• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ ነው – የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት

March 17, 2021 04:54 am by Editor Leave a Comment

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት በትግራይ ክልል የሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን አስታወቀ።

ፅህፈት ቤቱ በክልሉ እየተደረገ ያለውን ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፥ በክልሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሰብአዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን አስታውቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም እስካሁን በተመድ ስር በሚተዳደሩ ተቋማት የሚሰሩ 240 አባላት በክልሉ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሷል።

ከዚህ ባለፈም ከሌሎች ተቋማትና ድርጅቶች የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ የድጋፍ ሰጪ አባላት በክልሉ ድጋፍ እያደረጉ ስለመሆኑም ገልጿል።

እስካሁንም 900 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ሰብአዊ ድጋፍ ተደርጓልም ነው ያለው።

ከተደረገው ድጋፍ ባሻገር ግን በክልሉ ሙሉ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ 400 ሚሊየን ዶላር ያስፈልጋልም ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ከዚህ ቀደም በክልሉ ያደርግ የነበረውን የምግብ ድጋፍ በማሳደግ ለ770 ሺህ ሰዎች ምግብ ነክ ድጋፍ ለማድረግ የያዘውን እቅድም በትናንትናው እለት በይፋ ጀምሯል።

በዚህም በትናንትናው እለት ለ18 ሺህ የእደጋ ሃሙስ ነዋሪዎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።

ድጋፉ ሩዝ፣ በቆሎ እና የአትክልት ዘይትን ያካተተ መሆኑንም ገልጿል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ከተካሄደው የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ ጋር በተያያዘ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

ተቋሙም የድጋፉን ተደራሽነት ለማጠናከርና ለማሳደግ እንደሚሰራ መግለጹም ይታወሳል። (ፋና)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Right Column Tagged With: operation dismantle tplf, tigray, tigray aid

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአብን “ፀሐይ” ጎንደር ላይ ጠለቀች April 22, 2021 09:48 pm
  • ተፈትነን እንጂ ወድቀን አናውቅም April 22, 2021 10:55 am
  • ፍፁም ብርሃኔና ታምራት የማነ በቁጥጥር ሥር ዋሉ April 16, 2021 10:06 am
  • “ለአንድ ፓርቲ የማደላ ከሆነ ሄጄ እዚያው ፓርቲ እገባለሁ” ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ April 16, 2021 08:45 am
  • “ተዋግተን አይደለም ስንተኛ ብንውል እንኳን መቀሌና አዲስ አበባ አይገቡም” ጄኔራል ባጫ April 14, 2021 09:06 am
  • የስኳር ፋብሪካዎች ተሽጠው ዕዳቸውን እንዲከፍሉ ተወሰነ April 14, 2021 08:53 am
  • “ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ April 1, 2021 02:01 am
  • ምርጫ ቦርድ የኦነግን ጥያቄ ውድቅ አደረገ April 1, 2021 01:15 am
  • “እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ መንግሥት ኮሮጆ አይሰርቅም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ April 1, 2021 01:09 am
  • መንግሥት ካልደረሰልን አሁንም ግድያ ይኖራል – ነዋሪዎች April 1, 2021 01:04 am
  • በትግራይ ሊዘረፍ የነበረ የእርዳታ እህል ተያዘ April 1, 2021 12:39 am
  • “በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አልደራደርም” March 24, 2021 01:22 am
  • “ከዚህ በኋላ ህወሓት ማለት በነፋስ የተበተነ ዱቄት ነው” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ March 23, 2021 11:28 pm
  • እነ ስብሃት ነጋ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆነ March 23, 2021 10:23 pm
  • በርግጥ ኢትዮጵያ ዝናብ አዝንባለች? March 23, 2021 10:15 pm
  • አሜሪካ በሴናተሯ አማካይነት “ለቅሶ” ደረሰች March 21, 2021 08:57 pm
  • ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ March 19, 2021 04:32 pm
  • ባልደራስና የአብን የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ March 18, 2021 01:56 pm
  • ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም” March 17, 2021 09:54 pm
  • በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ ነው – የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት March 17, 2021 04:54 am
  • ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት ኦነግ በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ March 17, 2021 04:30 am
  • በዓለምአቀፍ ሚዲያ ዘጋቢዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው March 15, 2021 11:25 am
  • በሲዳማ/ሀዋሳ 128 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ፤ 2 መትረየስ ከ8,129 ጥይት ጋር ተያዘ March 15, 2021 10:13 am
  • የአክሱም ጅምላ ጭፍጨፋ ተብሎ የተሰራጨው ፎቶ የሐሰት ሆነ March 15, 2021 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule