እኔ ትጥቅ የለኝም፤ ወደትግሉ ስቀላቀል እንደ ትጥቅ ይዤ የገባሁት ጡርምባዬን ነው። ይህ የዘማቿ መምህርት ምዕራፍ ፍቃዴ ንግግር ነው።
አሸባሪውና ወራሪው ኃይል በአማራና አፋር ክልሎች እያካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥቃት ተከትሎ በርካታ ዜጎች በቁጭት ይህን ኃይል ለመመከት ተነስተዋል። መምህርት ምዕራፍም በዚህ የህልውና ዘመቻ መልስ ከሰጡ እንስት ታጋዮች አንዷ ሆናለች።
የአማራ ክልል የጠራውን የህልውና ዘመቻ በስኬት እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባትን እየተወጣች እንድምትገኝ የምትናገራው ዘማቿ መምህርት፤ ለትግሉ መሳካት እየተጠቀመችበት ያለው ጥሩምባዋ የጦር መሳሪያ ያህል ነው ትላለች።
ልብ ላለው ሰው አገርን በወሬ ለመፍታት የሚጥርን ወራሪ ቡድን ለመፋለም ድንጋይም ከትጥቅ በላይ መሆኑን ትናገራለች።
“እኔም በጡሩምባ ለሠራዊቱ የሚሆን የተሳካ ሎጅስቲክስ ድጋፍ ማሰባሰብ ችያለሁ” ስትል የምትናገረው ወዶ ዘማቿ መምህርት፤ በባዶ እጁ ለወረራ የሚመጣ ቡድንን ለመፋለም “ልብ ካለን” ጥሩምባ ትልቅ መሳሪያ ነው ትላለች።
እንደ ዘማች መምህርቷ ገለጻ፤ አሸባሪው ትህነግ አንድን መሳሪያ ለሰባት ሰዎች በማስታጠቅ ኢትዮጵያን በወሬ ለማፍረስ እየጣረ ነው። በወሬ አገርን ለማፍረስ የሚጥርን ጠላት ለመፋለም ድንጋይም ከመሳሪያ በላይ ነው።አንዳንድ ወጣቶች ትጥቅ የለንም እና ሌሎች ሰበቦችን በማንሳት የህዝቡን ወኔ ለማዳከም ሲጥሩ ይስተዋላል። እነኝህ አካላት የአሸባሪው ሕወሓት ተላላኪ እንደሆኑ ሕዝቡ ሊገነዘብ ይገባል ትላለች።
በመንግሥት የተጠራው የህልውና ዘመቻ ነው። በህልውና ዘመቻ የግድ ሁሉም መሣሪያ ካልተሰጠኝ ብሎ ራስን ለጠላት አሳልፎ መስጠት አይገባም። የተነሳው ወጣት ስንቅ በማዘጋጀት፣ የደከመን የወገን ኃይል በማገዝ፣ መሳሪያ በመሸከም፣ ቁስለኛን በማሸሽ እንዲሁም ሌሎች ተግባራትን በማከናወን ወጣቱ የድርሻውን በማበርከት አሸባሪው ቡድን እስኪቀበር መታገል ይኖርበታል ትላለች።
አሸበሪው ሕወሓት የአማራ ክልልን ለመውረር ሲመጣ አብዛኛዎቹ የወራሪ ቡድኑ አባላት የመጡት ባዶ እጃቸውን ነው የምትለው ወዶ ዘማች መምህርት፤ ወገንም ከጠላቱ ተምሮ የሽብር ቡድኑ አገር ለማተራመስ የሚጠቀምበትን ምላሱን መቀሌ ድረስ በመሄድ መቁረጥ ይገባዋል።
በአማራ ክልል የተጠራውን የክተት አዋጅ ተከትሎ አሁን ወጣቱ እና ሚሊሻው ከየቦታው እጅግ በከፍተኛ ቁጥር ወደ ጦር ግንባር እየተመመ ይገኛል። ይህን ወጣት እና ሚሊሻ በትንሽ መስዋእትነት አሸናፊ እንዲሆን ለማስቻል የሚያግዙ የአደረጃጀት ሥራዎች ሲከናወንም ቆይቷል። (ሙሉቀን ታደገ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply