በጉጂ ዞን የአዶላ ሬዴ ወረዳ በሞተር ብስክሌት ሲጓጓዝ የነበረ 119 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር አብዱልከሪም ሁሴን እንደገለጹት፤ አደንዛዥ እጹ በቁጥጥር ስር የዋለው ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም ጭለማን ተገን በማድረግ ወደ ነገሌ ከተማ ሲጓጓዝ በህብረተሰቡ ጥቆማ ተደርሶበት ነው፡፡ የሰሌዳ ቁጥር በሌለው ሞተር ብስክሌት ተጭኖ በገጠር ውስጥ ለውስጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረው አደንዛዥ እጹ አዳማ ዲባ በተባለ ገጠር ቀበሌ መቆጣጠር እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡ የሞተር ብስክሌቱ አሽከርካሪ ለጊዜው ሞተሩንና አደንዛዥ እጹን ጥሎ ከአካባቢው ሸሽቶ ቢያመልጥም ለመያዝ ክትትል እየተደረገበት መሆኑን አስረድተዋል። የወረዳው ህዝብ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ላደረገው … [Read more...] about በጉጂ 119 ኪሎ ግራም፤ በአርሲ ሦስት መኪና ጭነት አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር ዋለ