
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ዛሬ ምሽት በሰጠው መግለጫ ተደመሰሱ ካላቸው ውስጥ በፌዴራል መንግሥት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ጄነራሎችና ኮሎኔሎች ይገኙበታል።
በመግለጫው ላይ ተደመሰሱ የተባሉት ጄነራሎችና ኮሎኔሎች ስም አልተገለፀም።
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫ ይህን ነው ያሉት፦
“ባለፉት 2 ቀናት በባቲ ግንባር በተደረገ ልዩ ኦፕሬሽን 6 የአርሚና እና የኮር ከፍተኛ አመራሮቹ ተደምስሰዋል። እነዚህ አመራሮች በፌዴራል መንግሥት በሀገር ክህደት ወንጀል ሲፈጉ የነበሩ ከሃዲ ጄነራሎች እና ኮሎኔሎች ናቸው።
በተጨማሪ በከሚሴ ግንባር በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ልዩ ኦፕሬሽኖች የጠላትን ግንባር ጦር ሲመሩ የነበሩ 6 ከሃዲ ከፍተኛ የጦር አመራሮች ከነጠባቂዎቻቸው ተደምስሰዋል።
በዛሬው ዕለት በባቲ ግንባር በተደረገው ከፍተኛ የማጥቃት እርምጃ ቀደም ሲል ከነበሩት ጥቃቶች ተርፎ ለዳግም ማጥቃት ተዘጋጅቶ የነበረው የጠላት ኃይል የተደመሰሰ ሲሆን እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ኋላ እየፈረጠጠ ያለውን ጠላት እግር በእግር የወገን ኃይል እየተከተለ እያፀዳው እየገሰገሰ ይገኛል።
በሌሎች ግንባሮችም የወገን ጦር በሰነዘረው ከፍተኛ ማጥቃት ጠላት በከፍተኛ ደረጃ እየተመታ ይገኛል።
በዚሁ አጋጣሚ የወገንን ክንድ መቋቋም አቅቶት በተናጠል እና በቡድን እየሸሸ የሚገኘውን የጠላት ኃይል ዘረፋ እንዳይፈፅም እና ንብረት እንዳያወድም ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እንዲጠብቅ መንግሥት ጥብቅ ጥሪ ያቀርባል።

እንዳሁም እየሸሸ ያለው ጠላት እጁን እንዲሠጥ የማይሰጥ ከሆነ ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድ መንግሥት ያስገነዝባል። (ቲክቫህ እና ኢፕድ)
ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሞቱት መካከል አንዱ ት ህነጎች የሚተማመኑብትና የሚያመልኩት አብርሃ ተስፋየ ወይም ድንኩል የተባለው ይገኝበታል ይባላል።
ሌላው በቅዳሜ ምሽት ለእሁድ አጥቢያ ከሌሊቱ ፯ ሰዓት ላይ በመቀሌ የተፈጸመው የድሮን ጥቃት ፮ የትህነግ ሰዎች እንደሞቱ እየተነገረ ነው። ኬኒያዊው የደኀንነት መረጃ ባለቤት ካፒቴን ኮሊንስ ዋንዴሪ እንዳስታወቀው ሰዎቹ ምናልባትም ከፍተኛ ባለሥልጣናት ናቸው። ደብረጽዮን ገብረሚካኤልም በአካባቢው ነበር ተብሎ እንደሚታመን ጨምሮ ገልጾዋል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
እኮ በል ጉልጉሎች ረጋ በሉ። ወያኔ እኮ የራሱን ሞት ቀድሞ የሚያሰወራ ቡድን ነው። የደብረጽዪን እኮ ራሳቸው አንድ ጋ እጃቸውና ሌላው ሰውነታቸው ሌላ ጋ ተቀበሩ ተብሎ ባለፈው ሲዘባረቅ ሰምተናል። ግን የሆነው ያ አይደለም። የእጃቸውን ግለብ አውልቀው እንደገና ሲያስፈራሩን በትግራይ ቴሌቪዝን አይተናል። ወያኔ እባብ ነው። አንገቱን ስትቆርጠው ሌላው ሰውነቱ ቆሞ ለመራመድ ይሞክራል። እግራቸው ሲቆረጥ ከፍታ ላይ ሆነው ይፋለማሉ። ወሬው የተረጋገጠ ከሆነ እሰየው ፈጣሪ ከምድረ ገጽ ያጥፋቸው እንላለን። ግን አሜሪካና ሌሎች ሃገሮች በሳተላይት ድጋፍ የሚያደርጉለት የወያኔ ጥርቅም እንዲህ በቀላሉ በአንድ ሥፍራ ተሰብስቦ ለሞት ይበቃል ብሎ መገመት ከባድ ነው። የአሜሪካ ሴራ ጥልቅ ነው። እልፍ ጊዜ በሰላምና ዲሞክራሲ ስም ወደ አፍሪቃ ብሎም ወደ ኢትዮጵያ የሚመላለሱት እነዚህ ሙቶች በዋሽንግተን ዲሲ ጊዜአዊ መንግስት ካቋቋሙ በህዋላ ነው በሰውና በሃገር ላይ የሚቀልድት። ኬኒያታን በአብይ ላይ ጫና እንዲያደርግ የወተወቱትና በሙሉ ክብር በዋይት ሃውስ ተቀብለው ያስተናገድት አሜሪካኖች የመከሩት የኢትዮጵያ ጉዳይ አልቋል። አዲስ አበባ ሊገቡ 30 ኪ. ሜትር ቀራቸው፤ እኛና መሰሎቻችን ሰዎቻችን እያወጣን ነው በማለት ሲያዋክቡት ወይ ፍንክች ባለማለቱ መፍትሄ አጥተው አሜሪካኖች ሌላ ዘፈን ይዘው ብቅ ብለዋል።
አሁን ደግሞ ለይቶላቸው የኢትዮጵያ የአየር ሰማይ ላይ መብረር ዋስትና የለውም እያሉ እያናፈሱ ይባስ ብለው በአዲስ አበባና በከተሞች ጥቃት በአሸባሪዎች ሊደርስ ይችላል በማለት ወሬውን ይነዙታል። አሸባሪዋ አሜሪካ ናት። መረጃው ካላቸው ይህ ከመሆኑ በፊት ለምን ለመንግስት አካላት አካፍለው ጥበቃና የቀድሞ ማክሸፍ ሥራ እንዲሰራ አያደርጉም? እጃቸው እንዳለበት የሚያስታውቀው ለዚያ ነው።
አሁን በኢትዪጵያ ላይ አሜሪካ የምታደርገውን ሴራ ለመረዳት ታሪክን መለስ ብሎ በኢራን፤ በኢራቅ፤ በችሌ፤ በፓናማ እና በሌሎችም ሃገራት እንዴት አድርገው ለሃገርና ለወገን የሚያስቡ መሪዎችን በማጥፋት በራሳቸው አሻንጉሊቶች እንደተኳቸው ማየት ይቻላል። የቀድሞ የኢኮኖሚ የስለላ ሰው “The Economic Hit man” በተሰኘው መጽሃፉ ላይ የ 30 ዓመት ድርጊቱን ሲናዘዝ እያነበቡ አለማልቀስ አይቻልም። እጅግ ጭራቃዊ ስራ ነውና የሚሰሩት። ይህም በመሆኑ አሜሪካና ሌሎች የአውሮፓ ሃገሮች ወያኔን የሙጥኝ ቢሉ የሚያስገርም ነገር አይሆንም። ደም አፍሳሽና ሃገር አፍራሽ ህብረት ቢፈጥር እንግዳ ነገር አይደለም። ወያኔ ሸረኛና ተንኮለኛ ነው ይህን ሸሩንና ተንኮሉን የሚወድለት አሜሪካኖችም ተላላኪዎቻቸው መልሰው ስልጣን ላይ ለማውጣት ያልሞከሩት ነገር የለም። ስለዚህ የእነርሱ የሰላምና የዲሞክራሲ ጥሪ የማስመሰያ ካባ ነው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በህዋላ አሜሪካ ለሰው ልጆች መብት ቁማ አታውቅም። ለራሷ ጥቅም እንጂ!
ባጭሩ በዲሲ ያቋቋሙት ቡድን የሽግግር መንግስት መሆኑ ነበር። መሪውም ደም አፍሳሹና የሃገር ሃብትን የሟጠጠው ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ነው። ደርሰንበታል። ይህ ሌባና ደም አፍሳሽ እንኳን ሃገር ቤት ገብቶ መሪ ለመሆን መግባትም አይችልም። የአዲስ አበባ ወጣቶች ደብድበው ይገሉታል። ግፈኛ ሰው ነው። አምባሳደር ሆኖ የሰራቸውን ግፎች በቦታው ሁና የተመለከተች አንዲት ሰው ሥራቸው ሁሉ ስርቆትና ሌብነት ነው በማለት በእንባ በቦታው የተሰራውን አጫውታኛለች። እንግዲህ ይህን ሰው ነው አሜሪካ የሽግግር መንግስቱ መሪ ያደረገችው። ሰው ሰምቶና አይቶ ይፍረድ።
ግራም ነፈሰ ቀኝ የተባለው ቢባል። የተደረገው ሊደረግ ቢሞከር በጦር ሜዳው ላይ ወያኔ ተቀጥቅጦ ከተረታ ዞረው ተመልሰው እንርዳችሁ ማለታቸው አይቀሬ ነው። ስለሆነም የወታደራዊ የበላይነት ወያኔን ድባቅ መምታት ለአጭር ጊዜም ሆነ ለረጅሙ ትግል ወሳኝ ነው። በጦር ሜዳ ላይ ተሸንፎ ድርድር ላይ የፈለገውን ያገኘ አንድም መንግስት የለም። የህዝባችን አንድነት፤ የመንግስት ጥንካሬ የሚያመጣው ያ ሰላም አሜሪካና አውሮፓ ከሚሰጡን የእጅ አዙር ባርነት ይልቃል። እንበርታ። በቃኝ!