖ በዛ ቀን ሊዘንብ የነበረውን በቤጂንግ ኦሎምፒክ አካባቢ በዝናብ መልክ ቀድሞ በማበልፀግ መክፈቻውንም መዝጊያውንም በብሩህ ቀን እንዲከበር አድርጋለች” ሲሉ በምሳሌ አስረድተዋል።

ዝናብ ማዝነቡ ድርቅን በማጥፋት ደረጃ እንደሆነ የተጠየቁት አቶ ክንፈ ዝናብ ማዝነበ ድርቅን በማጥፋት ደረጃ አይደለም ያሉ ሲሆን ድርቅን ማጥፋት ሰፊ ጊዜ የሚወስድ ነው ብለዋል።

አቶ ክንፈ ፥ “ደመናው ከሌለ ዝናቡን ማበልፀግ አይቻልም፤ ደመናውን መፍጠር አንችልም፤ ዝናብ ለማበልፀግ ዝግጁ የሆነ ደመና በተፈጥሮ መምጣት አለበት፤ ሳይንሱም እሱን ነው የሚነግረን ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

እንዴት ነው የሚሰራው? ጎጃም እና ሸዋ ላይ እንዴት ዘነበ?

እቶ ክንፈ ኃይለማርያም ፦ “…ደመና በትነት መልክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወደዝናብ ያልተቀየሩ የውሃ ነጠብጣቦች የሚይዝ ነው። እነዛ ተሰብስበው መጠናቸው አድጎ በመሬት ስበት ወደመሬት ዝናብ ሆነው እንዲመጡ መሰባሰብ አለባቸው፤ ያን የሚያሰባስብ ኬሚካል ነው የሚደረገው።

ይህ ከደመናው አይነት ይለያያል እኛ የሞከርነው ውሃ የሚስማማው አይነት ነው። ይህ የጨው አይነት ያላቸው ሶዲየም፣ ፖታሲየም፣ ክሎራይክ፣ ሌላም ናኖ ቴክኖሎጂ የተጨመረባቸው አሉ። 

አንዳንድ ሀገሮች በሮኬት መልክ ይተኩሱታል፤ ለምሳሌ ቻይና፣ አንዳድን ሀገሮች ደግሞ በድሮን ደመናው ጋር ያደርሳሉ ለምሳሌ ኢራን፣ ሌሎች ሀገሮች ከመሬት ግራውንድ ጄኔሬተር ይባላሉ ተራራማ የሆኑ እንደኛ አይነት ሀገራት ደመናው ቅርብ ስለሆነ ንፋስ በሚመጣበት አቅጣጫ ከመሬት ኬሚካሉን በጭስ መልክ በመልቀቅ ወደ ደመናው እንዲደርስ ያደርጋሉ። ዋነኛው በአውሮፕላን የሚረጭ ነው፤ እኛ ባለፈው የሞከርነው በአውሮፕላን የረጨነውን ነው።”

ኢትዮጵያን እያገዙ ያሉ ሀገራት እነማን ናቸው?

“አሁን ላይ በቴክኒክም በፋሲሊቲም የሚያግዙን የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) መንግሥት እና የሜትሪዮሎጂ ማዕከል ናቸው። ቴክኖሎጂውን አሁን የምንሞክረውን ቀጥታ ከነሱ በመጣ ቴክኖሎጂ ነው ኤር ክራፍቱም ፣ ንጥረ ነገሩም ከነሱ የመጣ ነው። ዋና የሚያስተባብረው እና የሚመራው የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነው”።

ቀጣዩ ሙከራ የት ነው የሚደረገው?

“አሁን Weather Condition ያለው ሻውራ ነው። ሻውራ ማለት ከጣና በስተምዕራብ ነው ያለው። ስለዚህ ከአ/አ እስከ ሻሁራ የተሻለ ደመና የተገኘበት ነው የሚሆነው። ከተቻለ ጥሩ ደመና ካገኘን ቅድሚያ ሰጥተን የምንሞክርበት ከሻውራ ወደ ወልዲያ አቅጣጫ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ጨምሮ ነው። የሚወስነው በአየር ሁኔታ መከታተያ ራዳር የምያገኛቸው የደመና ይዘቶች እና መጠን ነው።”

ምንጭ፦ ቢቢሲ ሬድዮ (Compiled By: Tikvah)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: News, Right Column, Social Tagged With: artifical rain, gojjam, shoa

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    March 23, 2021 10:46 pm at 10:46 pm

    ቀዳዳው አብይ ምን የማይለው ነገር አለ ! እንዳውም ሰሞኑን አንድ ስም ወጥቶለት አይቻለሁ “ምን ተስኖት” ብልውት በማኅበራዊ ሚዲያ ተለቆ ነበር ፥ አብይ ገና ብዙ ነገር ይለናል ፥ ሰማይ ተቀዶ ስሰፋ አደርኩ እንዳለችው ሴትዮ ማለት ነው የትግራይ ፋሽስትና ነፍሰ_ገዳይ ያስተማሩትን ውሸት ከእነርሱ በበለጠ እየሰራበት ነው ፥ እግዚአብሔር አብይን እንደ ጌታው ለገሰ ዜናዊ ድንገት ድብን ካላደረገልን የኢትዮጵያ ጉዳይ በእጅጉ አሳሳቢ ነው ፡፡

    Reply
    • Abraham says

      April 7, 2021 05:54 pm at 5:54 pm

      ከመሳደብህ በፊት ሳይንስ አጥና መሃይምነት ከለመማርና መመራመር ይመጣል

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule