
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ አማጺ ሃይል መሪ የሆነው ጻድቃን ገብረትንሳይ ጦርነቱ እንደማይራዘም አመለከተ። አዲስ ተጀመረ የተባለውን ጦርነት “የቀናት ጉዳይ ነው፣ ግፋ ቢል በሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል” ሲል የተናገረው ለኒውዮርክ ታይምስ ነው። የትግራይ ሕዝብ የዕድሜ ልክ ጠላት ሲሉ የጠራቸው ኢሳያስ መወገድ እንዳለባቸው ለዓለም ማህበረሰብ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እስካሁን ማጥቃት አለመጀመሩን፣ ነገር ግን ዝግጅቱን አጠናቆ መመሪያ እየጠበቀ መሆኑንና ማጥቃት ከጀመረ “ድረሱልኝ” የሚል ጊዜ የሚሰጥ እንዳልሆነ ከዚህ በፊት ሲነገር ነበር። ትህነግ ያወጣውን የድረሱልኝ ጥሪ ተከትሎ መከላከያ ይህንን ቢልም የተለያዩ ሃላፊዎችና ዓለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ደጋግመው ጥቃት መጀመሩን እያስታወቁ ነው። የአየር ሃይል አዛዥም በባንዲራ ቀን አየር ኃይል “ጠላትን እየቀጠቀጠ ነው” ብለዋል።
የሽፍታው መሪ ጻድቃን ጦርነቱ የቀናት፣ ግፋ ቢል የሳምንታት ጉዳይ መሆኑንን ሲናገር ከማን ወገንና እንዴት ገምግሞት እንደሆነ ዘገባው ጥልቅ ትንተና አልሰጠም። ነገር ግን ጻድቃን “… Airstrikes took out most of the Tigrayan artillery and forced its troops to retreat into the remote countryside.” ማለቱን ጋዜጣው ዘግቧል። በአየርና በምድር ከባድ መሳሪያ ድብደባ የተነሳ ከባድ መሳሪያና ሽግታው ስብስብ ራቅ ወዳለው የትግራይ ገጠራማ አካባቢ እንዳፈገፈገ ፃድቃን ሳይደብቅ ተናግሯል። (ሩቅ ገጠራማ የተባለው ቆላ ተንቤን ስለመሆኑ በግልጽ አልተገለጸም)።
ኒውዮርክ ታይም የኢትዮጵያ መንግሥት በትህነግ ሃይል የተያዙ ስፍራዎችን ለማስለቀቅ ማጥቃት መጀመሩን “አማጺ” ሲል የሚጠራቸው የትህነግ ሃላፊዎችና የምዕራብ ዲፕሎማቶች እንዳረጋገጡለት ይገልጻል። ከመንግሥት ወገን ምንም መረጃ ማግኘት እንዳልቻለና በመገናኛ እጥረት ሳቢያ በዝርዝር ማቅረብ እንዳልቻለ አመላክቷል።
የመንግስት ቃለ አቀባይ የሆኑት ቢለኔ ስዩም “መንግስት በመላው አገሪቱ ያሉትን ዜጎቹን ከሽብር ተግባራት የመጠበቅና የመከላከል ሃላፊነት አለበት” ሲሉ ለፍራንስ 24 መናገራቸውን በርካታ መገናኛዎች መግለጻቸው ይታወሳል።
የሽፍታው የትግራይ ኃይል አመራር ጻድቃንን በስክል ማናገሩን የጠቀሰው የኒውዮርክ ታይም ዘገባ እንደሚያስረዳው የኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል ድሮን፣ ከባድ መሳሪያና ተዋጊ ጀቶችን ተጠቅሞ በትግራይ አማጺ ሃይል ላይ ጥቃት የጀመረው ባለፈው ዓርብ ዕለት ነው ብሏ።
“ሰኞ” አለ የሽፍታው መሪ ጻድቃን “በሺህ የሚቆጠሩ የመከላከያ ሰራዊት ሰኞ የምድር ውጊያ ጀመሩ”፤ አክሎም “ጠላት” በማለት የጠራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለወራት ሲዘጋጅ መቆየቱን አመልክቶ “መጪው ጦርነት ለአገሪቱ ወሳኝ ጊዜ ነው” ሲል ተንብይዋል። እነሱም በተመሳሳይ ሲዘጋጁ እንደነበር አስታውቋል።
ስለጦርነቱ ወሳኝነት ያነሳው የወንበዴው መሪ፣ የጦርነቱ ውጤት ወይም መደምደሚያ ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ እንደሚሆን አመልክቷል ። ይህንን ሲል ግን ምን ለማለት እንደሆነ ዝርዝሩን ዘጋቢው አልጠየቀም። “ጦርነቱ የሚራዘም አይመስለኝም። የቀናት ጉዳይ ነው። ምናልባትም ሳምንታት” በማለት ፃድቃን ቀን በመቁረጥ ተንብዮዋል። “I don’t think this will be a protracted fight — a matter of days, most probably weeks.”
የትህነግ ቃል አቀባይ ጌታቸው ልክ እንደ ጻድቃን መደብደባቸውን በተደጋጋሚ በመግለጽ ለጦርነት አመቺ የሆነ ገዢ መሬቶችን እንደያዙ ማስታወቁ አይዘነጋም። በሰሜን ወሎ ያሉ የአካባቢውን አስተዳደሮች ያነጋገረው የጀርመን ድምጽ እንዳረጋገጠው የትህነግ ሃይል (በነሱ አባባል የተረፈው) ከተማ እያወደመ፣ ያልቻለም እየሸሸ መሆኑንና ጥቃቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን ማስታወቃቸው፣ የትግራይ የጀርመን ድምጽ ባልደረባ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዳላከለ ይታወሳል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ በየአቅጣጫው የተከፈተውን ዘመቻ በአሉታዊ ጎኑ አሰባስቦ ለዜናው ማዳመቂያነት ኢትዮጵያ ላይ ለተከፈተው የድራማ ማስዋቢያነት ይጠቅመው ዘነድ የሰገሰገው የኒውዮርክ ታይም ዘገባ ኢትዮጵያ ከኢራን፣ ከቱርክና ከቻይና ድሮኖችን በመግዛት በደንብ መታጠቋን ገልጿል። አንድ የምዕራብ ባለሥልጣን እንደነገሩት ጠቅሶ ባለፉት ስድስት ሳምንታት ብዛት ያለው የግዙፍ ካርጎ በረራ ከአረብ ኢምሬትስ ወደ ኢትዮጵያ መጓጓዙን ኒውዮርክ ታይም አመልክቷል። አስከትሎም ጻድቃን አረብ ኢምሬትስን ቀደም ሲልም ሆነ አሁን ዕርዳታ ማድረጓን ማውገዙ አትሟል። የኢሚሬትስ ባለስልጣናት ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑም አስታውቋል።
ጋዜጣው የወቅቱን የትህነግን ሁኔታ ሲያስረዳ “… Airstrikes took out most of the Tigrayan artillery and forced its troops to retreat into the remote countryside.”ብሏል ። የአየር ጥቃቱ አብዛኛውን ከባድ መሳሪያና ሰራዊታቸውን ወደ ሩቅ ገጠራማ ስፍራ እንዲያሸሹና እንዲያፈገፍጉ እንዳደረጋቸው ጻድቃን ለኒውዮርክ ታይም ተናግሯል።
“የትግራይ የዘመናት ጠላት” ሲል የኤርትራን ፕሬዚዳንት ኢሳያስን የጠቀሰው ጻድቃን “ኢሳያስና ሰራዊታቸው ለቀጣናው መርዝ ናቸው” ብሏል። “If the international community is earnestly looking for a peaceful solution, a settlement will not happen without taking care of Isaias.” አያይዘውም “ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሰላማዊ መፍትሔ ለማግኘት ከልብ የሚፈልግ ከሆነ ፣ ቅድሚያ ኢሳያስን መላ/ ሊያስወግዷቸው ይገባል” የሚል መልዕክት አስተላልፏል።
በስልክ ጻድቃንን ያናገረው የናይሮቢው ዘገቢ ስጋና ደሙን በፍለገው ቦታ እየቀላቀለ ባተመው ጽሁፍ “አሁን ትልቁ ጥያቄ የኤርትራ ሃይሎች ዳግም ኢትዮጵያን ይረዱ ይሆን የሚለው ነው” ሲል ይጠይቅና፣ ሁለት የምዕራብ አገር ባለሥልጣናት እንደነገሩት ጠቆም አድርጎ የኤርትራ ሃይሎች አሁን ላይ (ከ1983 በኋላ ወደትግራይ እንድትቀላቀል የተደረገችው) ሁመራ እንደሚገኙ አንዳንዶችም አማራ ክልል እንደዘለቁ ገልጿል። ዘጋቢው ይህ ቢልም ጻድቃን የኤርትራ ሰራዊትን አስመልክቶ ያለው ነገር የለም። ጌታቸውም “የኤርትራ ሰራዊት ስለመኖሩ እርግጠኞች አይደለንም” ሲል ለፍራንስ 24 አስታወቋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply