የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት በትግራይ ክልል የሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን አስታወቀ። ፅህፈት ቤቱ በክልሉ እየተደረገ ያለውን ሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፥ በክልሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሰብአዊ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን አስታውቋል። ከዚህ ጋር ተያይዞም እስካሁን በተመድ ስር በሚተዳደሩ ተቋማት የሚሰሩ 240 አባላት በክልሉ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሷል። ከዚህ ባለፈም ከሌሎች ተቋማትና ድርጅቶች የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ የድጋፍ ሰጪ አባላት በክልሉ ድጋፍ እያደረጉ ስለመሆኑም ገልጿል። እስካሁንም 900 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ሰብአዊ ድጋፍ ተደርጓልም ነው ያለው። ከተደረገው ድጋፍ ባሻገር ግን በክልሉ ሙሉ ምላሽ ለመስጠት ተጨማሪ 400 … [Read more...] about በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ ነው – የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት