አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን የዛሪማ መስጊድን በከባድ መሳሪያ ደብድቦ ማውደሙን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አረጋ ገጠ። አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ድርጊትም የሰዎችን እምነት የሚጋፋ መሆኑን ምክር ቤቱ ገልጿል። የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ፀሐፊ ሀጂ ሙሀመድ ሀሰን፣ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፣ በሰሜን ጎንደር ውስጥ በሚገኘውና በቅርብ በተገነባው የዛሪማ መስጊድ ላይ በከባድ መሳሪያ ተኩሶ መስጊዱን በከፊል አውድሟል። በአካባቢው አሸባሪው ቡድን ሸሽቶ ጫካ በመግባቱና ደብቆ ባከማቸው የከባድ መሳሪያ ከርቀት በማስወንጨፍ በዛሪማ መስጊድና በአካባቢው በሚገኙ ቤተ-እምነቶችና ንፁሀን ላይ ጉዳት እያደረሰ እንዳለ ገልጸዋል። አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመው ተግባርም ለእምነት ክብር እንደማይሰጥ አንዱ ማሳያ መሆኑንም … [Read more...] about ትህነግ የዛሪማን መስጊድ አወደመ
News
ዜና
ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጋምቤላ ከተማ ለአሸባሪው ሸኔ ሊተላለፍ የነበረ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ከሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ጋር ትናንት በቁጥጥር ስር መዋሉን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊ አቶ ቡን ዌው ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የጦር መሳሪያው የተገኘው በጋምቤላ ከተማ በባጃጅ ተሽከርካሪ ተጭኖ ለማስተላለፍ ሲሞከር ነው። ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ከዋለው የጦር መሳሪያ መካከል አንድ ላውንቸር፣ አንድ ክላሽንኮቭ ከ705 ጥይት ጋር እንዲሁም 76 ዲሽቃ እንደሚገኝበት አመልክተዋል። ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ በሰጡት ቃል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ ለሸኔ የሽብር ቡድን ሊተላለፉ እንደነበር መናገራቸውን ኃላፊው አስረድተዋል። የክልሉ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ በጋራ በመሆን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከላከል ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል። … [Read more...] about ለሸኔ ሊተላለፍ የነበረ የጦር መሳሪያ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ዋለ
በባህርዳር ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ
በባህርዳር ከተማ በዳግማዊ ሚኒሊክ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ማር ዘነብ ቀበሌ ሲቱ ዋርካ አካባቢ በአንድ ተጠርጣሪ ቤት ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማና ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 3 ሺህ 676 የክላሽ ጥይት፣ 1 ሺህ 288 የመትረየስ ጥይት፣ 3 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ እና 20 የተለያዩ ሽጉጦችን ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መያዙን የ9ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ አስታውቀዋል። እንደ ምክትል ኢንስፔክተር ቀለሙ ረታ ገለጻ በክፍለ ከተማው ብሎም በከተማዋ መሰል ወንጀሎች ከጊዜ ወደጊዜ ተደጋግመው ቢከሰቱም በፀጥታ ኀይሉ የጠነከረ ትጋትና በህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ይገኛሉ። አሸባሪው ህወሓት በየቦታው ህዝብን ለማጥፋት እሳት እያነደደ ባለበት በዚህ ጊዜ መላው ህዝብ ከፀጥታ ኀይሉ ጎን በመሆን … [Read more...] about በባህርዳር ከተማ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጉጂ 119 ኪሎ ግራም፤ በአርሲ ሦስት መኪና ጭነት አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ዋለ
በጉጂ ዞን የአዶላ ሬዴ ወረዳ በሞተር ብስክሌት ሲጓጓዝ የነበረ 119 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብዱልከሪም ሁሴን እንደገለጹት፤ አደንዛዥ እጹ በቁጥጥር ስር የዋለው ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ጭለማን ተገን በማድረግ ወደ ነገሌ ከተማ ሲጓጓዝ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተደርሶበት ነው፡፡ የሰሌዳ ቁጥር በሌለው ሞተር ብስክሌት ተጭኖ በገጠር ውስጥ ለውስጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረው አደንዛዥ እጹ አዳማ ዲባ በተባለ ገጠር ቀበሌ መቆጣጠር እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡ የሞተር ብስክሌቱ አሽከርካሪ ለጊዜው ሞተሩንና አደንዛዥ እጹን ጥሎ ከአካባቢው ሸሽቶ ቢያመልጥም ለመያዝ ክትትል እየተደረገበት መሆኑን አስረድተዋል። የወረዳው ህዝብ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ላደረገው … [Read more...] about በጉጂ 119 ኪሎ ግራም፤ በአርሲ ሦስት መኪና ጭነት አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ዋለ
“የኢትዮጵያ ችግር የዕርዳታ ስንዴ ነው”
https://www.youtube.com/watch?v=IZmU5BgDfJA … [Read more...] about “የኢትዮጵያ ችግር የዕርዳታ ስንዴ ነው”
በወለጋ የሰፈሩ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ትህነጎችና የሸኔ ግፍ
በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሙ ወረዳ ሀሮ ከተማ ፅንፈኛው የአሸባሪ ቡድን ሸኔ ጥቅምት 1 እና 2 በንፁሃን ላይ በከፈተው ጥቃት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል። ቡድኑ ከህውሃት የሽብረ ቡድን ጋር ህብረቱን ካረጋገጠ በኋላ በብሄር ብሄረሰቦች ላይ ትንኮሳ በማድረግ ግጭቶችም የብሄር መልክ እንዲይዙ እየሰራ ይገኛል ብለዋል የቢሮው ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ። ኃላፊው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ሸኔ በአካባቢው ከሚንቀሳቀስ ሌላ የሽፍታ ቡድን ጋር በመተባበር በሀሮ ከተማ በከፈተው ጥቃት የ15 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የንብረት ውድመት እንዳደረሰ እንዲሁም 967 አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ተናግረዋል። የክልሉ መንግስት ተጨማሪ የፀጥታ ሀይል ወደ ስፍራው በማሰማራት ወረዳውን እና ከተማውን … [Read more...] about በወለጋ የሰፈሩ ኦሮሚኛ ተናጋሪ ትህነጎችና የሸኔ ግፍ
እያፈገፈገ ያለውን ሽፍታ የሚመራው ፃድቃን ጦርነቱ “በቀናት፣ ግፋ ቢል በሳምንታት ይጠናቀቃል” አለ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ አማጺ ሃይል መሪ የሆነው ጻድቃን ገብረትንሳይ ጦርነቱ እንደማይራዘም አመለከተ። አዲስ ተጀመረ የተባለውን ጦርነት “የቀናት ጉዳይ ነው፣ ግፋ ቢል በሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል” ሲል የተናገረው ለኒውዮርክ ታይምስ ነው። የትግራይ ሕዝብ የዕድሜ ልክ ጠላት ሲሉ የጠራቸው ኢሳያስ መወገድ እንዳለባቸው ለዓለም ማህበረሰብ አስታውቋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ማጥቃት አለመጀመሩን፣ ነገር ግን ዝግጅቱን አጠናቆ መመሪያ እየጠበቀ መሆኑንና ማጥቃት ከጀመረ “ድረሱልኝ” የሚል ጊዜ የሚሰጥ እንዳልሆነ ከዚህ በፊት ሲነገር ነበር። ትህነግ ያወጣውን የድረሱልኝ ጥሪ ተከትሎ መከላከያ ይህንን ቢልም የተለያዩ ሃላፊዎችና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ደጋግመው ጥቃት መጀመሩን እያስታወቁ ነው። የአየር ሃይል አዛዥም በባንዲራ ቀን አየር ኃይል “ጠላትን … [Read more...] about እያፈገፈገ ያለውን ሽፍታ የሚመራው ፃድቃን ጦርነቱ “በቀናት፣ ግፋ ቢል በሳምንታት ይጠናቀቃል” አለ
መረን የለቀቀ ግፍ፤ በዛገ በርሜል የተሠራ የጎመንዘር ዘይት ለሕዝብ
በሻሸመኔ በህገወጥ መንገድ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረተ ለህብረተሰቡ ሲሸጥ የነበረ ድርጅት ታሸገ። በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ከሻሸመኔ ጤናና ጤና ነክ የስራ ሂደት ተቆጣጣሪ ጋር በጋራ በመሆን በኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የደቡብ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በምግብ ዘይት ላይ የገበያ ቅኝት መሥራቱን የኢትዮጲያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል። በዚህም ቅኝት ከሚመለከተው የተቆጣጣሪ አካል የዘይት ምርት ለማምረት የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳይኖራቸው፣ የምርት ማሸጊያ መስፈርት ባላሟላ፣ ንጽህናዉ ባልጠበቀ የአመራረት ሂደት እንዲሁም ዘይት ለማምረት ምቹ ባልሆነ ቤት ውስጥ የጎመንዘር እህል ዘይት በመጭመቅ እያመረቱ ለህብረተሰቡ እየሸጠ የተገኘ አንድ ድርጅት ላይ ምርት የማምረት ሥራዉን እንዲያቆሙና ድርጅቶቹ ከተመረተው የዘይት … [Read more...] about መረን የለቀቀ ግፍ፤ በዛገ በርሜል የተሠራ የጎመንዘር ዘይት ለሕዝብ
የተመድ የሥልጣን ሽኩቻና የኃላፊዎች መጠራት
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ ያልተገባ አስተያየት ሰጥተዋል ያላቸውን ሁለተኛዋን የተመድ የኢትዮጵያ ኃላፊን ጠርቷል። ተመድ የጠራቸው የድርጅቱ ሥነ ሕዝብ ጽ/ቤት (ዩኤንኤፍፒኤ) የኢትዮጵያ ኃላፊ ዴኒያ ጌይል መሆናቸውን ኤኤፍፒን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል። ቀደም ሲል የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) የኢትዮጵያ ኃላፊ ማውሪን አቻንግ "የድርጅቱን እሴቶች የማያንጸባርቅ" አስተያየት በመስጠታቸው ምክንያት አስተዳደራዊ እረፍት እንዲወስዱ መደረጉን ተቋሙ ገልጾ ነበር። መንግሥታቱ ድርጅት የሥነ ሕዝብ እና የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊዎች ለትግራይ ኃይሎች ርኅራኄ አላቸው ባሏቸው የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ጎን ገሸሽ ተደርገናል ማለታቸው ተዘግቧል። ሁለቱ በኢትዮጵያ የተመድ ከፍተኛ ኃላፊዎች የፌዴራሉ መንግሥት በትግራይ ላይ … [Read more...] about የተመድ የሥልጣን ሽኩቻና የኃላፊዎች መጠራት
የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኃይል ለማመንጨት የሚረዳ ግንባታ ሊጀመር ነው ተባለ
የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ ከመሬት ውስጥ እንፋሎት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የሚችል ፕሮጀክት ሲሆን፣ የሀይል ማመንጫ ግንባታውን ለማካሄድ መታቀዱን በቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኢነርጂ ድርጅት የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ነዚፍ ጀማል ገልጸዋል። ነዚፍ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት ይህንን ግንባታ ለማካሄድ ጨረታ የወጣ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የሀይል ማመንጫው ቁፋሮ ላይ የሚገኝ የግንባታ ሂደት ነው ብለዋል። በፈረንጆች 2020 የወጣው የመጀመሪያ ጨረታ ሰባት ትልልቅ አለም አቀፍ የተርባይን አምራች ድርጅቶች መወዳደራቸውንና በአሁኑ ሰዓት ኹለት ድርጅቶች ስራውን ተቀብለው ለመስራት እየተጠባበቁ መሆናቸውን ነዚፍ ጠቁመዋል። በአሁኑ ሰዓት ጨረታው ላይ በቀረበው የቴክኒክ ብቃት መሰረት ከሰባት ድርጅቶች ውስጥ ኹለት ብቻ የቀሩ ሲሆን፣ በዋናነት ግንባታውን የሚያካሂደው እና በተጠባባቂነት ያለው … [Read more...] about የቱሉ ሞዬ ጂኦተርማል ኃይል ለማመንጨት የሚረዳ ግንባታ ሊጀመር ነው ተባለ










