የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ዛሬ ምሽት በሰጠው መግለጫ ተደመሰሱ ካላቸው ውስጥ በፌዴራል መንግሥት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ጄነራሎችና ኮሎኔሎች ይገኙበታል። በመግለጫው ላይ ተደመሰሱ የተባሉት ጄነራሎችና ኮሎኔሎች ስም አልተገለፀም። የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ ይህን ነው ያሉት፦ "ባለፉት 2 ቀናት በባቲ ግንባር በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን 6 የአርሚና እና የኮር ከፍተኛ አመራሮቹ ተደምስሰዋል። እነዚህ አመራሮች በፌዴራል መንግሥት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈጉ የነበሩ ከሃዲ ጄነራሎች እና ኮሎኔሎች ናቸው። በተጨማሪ በከሚሴ ግንባር በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ልዩ ኦፕሬሽኖች የጠላትን ግንባር ጦር ሲመሩ የነበሩ 6 ከሃዲ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ከነጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል። በዛሬው ዕለት በባቲ ግንባር በተደረገው … [Read more...] about በ2 ቀናት በተካሄደ ኦፕሬሽን 12 የትህነግ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ተደምስሰዋል
News
ዜና
TPLF dehumanized Olusegun Obasanjo as the “worst kind of chimpanzee”
A top confidant and an avid activist of the TPLF (Tigray People's Liberation Front) dehumanized the African Union’s High Representative for the Horn of Africa, Olusegun Obasanjo as “worst kind of chimpanzee”. In a Facebook post made in Tigrigna on Sunday, November 21, 2021, Gebremichael said, “this worst kind of chimpanzee called Obasanjo, following his trip from Mekelle (Tigray’s capital), it is now reported that Isayas (Eritrea’s president) (and) Prosperity (Party) conducted a drone attack … [Read more...] about TPLF dehumanized Olusegun Obasanjo as the “worst kind of chimpanzee”
ትህነግ ኤርትራውያንን ለመጨፍጨፍ ማቀዱን ትሮንቮል አረጋገጠ
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር - ትህነግ ስም ሳይጠራ “ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ትሠራላችሁ" በሚል የጠቀሳቸው ክፍሎች ኤርትራዊያንን እንደሆነ ጥርጥር እንደሌለው ተመለከተ። ዛቻው በኢትዮጵያ ያሉ የኤርትራ ተወላጆች ላይ እንደሆነም ተጠቁሟል። ትህነግ በመግለጫው በመከላከያ፣ በደኅንነትና ጸጥታ ተቋማት “ተሰግስጋችሁ” ሲል የፈረጃቸው ማስጠንቀቂያው እንዲደርሳቸው ደጋግሞ አመልክቷል። በዚሁ ስምና አገር ይፋ ባልተደረገበት የማስጠንቀቂያ መግለጫ የተጠቀሱት ተቋማት ውስጥ አሉ ያላቸው የውጭ ዜጎች “የአስካሁኑ በቃን” ብለው አገር ለቀው እንዲወጡ፣ አገራቸውም የተጠቀሱትን ወገኖች ከኢትዮጵያ እንዲያስወጡ ያሳሰባል። ይህ ካልሆነ “የትግራይ መንግሥትና ሰራዊት በትግራይ ህዝብ ጆኖሳይድ በፈፀሙ ወንጅሎኞች ላይ በሚወሰደዉ ማንኛዉም አፀፋዊ እርምጃ ተጠያቂ እንደማይሆን የዓለም አቀፍ … [Read more...] about ትህነግ ኤርትራውያንን ለመጨፍጨፍ ማቀዱን ትሮንቮል አረጋገጠ
የዛሬ ዓመት በማይካድራ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ
• አንድ ሺ 564 ሰዎች በጭካኔ ተገድለዋል። • 81 ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። • ድርጊቱን የፈጸመው አሸባሪው ሕወሓት ያደራጀው ሳምሪ የሚባል ገዳይ ቡድን ነው። የዛሬ ዓመት በማይካድራ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ አንድ ሺ 564 ሰዎች በጭካኔ መገደላቸውን፤ 81 ሰዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ድርጊቱን የፈጸመው አሸባሪው ሕወሓት ያደራጀው ሳምሪ የሚባል ገዳይ ቡድን መሆኑን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የጥናት ቡድን መሪ ገለጹ። የጥናት ቡድኑ መሪ አቶ ጌታ አስራደ አለማየሁ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የዛሬ አመት በማይካድራ ጭፍጨፋውን ያካሄዱት ሳምሪ የተባለ አሸባሪው ሕወሓት ያደራጃቸው ገዳይ ቡድን ነው። ይህ ቡድን አንድ ሺ 564 ሰዎችን መጥረቢያ፣ ቆንጨራና፣ ቢለዋ፣ ማጭድና መሰል … [Read more...] about የዛሬ ዓመት በማይካድራ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ
“ሀገርን ማዳን ማለትም መንግሥትን መደገፍ ማለት አይደለም”አቶ ክርስቲያን
ኢትዮጵያ ከውስጥም ሆነ ከውጭ የተቃጣባትን የህልውና አደጋ ለመመከትና ሀገርን ለማስቀጠል እያንዳንዱ ዜጋ የአርበኝነት ተጋድሎ ማድረግ ይጠበቅበታል ሲሉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ገለጹ። የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እንደተናገሩት፤ አሸባሪው ሕወሓት ከምስረታው ጀምሮ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተፈጠረ ቡድን በመሆኑ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል የሚፈልግ ዜጋ ሁሉ ይህንን አሸባሪ ቡድን ግንባር ድረስ ሄዶ ሊፋለመው ይገባል። አቶ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ ከአሸባሪው ሕወሓት ውጪ በዓለም ታሪክ የመራትን ሀገር ለማጥፋት አልሞ የተነሳ የፖለቲካ ፓርቲ የለም። አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በገሀድ ሀገርን የማፍረስ አላማን አንግቦ ኢትዮጵያን … [Read more...] about “ሀገርን ማዳን ማለትም መንግሥትን መደገፍ ማለት አይደለም”አቶ ክርስቲያን
“ወያኔ የመርገም ውጤት ነው” አቶ ሽመልስ
ይህ ኃይል አስተሳሰቡም ተግባሩም ሠይጣናዊ ነው፤ የሠይጣን ቁራጭ ነውወያኔ ይዋሻል፤ የውሸት አባት ደግሞ ሠይጣን ነውየኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ድጋሚ ወያኔን የበላይነት ቢቀበል እግዚአብሔር አይቀበለውምኢትዮጵያዊ ውስጥ ወያኔን የሚወጋው ሰው እንኳን ባይኖር ንፋስ ይጥለዋልወያኔ ውሸት ላይ ስለቆመ ከእንግዲህ ኃይል ሆኖ አይቆምም ሕዝቡ በየአካባቢው በውስጡ ተሰግስገው ያሉት የአሸባሪው ሕወሓት ተላላኪዎችንና የሸኔ ጉዳይ አስፈፃሚዎችን መታገልና ከውስጡ መንጥሮ ማውጣት እንዳለበት የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አሳሰቡ። አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፤ አሸባሪው ትሕነግ ለኢትዮጵያ ጠላት ሆኖ የተፈጠረ ኃይል ነው። ይህ የአገር ጠላት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የኢትዮጵያ ሕዝብ … [Read more...] about “ወያኔ የመርገም ውጤት ነው” አቶ ሽመልስ
በአራት ቀን፣ አምስት ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ላይ 72 የሀሰት ዜናዎችን ለቀዋል
ሲኤንኤን፣ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ፣ አሶሼትድ ፕረስ እና ፍራንስ 24 የተሰኙ የምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን በአራት ቀኖች ውስጥ ብቻ በኢትዮጵያ ላይ 72 የሀሰት ዜናዎችን መልቀቃቸው ታውቋል። በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ የሚተላለፈው የ"ቴክቶክ" ፕሮግራም አዘጋጅ ሰለሞን ካሳ በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ፤ ምዕራባዊያኑ መገናኛ ብዙኃን ሆን ብለው በህዝቡ ውስጥ ሽብር ለመፍጠር የሀሰት ዘገባዎችን በስፋት እያሰራጩ ናቸው ብሏል። ዛሬም የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ በህይወት አለ ያለው ሰሎሞን፤ ከሰሞኑ የሚሰራጩት ሀሰተኛ ዘገባዎች ዋና አላማም አዲስ አበባ በሽብር ቡድኖች እንደተከበበች በማስመሰል ሽብር መንዛትና ሥነ ልቦናዊ አለመረጋጋት መፍጠር ነው ብሏል። እሁድ እለት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባደረጉት ሰልፍ ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ላይ … [Read more...] about በአራት ቀን፣ አምስት ምዕራባዊያን መገናኛ ብዙኃን በኢትዮጵያ ላይ 72 የሀሰት ዜናዎችን ለቀዋል
“ልብ ላለው ሰው ድንጋይም ከትጥቅ በላይ ነው” ባለጥሩምባ ዘማች መምህርት ምዕራፍ ፍቃዴ
እኔ ትጥቅ የለኝም፤ ወደትግሉ ስቀላቀል እንደ ትጥቅ ይዤ የገባሁት ጡርምባዬን ነው። ይህ የዘማቿ መምህርት ምዕራፍ ፍቃዴ ንግግር ነው። አሸባሪውና ወራሪው ኃይል በአማራና አፋር ክልሎች እያካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥቃት ተከትሎ በርካታ ዜጎች በቁጭት ይህን ኃይል ለመመከት ተነስተዋል። መምህርት ምዕራፍም በዚህ የህልውና ዘመቻ መልስ ከሰጡ እንስት ታጋዮች አንዷ ሆናለች። የአማራ ክልል የጠራውን የህልውና ዘመቻ በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባትን እየተወጣች እንድምትገኝ የምትናገራው ዘማቿ መምህርት፤ ለትግሉ መሳካት እየተጠቀመችበት ያለው ጥሩምባዋ የጦር መሳሪያ ያህል ነው ትላለች። ልብ ላለው ሰው አገርን በወሬ ለመፍታት የሚጥርን ወራሪ ቡድን ለመፋለም ድንጋይም ከትጥቅ በላይ መሆኑን ትናገራለች። “እኔም በጡሩምባ ለሠራዊቱ የሚሆን የተሳካ ሎጅስቲክስ ድጋፍ ማሰባሰብ … [Read more...] about “ልብ ላለው ሰው ድንጋይም ከትጥቅ በላይ ነው” ባለጥሩምባ ዘማች መምህርት ምዕራፍ ፍቃዴ
በደሴ የወንበዴው ክፍለ ጦር አዛዥ ጉዕሽ ገብሩ በቁጥጥር ሥር ውሏል
አሸባሪው የትህነግ ቡድን አገር የማፍረስ እቅዱን ለማሳካት በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ እንደሚገኝ በደሴ ግንባር የተማረከው የሽብር ቡድኑ ሜይዴይ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ጉዕሽ ገብረ ተናገረ። የሽብር ቡድኑ በርካታ ህፃናትና ሽማግሌዎችን ያለ ትጥቅ በማሰለፍም ለአላስፈላጊ መስዋዕትነት እየዳረጋቸው እንደሚገኝም ምርኮኛው ተናግሯል። አሸባሪው ትህነግ አገር የማፍረስ እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ከጀመረ ድፍን አንድ አመት ተቆጥሯል። ቡድኑ በጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም በሰሜን እዝ ላይ ያሰበው እቅድ እንዳሰበው አልሆን ሲለው የትግራይን ህዝብ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰባሰብ ለዳግም የክህደት ተግባር በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት ከፍቶ ይገኛል። የሽብር ቡድኑ ሰሞኑን እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል በማሰለፍ በደሴ ግንባር ውግያ ቢከፍትም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ … [Read more...] about በደሴ የወንበዴው ክፍለ ጦር አዛዥ ጉዕሽ ገብሩ በቁጥጥር ሥር ውሏል
“በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለም፤ በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ” ላይ መንግሥት የማያዳግም ርምጃ ይወስዳል
በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግስት አሳሰበ፡፡ በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ ወገኖች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አሳሰበ፡፡ በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለም ያለው አገልግሎቱ ከዚህ ድርጊታቸው በማይቆጠቡት ላይ መንግስት የማያዳግም ርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡ መላው ህዝብ ኢትዮጵያን የማዳን የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተገንዝቦ የጀመረውን ሀገር የማዳን ንቅናቄ አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስቧል፡፡ "ዋስትናችን ህልውናችንን በአንድነት ማረጋገጥ መሆኑን በመረዳት" በአፍራሽ ኃይሎችና ግብረ አበሮቻቸው በኩል የሚነዙ መርዛማ ወሬዎች የሚመጡበትን መንገድ መዝጋት እንደሚገባም ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያውያንና የወዳጅ ሀገራት ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ ትክክለኛውን … [Read more...] about “በሀገር ጉዳይ ቀልድ የለም፤ በነጭ ፕሮፖጋንዳ ሀገርን በማፍረስ ተግባር የተጠመዱ” ላይ መንግሥት የማያዳግም ርምጃ ይወስዳል










